Saturday, December 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜና

ከፍተኛ ባለሥልጣናት አገሪቱ የምትመራበትን ሁለተኛ ዕቅድ በመንደፍ ላይ ናቸው

- ለስምንት ርዕሰ ጉዳዮች ኮሚቴ ተዋቅሯል የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገውን ሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በማዘጋጀት ላይ ናቸው፡፡

መንግሥት በካሩቱሪ ኩባንያ ላይ እምነት ማጣቱን አስታወቀ

- የኩባንያው ዕዳና የወሰደው መሬት አሳስቧል - የካሩቱሪ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በወሩ መጨረሻ የባንክ ዕዳዎች ይዘጋሉ ብለዋል የህንዱ ግዙፍ ኩባንያ ካሩቱሪ ግሎባል ሊሚትድ በኢትዮጵያ ሲያደርግ በቆየው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ መንግሥት እምነት እንዳጣበት ገለጸ፡፡

ለመሬት ሊዝ ጨረታ 305 ሺሕ ብር ያቀረበው ኩባንያ ውል ሳይፈጸም ቀረ

በአዲስ አበባ ከተማ ለሊዝ ጨረታ ለቀረበ መሬት በካሬ ሜትር 305 ሺሕ ብር ያቀረበው ዝዋይ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ኩባንያ ውል ሳይፈጽም ቀረ፡፡

ለኢትዮጵያዊው ሕልፈት ምክንያት ኢቦላ አለመሆኑን ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ማረጋገጫ ሰጠ

በኢቦላ ቫይረስ ተጠርጥሮ የነበረው ኢትዮጵያዊ ሕልፈት ምክንያት ኢቦላ አለመሆኑን፣ ከአገር ውስጥ በተጨማሪ በውጭ አገር ላብራቶሪ ምርመራ ውጤት መረጋገጡን፣ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጥር 8 ቀን 2007 ዓ.ም. አስታወቀ፡፡

የሰው ዘር አመጣጥ ታሪክን ክፍተት የሚሞሉ ቅሪቶች በኢትዮጵያ ተገኙ

ከተገኙት ቅሪተ አካላት መካከል አሥራ አንዱ የሰው ልዩ ልዩ አካል ክፍል ሲሆኑ፣ ዝርያቸው የጠፋና አሁንም ያሉ እንስሳትም ይገኙበታል፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት በባለአደራ ቦርድ እንዲመራ ተወሰነ

- ባለአደራ ቦርዱ አዲስ ምርጫ እስኪደረግ በጊዜያዊነት ይሠራል  የንግድ ሚኒስቴር የሚመራው ባለአደራ ቦርድ የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቱን እንዲረከብ ተወሰነ፡፡
- Advertisement -

አልሲሲ ለኢትዮጵያ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ዓባይ የግብፅ “የደም ሥር” ነው አሉ

የግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ አገሪቱን ሰሞኑን ለጎበኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ዓባይ (ናይል) ለግብፅ “የደም ሥር” እንጂ የልማት ምንጭ አይደለም አሉ።

የሽብርተኝነት ክስ ተመሥርቶባቸው የነበሩ ሁለት እንግሊዛውያን በጽኑ እስራት ተቀጡ

- ከሁለት ዓመታት በላይ ታስረዋል ጀመአተ ሙስሊም ጀሀድ አሸባሪ ቡድን በሚባል በህቡዕ ተደራጅቶ በሚንቀሳቀስ አሸባሪ ድርጅት ውስጥ፣ አባል ሆነው ‹‹በሸሪዓ የሚተዳደር እስላማዊ መንግሥት እንመሠርታለን›› የሚል ዓላማ ይዘው ሲንቀሳቀሱ መገኘታቸው ተገልጾ በቁጥጥር ሥር ውለው ክስ ተመሥርቶባቸው የነበሩ ሁለት እንግሊዛውያንና አንድ የሶማሊያ ዜጎች፣ በጽኑ እስራት እንዲቀጡ ጥር 6 ቀን 2007 ዓ.ም. ተወሰነባቸው፡፡

ዓቃቤ ሕግ በቀድሞ የጋምቤላ ፕሬዚዳንት ላይ በድጋሚ ምስክሮቹን ሊያሰማ ነው

​​​​​​​በአሁኑ ጊዜ የኖርዌይ ዜግነት ያላቸው ቀድሞ የጋምቤላ ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ኦኮሎ አኳይ ላይ ተሰምተው የነበሩ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ቃል ሳይቀረፅ በመቅረቱ፣ ከሳሽ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በድጋሚ እንዲያሰማ ታዘዘ፡፡

ኖክ በነዳጅ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ላይ መቆጣጣሪያ መሣሪያ ሊገጥም ነው

በኢትዮጵያ ከሚንቀሳቀሱ የነዳጅ ኩባንያዎች ቀዳሚ የሆነው ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ (ኖክ)፣ የነዳጅ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎችን የሚቆጣጠር ዘመናዊ መሣሪያ ጥቅም ላይ ሊያውል መሆኑን አስታወቀ፡፡
- Advertisement -