Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚታዩ የሕግ ጥሰቶች እየጨመሩ መሆናቸው ተገለጸ

በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚታዩ የሕግ ጥሰቶች እየጨመሩ መሆናቸው ተገለጸ

ቀን:

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ሥርዓቱ ከሚፈቅደው ውጪ የሚፈጽሟቸው የሕግ ጥሰቶች እየጨመሩ መሆናቸው በሪፖርት ቀረበ፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈቃድ አሰጣጥና ጥራትና ቁጥጥርን በተመለከተ፣ በ2012 እና በ2013 ዓ.ም. ያከናወነው የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት መጋቢት 22 ቀን 2014 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ቀርቦ፣ ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡

በውይይቱ ወቅት በቀድሞ ስሙ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ አሁን የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን የሚከታተላቸው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተገኙባቸው የሕግ ጥሰቶች ተገልጸዋል፡፡

ለአብነት ከተጠቀሱት መካከል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ከሚገኙና በናሙና ከተመረጡ 17 ከፍተኛ የግል ትምህርት ተቋማት፣ ከአዋጅና ከመመርያ ውጪ በመጀመርያ ዲግሪና በማስተርስ ዲግሪ ከ180 እስከ 200 በመቶ ከተፈቀደላቸው በላይ  ተማሪዎች መዝግበው ሲያስተምሩ መገኘታቸው በሪፖርቱ ተመልክቷል፡፡

የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አንዷለም አድማሴ (ዶ/ር) እንዳሉት፣ ከተፈቀደላቸው በላይ ከፍተኛ የተማሪዎች ቁጥር ለአብነትም በሦስት ዓመታት ውስጥ 15 ሺሕ የማስተርስ ተማሪዎችን ያስመረቀ የትምህርት ተቋም ተዘግቷል፡፡

ችግር ታይቶባቸዋል ከተባሉት ተቋማት መካከል ድንገተኛ ፍተሻ ሲካሄድባቸው ሁለትና ሦስት መዝገብ ቤቶች አዘጋጅተው አንዱን ተቆጣጣሪ ባለሥልጣኑ በሚፈልገው ልክ የተዘጋጀ መረጃ፣ ሁለተኛው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች የተመዘገቡበት መረጃ የሚይዝና ተቋሙ ለራሱ ቁጥጥር እንዲያመቸው፣ ለሌላ ዓላማ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ሦስተኛ መዝገብ ቤት እንደሚያዘጋጁ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አስረድተዋል፡፡

በናሙና ከታዩት ትምህርቶች ውስጥ በኢንጂነሪንግ ቴክኖሎጂ፣ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ በተፈጥሮ ሳይንስና በኮምፒውቴሽናል ሳይንስ፣ በፊዚዮቴራፒ፣ በአካባቢ ሳይንስ፣ በራዲዮሎጂ ሕክምና፣ በጥርስ ሕክምና የትምህርት ዘርፎች የዕውቅና ስታንዳርድና የብቃት ማረጋገጫ መመርያ በባለሥልጣኑ አለመሰጠቱ ተገልጿል፡፡

የኦዲቱ ሪፖርት እንደሚያሳየው ባለሥልጣኑ ከሕግና ከጤና ተማሪዎች በስተቀር፣ በሌሎች የትምህርት መስኮች የሙያ ብቃት ምዘና የሚካሄድበት ሥርዓት አልዘረጋም፡፡

በሌላ በኩል የብቃት ማረጋገጫ (COC) ሳይፈተኑ ወይም ማረጋገጫ ሳያቀርቡ የዲግሪ ፕሮግራም የሚማሩ ተማሪዎች ስለመኖራቸው፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከሚያስተምሩ መምህራን ተገቢውን ሥልጠና ያልወሰዱ በብዛት መኖራቸው ተነግሯል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ምክትል ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ በበኩላቸው፣ መሥሪያ ቤታቸው በባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ላይ በ2001 ዓ.ም. ተመሳሳይ ኦዲት አደርጎ እንደነበረ አስታውሰው የተጠቀሱት ችግሮች ከ11 ዓመታት በኋላም ሳይፈቱ መገኘታቸውን ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...