Saturday, December 2, 2023

ርዕሰ አንቀጽ

ድጋፍና ተቃውሞ እኩል ይስተናገዱ!

ኢትዮጵያ ውስጥ ለረዥም ዓመታት ለመንግሥት ከሚቀርቡ ጥያቄዎች መካከል አንዱ የመብት መከበር ጉዳይ ነው፡፡ ዜጎች ተፈጥሯዊም ሆኑ ሕጋዊ መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው ለመንግሥት ጥያቄ ሲያቀርቡ፣ ጥያቄው የቀረበለት...

ፖለቲካዊ ችግሮች ፖለቲካዊ መፍትሔ ይፈለግላቸው!

መንግሥት ከኦነግ ሸኔ ጋር በታንዛኒያ ዳሬሰላም ከተማ ሲያካሂድ የነበረው ንግግር ያለ ውጤት መጠናቀቁን ካስታወቀ በኋላ፣ በኦሮሚያ ክልልም ሆነ በሌሎች ቦታዎች ሰላም ለማስፈን የነበረው ተስፋ...

ኢትዮጵያን ከግጭት ቀጣናነት ማላቀቅ የግድ ነው!

ፍሬ አልባ ፖለቲካዊ ልዩነቶች ወደ ግጭት እያመሩ ለአገርና ለሕዝብ የማያባራ መከራ ሲያቀባብሉ፣ ከትናንት ስህተቶች ለመማር ፈቃደኛ ያልሆኑ ፖለቲከኞችና ተከታዮቻቸው በእሳት ላይ ቤንዚን እያርከፈከፉ ጠማማ...
- Advertisement -
- Advertisement -

አስጨናቂውን የኑሮ ውድነት የማርገብ ኃላፊነት የመንግሥት ነው!

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ማክሰኞ ኅዳር 4 ቀን 2016 ዓ.ም. ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ካቀረቡላቸው ጥያቄዎች መካከል አንደኛው የኑሮ ውድነትን በተመለከተ ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የኑሮ ውድነት መኖሩን፣ ሰዎች በዚህ ምክንያት ለመመገብ እንደሚቸገሩና ጥያቄው እውነት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ‹‹…ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን እዚህ ከእኛ ቢሮ በመቶ ሜትር ርቀት ሰዎች ይቸገራሉ፡፡ ባለፉት 40 ዓመታት...

የአገር ጉዳይ የሁሉም ዜጎች የጋራ ኃላፊነት ነው!

በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፣ ለአገራቸው መፃኢ ዕድል ስኬት ሲሉ የሚፈለግባቸውን ሁሉ እንዲያደርጉ የሚፈለጉበት ወሳኝ ጊዜ አሁን ይመስላል፡፡ በኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ የፖለቲካ ዘመን ውስጥ ያለፉት ሃምሳ ዓመታት በርካታ ክስተቶች የታጨቁባቸው ናቸው፡፡ በወርኃ የካቲት 1966 ዓ.ም. ድንገት እንደ ደራሽ ውኃ ኢትዮጵያን ያጥለቀለቀው አብዮት፣ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ሥርዓት ብቻ ሳይሆን የዘውድ አገዛዝን ከሥሩ መንግሎ ከጣለ ሃምሳ ዓመታት...

በአገር ሰላም ላይ የተጋረጠው የጥፋት ጭጋግ ይገፈፍ!

ዓለም በሩሲያና በዩክሬን፣ በእስራኤልና በሐማስ አደገኛ ጦርነቶች፣ እንዲሁም በኮሪያ ልሳነ ምድር ውጥረትና በተለያዩ አካባቢዎች በሚቀሰቀሱ ግጭቶች፣ በተፈጥሮና በሰው ሠራሽ አደጋዎችና በተለያዩ ችግሮች ተቀስፋ ተይዛለች፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥም በትግራይ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያና በተለያዩ ሥፍራዎች ከፍተኛ ውጥረት ነው ያለው፡፡ የኢትዮጵያ ሰላም ደፍርሶ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ያለቁበት የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ለጊዜውም ቢሆን በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ጋብ ቢልም፣ በአማራ ክልል የቀጠለው ውጊያና በተለያዩ አካባቢዎች...

መንግሥት ለሰብዓዊ መብት ተቋማት ልዩ ትኩረት ይስጥ!

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባለፈው ሳምንት በአማራ ክልል እየተፈጸሙ ስላሉ የመብት ጥሰቶችና ሕገወጥ ድርጊቶች የሚመለከት መግለጫ ካወጣ በኋላ፣ በመንግሥት በኩል የኮሚሽኑን ሪፖርት በደፈናው የሚያጣጥልና ጥያቄ የሚያስነሳ ምላሽ መሰጠቱ እርምት ያስፈልገዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ በርካታ ተቋማት ውስጥ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ በተነፃፃሪ ኃላፊነቱን ለመወጣት ብርቱ ጥረት እያደረገ ያለን ተቋም፣ ስህተት ወይም ጥፋት ቢገኝበት እንኳ ነጥብ በነጥብ ችግሩን በተገቢው ቦታ...

ከምናባዊ መረጃዎች ይልቅ ለሚታዩ እውነታዎች ትኩረት ይሰጥ!

ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ መስኮች የተለያዩ ምናባዊ መረጃዎች ሲወጡ ብዙ ጊዜ የተዓማኒነት ጥያቄ ይነሳባቸዋል፡፡ የተዓማኒነት ጥያቄ የሚነሳባቸው በርካታ ምናባዊ መረጃዎችም አሳማኝ ምላሽ አያገኙም፡፡ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም ሆነ ለሌሎች አካላት የሚቀርቡ ብዙዎቹ ሪፖርቶች ላይ የተዓማኒነት ጥያቄዎች ይነሳሉ፡፡ ሪፖርት አቅራቢ የካቢኔ አባል የሆኑ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችም ሆኑ የእነሱ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት፣ በተደጋጋሚ በፓርላማ ቋሚ ኮሚቴዎች ሳይቀር ጥያቄዎች ሲቀርቡላቸው ከእውነታው ጋር የሚቀራረቡ...

በሰላምና በምግብ ዕጦት ለሚፈተኑ ወገኖች መፍትሔ ይፈለግ!

ለበርካታ ኢትዮጵያውያን የወቅቱ ከባዱ ችግር የሰላምና የምግብ ዕጦት ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ዜጎች ሰላም አጥተው በየቦታው በነፃነት መንቀሳቀስም ሆነ መሥራት ሲቸግራቸው በስፋት ይስተዋላል፡፡ በትግራይ ክልል ውስጥ ተጀምሮ ለሁለት ዓመታት ያህል የዘለቀው ጦርነት በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ቢገታም፣ በትግራይ ብቻ ሳይሆን በአማራና በአፋር ክልሎች ላይ ያደረሰው ዕልቂትና ውድመት አይዘነጋም፡፡ በፕሪቶሪያ ስምምነት መሠረት አንፃራዊ ሰላም ሊሰፍን ነው ተብሎ በተስፋ ሲጠበቅ፣ በአማራ ክልል...

ለአገር ሰላምና ደኅንነት ሲባል ችግር አባባሽ ድርጊቶች ይወገዱ!

የኢትዮጵያ ውሎና አዳር አስተማማኝ ባልሆነበት በዚህ አስጨናቂ ጊዜ፣ ከምንም ነገር በላይ ግጭቶችን ማስቆም ቅድሚያ የሚሰጠው የተቀደሰ ተግባር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሞችና ደኅንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ሊከበሩ የሚችሉት፣ ለግጭቶች መነሳትም ሆነ መባባስ ምክንያት የሚሆኑ ችግሮች መፍትሔ እንዲያገኙ የጋራ ጥረት ሲኖር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብን ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ፣ ኢኮኖሚውን ካለበት የችግር መንጋጋ ለማላቀቅ፣ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ አሁን ካለበት አስፈሪ አዘቅት ውስጥ ለማውጣት፣ ለወጣቶች...

የአገር ህልውና የቆመባቸው ምሰሶዎች ልዩ ጥንቃቄ ይፈልጋሉ!

የአንድ አገር መሠረታዊ የህልውና ምሰሶዎች ተብለው የሚታወቁት የሕዝቡ አንድነት፣ የጋራ ታሪኮች፣ ሰላምና ፀጥታ፣ የሕግ የበላይነት፣ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች፣ ልማትና የጋራ ተጠቃሚነት፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ መስተጋብሮችና የመሳሰሉት ከብዙ በጥቂቱ ይጠቀሳሉ፡፡ በእነዚህ ምሰሶዎች ላይ የሚታነፅ አገረ መንግሥት በምርጫ በሚለዋወጡ የመንግሥት አስተዳደሮች እየተጠናከረ፣ ህልውናውን አስጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ በመተላለፍ በቁሳዊም ሆነ በሰብዓዊ ሀብት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ይደርሳል፡፡ በኢትዮጵያ ከእነ ችግሩም ቢሆን አገር የቆመችባቸው...

ማህበራዊ ሚዲያዎች

167,329FansLike
276,491FollowersFollow
13,800SubscribersSubscribe
- Advertisement -

ትኩስ ዜናዎች ለማግኘት

ትኩስ ዜናዎች

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...

ሀብቱንና ትርፉን እያሳደገ የቀጠለው አዋሽ ባንክ

አዋሽ ባንክ በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ዋና መሥሪያ ቤት...