Tuesday, May 21, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የቆዳ አምራች ድርጅቶች ከወታደር ጫማ ሽያጭ ምርት ከፍተኛ ገቢ እንዳገኙ ተገለጸ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

በሳሙኤል ቦጋለ

በተያዘው በጀት ዓመት በአሥር ወራት ውስጥ ከቆዳ አምራች ድርጅቶች በአገር ውስጥ ገበያ ለማግኘት ታቅዶ ከነበረው 104.6 ሚሊዮን ዶላር፣ 144.6 ሚሊዮን ዶላር በማስመዝገብ የዕቅዱን 138.2 በመቶ ዕድገት ማስመዝገብ መቻሉንና ይህም የተገኘው በአገር ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የወታደር ጫማ በማምረት መሆኑ ተገለጸ፡፡

ምንም እንኳን በአምራቾቹ በዚህ አሥር ወራት ውስጥ ወደ ውጪ ለመላክ ታቅዶ ከነበረው 69.21 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ የዕቅዱን ከግማሽ በታች ወይም 33.14 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ለመላክ የተቻለ ቢሆንም፣ በአገር ውስጥ አምርቶ ለገበያ ለማቅረብ የቻሉት ግን ከዕቅዳቸው በላይ እንደሆነ የቆዳና የቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪ ምርምርና ልማት ተቋማት ገልጸዋል፡፡

አምራቾቹ የተለያዩ ጫማዎችንና የቆዳ ውጤቶችን ቢያመርቱም፣ ባለፉት አሥር ወራት ከፍተኛ የሆነ የወታደር ጫማ ምርቶችን ትዕዛዝ የተቀበሉ መሆኑንና ይህንንም በማምረት ከውጭ በማስገባት ሊወጣ የሚችለውን የውጭ ምንዛሪ ማስቀረታቸውን የተቋሙ ምክትል ዳይሬክተር አቶ መሐመድ ሁሴን ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

‹‹አምራቾቹ ለአገር ውስጥ ምርት ትኩረት ሰጥተው ሳያመርቱ ቢቀሩና በውጭ ንግዱ ላይ ብቻ ተንጠልጥለው ቢሆን ኖሮ አብዛኞቹ ድርጅቶች መዘጋታቸው አይቀርም ነበር፤››፡፡ የገንዘብ እጥረት እንዳጋጠማቸውና የተዘጉም የተወሰኑ ፋብሪካዎች እንዳሉ አቶ መሐመድ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ የወታደር ጫማዎችን ለተለያዩ የአፍሪካ አገሮች እንደ ዑጋንዳና ዴሞክራቲክ ኮንጎና ሌሎችም አገሮች ወደ ውጭ ኤክስፖርት የምታደርግ መሆኗንም ምክትል ዳይሬክተሩ አክለው ገልጸዋል፡፡

ከአገር ውስጥ አምራች ድርጅቶች መካከል በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ውስጥ የሚገኘው ኢትዮ ሌዘር ኢንዱስትሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሲሆን፣ ድርጅቱም አምስት ፋብሪካዎች አሉት፡፡ ሁለቱ የጫማ ፋብሪካዎች ሲሆኑ ከሚያመርታቸው ምርቶች አብዛኞቹም በአገር መከላከያ፣ በፌዴራል ፖሊስ፣ በክልል ፀጥታ ተቋማት የሚገለገሉበት ጫማዎች ናቸው፡፡

‹‹ከመከላከያና ከፀጥታ ተቋማት ከፍተኛ ትዕዛዞች እንቀበላለን፤›› ሲሉ የገለጹት የድርጅቱ ንግድ ኃላፊ አቶ ኃይለ ኪሮስ ደበሳይ፣ አብዛኞቹን ትዕዛዞችም በቀጥታ ግዥ ከድርጅታቸው እንደሚፈጸም ገልጸዋል፡፡

እንደ ምክንያት የጠቀሱትም ድርጅቱ ያለውን የጥራት፣ የሥራን ፍጥነት ነው፡፡ ‹‹የጫማ ትዕዛዞችን ለማድረስ በሁለት ሽፍት እንሠራለን ሲሉ አቶ ኃይለ ኪሮስ ገልጸዋል፡፡

ድርጅቱ በአሁኑ ሰዓት እስራኤልና ጣሊያንን ጨምሮ ለበርካታ የአውሮፓና አፍሪካ አገሮች ኤክስፖርት የሚያደርግ ሲሆን፣ ከኤክስፖርቱ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሪ በብሔራዊ ባንክ ትዕዛዝ መሠረት ከ20 በመቶ በላይ ባለማግኘቱ ከፍተኛ የሆነ ችግር ውስጥ እንደገባም ገልጿል፡፡ እንደ ኬሚካል ዓይነት ግብዓቶችን ከውጭ አገር ያስገባል፡፡ ይህ በኤክስፖርተሮች ላይ የተላለፈው የውጭ ምንዛሪ፣ የውጭ ንግዱ ላይ ተፅዕኖ እንደፈጠረ ቢገመትም፣ አንደ ተቋሙ ምክትል ዳይሬክተሩ ገለጻ ግን የኮቪድ ተፅዕኖ አንደኛው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ‹‹የአጎዋ መታገድም ሌላው ለውጭ ንግድ ማነስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፤›› ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች