Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለጤና ኢንሹራንስ ብቁ የሆኑ ዜጎች የግዴታ ውል እንደሚገቡ ተገለጸ

ለጤና ኢንሹራንስ ብቁ የሆኑ ዜጎች የግዴታ ውል እንደሚገቡ ተገለጸ

ቀን:

በውይይት ላይ ያለው ረቂቅ የማኅበረሰብ አቀፍ የጤና መድን አዋጅ በፓርላማው ፀድቆ ወደ ሥራ ሲገባ፣ ለጤና ኢንሹራንስ ብቁ የሆኑ ዜጎች በግዴታ ውል እንደሚገቡ ተገለጸ፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በላከው ረቂቅ የጤና መድን አዋጅ ላይ ተወያይቶበታል፡፡ ረቂቅ አዋጁ በአሁኑ ወቅት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት እየተደረገበት የሚገኝ ሲሆን፣ መደበኛ ባልሆነው ዘርፍ የተሰማራ ማንኛውም ሰው በአስገዳጅነት የማኅበረሰብ አቀፍ የጤና መድን አባል እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

መደበኛ ባልሆነው የሥራ ዘርፍ የተሰማራውን የኅብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለው የማኅበረሰብ አቀፍ የጤና መድን ሥርዓት ከ2003 ዓ.ም. ጀምሮ በሙከራ ደረጃ በአራት ክልሎች በተመረጡ 13 ወረዳዎች ተጀምሮ፣ በአሁኑ ወቅት ከ770 ወረዳዎች በላይ እየተተገበረ እንደሚገኝ የጤና፣ ማኅበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድን ረቂቅ አዋጅ ላይ ከአስረጂ አካላት ጋር፣ ሰኞ መጋቢት 26 ቀን 2014 ዓ.ም. ውይይት ባደረገበት ወቅት ተብራርቷል፡፡

 ይሁን እንጂ ይህ አስቀድሞ በሚደረግ አነስተኛ መዋጮ የጤና አገልግሎት ወጪ የሚሸፈንበት ሥርዓት፣ የከፍተኛ የጤና ወጪ ሥጋትን በመቅረፍና ፍትሐዊነትን በማረጋገጥ፣ ሁሉም እንደ ሕመሙ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያስችል የተባለለት አግልግሎት ከዚህ በፊት የሕግ ማዕቀፍ አልተዘጋጀለትም ነበር፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ ጥር 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ባካሄደው 3ኛ ልዩ ስብሰባው፣ የማኅበረሰብ ዓቀፍ የጤና መድን ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 4/2014 ላይ ተወያይቶ ለጤና፣ ማኅበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ  ለዝርዝር ዕይታ  መምራቱ ይታወሳል፡፡

በዚህ ረቂቅ አዋጅ መሠረት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራና ሁሉም የክልል ፕሬዚዳቶች አባል የሆኑበት ‹‹የማኅበረስብ አቀፍ ጤና መድን ብሔራዊ ምክር ቤት›› የሚባል ተቋም ይቋቋማል፡፡

ምክር ቤቱ ለማኅበረሰብ አቀፍ የጤና መድን ሥርዓት ትግበራ የሚረዱ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን እንደሚሰጥ ተቀምጧል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...