Wednesday, November 29, 2023

ሥነ ፍጥረት

- Advertisement -
- Advertisement -

እንቁላሎቿን ሆዷ ውስጥ የምትታቀፈው እንቁራሪት

እንቁላሎቿን ሆዷ ውስጥ የምትታቀፈው የአውስትራሊያ የእንቁራሪት ዝርያ (ጋስትሪክ ብሩዲንግ ፍሮግ) ያልተለመደ ዓይነት የመራቢያ ሥርዓት አላት፤ የዚህች እንቁራሪት ዝርያ ከ2002 ጀምሮ እንደጠፋ ይታሰባል የሚለው ጄደብሊው ዶት ኦርግ ድረ ገጽ ነው።

እንሽላሊቱ ኮሞዶ ድራጐን

ኮሞዶ ድራጐን የእንሽላሊት ዝርያ ነው፡፡ ከእንሽላሊት ዝርያዎች በትልቅነቱ የሚታወቀው ኮሞዶ፣ በማዕከላዊ ኢንዶኔዥያ ኮሞዶ ደሴት ላይ በብዛት ይኖራል፡፡ አንዱ ኮሞዶ ድራጐን እስከ 70 ኪሎ ግራም የሚመዝን ሲሆን፣ ርዝመቱም ከሁለት እስክ ሦስት ሜትር ይደርሳል፡፡ መጋዝ የመሰሉ 60 ጥርሶች አሉት፡፡ ጥርሶቹ በተደጋጋሚ እየወለቁ የሚበቅሉም ናቸው፡፡

ድምፅ አልባ አጥፊዎች

ምስጦች ድምፅ አልባ አጥፊዎች በመባል ይታወቃሉ፡፡ ይህ ስም የተሰጣቸው ዛፎችን፣ የዛፍ ስሮችንና ተክሎችን እንዲሁም የእንጨት ውጤቶችን ከላይ ሳይሆን ከሥር ገብተው ውስጡን ቦጥቡጠው ስለሚበሉና ቅርፊት ብቻ ስለሚያስቀሩ ነው፡፡ ምስጦች ለ24 ሰዓት ሳያቋርጡ የሚመገቡ ሲሆን፣ የተመቻቸ ስፍራ ካገኙ እዚያው መጠለያቸውን ሠርተው ይሰፍራሉ፡፡

የደን ንጉሥ

ቺምፓንዚ በጥንት ግሪኮች “የደን ንጉሥ” በመባል ይታወቃል፡፡  ቺምፓንዚ በመካከለኛው አፍሪካ ሰፊ ሥርጭት ያለው፣ በምዕራብ በኩል ከሴኔጋል አንስቶ እስከ ታንዛንያ የሚገኝ እንስሳ ነው፡፡

ፀጉሩ በክረምትና በበጋ የሚቀያየረው ሽኮኮ

ሽኮኮ ፅድ በሞላባችው ደኖች ውስጥ በብዛት ይገኛል። እንስሳው ረጅምና ፀጉራም በሆነው ጭራው በቀላሉ ይታወቃል። ፀጉሩ በክረምት ወቅት ቀይና ቡናማ ዓይነት ሲሆን፣ በበጋ ወቅት አመድማ ነጭ ይሆናል። ፍራፍሬና ተክሎች የሚመገብ ቢሆንም፣ ጫጩቶችንና የአዕዋፍ እንቁላል ሊበላ ይችላል። ክብደቱ እስከ ሁለት ኪሎ ግራም አካባቢ ይመዝናል።

ነጭ ጉጉት

ከጉጉቶች ሁሉ እንደበረዶ የነጡት ነጭ ጉጉቶች (Snowy owl) በአርክቲክ፣ ዛፍ በሌለበት ተንድራ አካባቢ ብቻ ይኖራሉ፡፡ ከሴቶቹ ይልቅ ወንዶቹ እንደበረዶ የነጡ መሆናቸውን ናሽናል ጂኦግራፊ በድረ ገጹ አሥፍሯል፡፡ ሴቶቹ እንደበረዶ በነጣው ላባቸው ላይ ቡናማ ወይም ጥቁር ነጠብጣብ አላቸው፡፡

አንበጦችና የነርቭ ሴላቸው

በራሪዎቹ አንበጦች እንቅስቃሴያቸውን የሚቆጣጠሩት በነርቭ ሴላቸው አማካይነት መሆኑ ይወሳል፡፡ ጄ ደብሊው ኦርግ በድረ ገጹ እንደጻፈው፣ በመንጋ የሚጓዙት አንበጦች ‹‹በአንድ ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት ውስጥ 80 ሚሊዮን›› አንበጦች አብረው ሊበርሩ ይችላሉ፡፡

እንሽላሊቶች

እንሽላሊቶች በብዙ ቦታ ተሰራጭተው የሚገኙ ናቸው፡፡ የብስ፣ ጎሬ፣ ውኃ እና ዛፍ ላይ ሁሉ ይገኛሉ፡፡ አብዛኞቹ አራት እግርና አጭር ቁመት ሲኖራቸው፣ እግራቸውም እምብዛምም ጠንካራና የዳበረ አይደለም፡፡

ሚዳቋ

ሚዳቋዎች Common duiker sylvicapra grimmia  በብዙ የአገራችን ክፍሎች ይገኛሉ፡፡ መጠናቸው ከሥፍራ ሥፍራ ቢለያይም፣ ሴቶቹ ከወንዶቹ ይልቅ ተለቅ ይላሉ፡፡ የወንዶቹ ከፍታ በአማካይ 50 ሴ.ሜ ደገማ ይሆናል፡፡

ጉሬዛ

ጉሬዛ (Abyssinian Black and White Colobus Colobus Guereza) ከአፍሪካ ጉሬዛ አስተኔዎች ሁሉ ተለቅ ያሉ፣ ሴቶቹ በአማካኝ 9.2 ኪግ ሲመዝኑ፣ ወንዶቹ ደግሞ 13.5 ኪግ የሚመዝኑ፣ ዛፍ ላይ የሚኖሩ እንስሶች ናቸው፡፡
- Advertisement -

ትኩስ ፅሁፎች

ትኩስ ዜናዎች ለማግኘት