Monday, April 15, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የታሸገ ውኃ አምራቾች የጉምሩክ ዋጋ ትመና ለኪሳራ እየዳረገን ነው አሉ

ተዛማጅ ፅሁፎች

የታሸገ ውኃ አምራቾች ከውጭ ለሚያስገቧቸው ጥሬ ዕቃዎች የሚጠየቁት የጉምሩክ ዋጋ ትመና፣ ለኪሳራ እየዳረጋቸው በመሆኑ ማስተካከያ እንዲደረግ ጠየቁ፡፡

አምራቾቹ በተለይም በአሁኑ ወቅት በገጠማቸው የጥሬ ዕቃ እጥረትና የዋጋ መወደድ ምክንያት ማምረት እየተቸገሩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ውኃ አምራቾቹ ውኃ ማምረት የሚያስፈልጉ ስምንት ያህል ጥሬ ዕቃዎችን ቻይናን ጨምሮ ከተለያዩ አገሮች የሚያስመጡ ሲሆን፣ በተለይም በብዛት የሚያስመጡት ፒኢቲ የተባለው ጥሬ ዕቃ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ማሳየቱን ተናግረዋል፡፡

ከአንድ ዓመት ባነሰ ዜ ውስጥም ከነበረበት 53 ብር በኪሎ ግራም ወደ 180 ብር ከፍ ማለቱን የኢትዮጵያ ውኃ፣ ለስላሳ መጠጦች፣ አትክልትና ፍራፍሬ አምራቾች ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ አሸናፊ መርዕድ ገልጸዋል፡፡

እንደ አቶ አሸናፊ ገለጻ በአሁኑ ወቅት 21 አምራቾች ሙሉ በሙሉ ሥራ ያቆሙ ሲሆን፣ 3,000 የሚጠጉራተኞችም ከሥራ ውጭ ሆነዋል፡፡ ለዚህም በተለይ ከጥሬ ዕቃ ዋጋ ከፍ ማለት በተጨማሪ፣ የጉምሩክ ቀረጥ ክፍያ ጫና እየፈጠረባቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ከውጭ የሚገባው ጥሬ ዕቃ ከሚገዛበት ዋጋ በላይ በጉምሩክ የዋጋ ትመና እንደሚጣልበት የገለጹት አቶ አሸናፊ፣ እስከ ሁለት ዶላር በኪሎ ግራም የተገዛን ጥሬ ዕቃ ከስድስት ዶላር በላይ እንደተገዛ ተድርጎ እንደሚመዘገብ አስረድተዋል፡፡ ይህም አምራቾች ከፍተኛ የጉምሩክ ቀረጥ እንዲጠየቁና ተጨማሪ ጫና ውስጥ እያስገባቸው እንደሚገኝ ተናግረው፣ ጉምሩክ ኮሚሽን ማስተካከያ እንዲያደርግበት ጠይቀዋል፡፡

የፍቅር ውኃ ማናጀር አቶ ቢኒያም ዘለቀ ድርጅታቸው በቂ ጥሬ ዕቃ ባለማግኘቱ፣ እንዲሁም በዋጋ ጭማሪው ምክንያት 40 በመቶ አቅማቸው ብቻ እያመረቱ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ አምራቾች የሚወስዱት ብድር እስከ 18 በመቶ ወለድ የሚታሰብበት መሆኑንና ይህም ከአስመጪዎች እኩል የሚስተናገዱበት በመሆኑ፣ ቢያንስ አሥር በመቶ ያልበለጠ ወለድ ብቻ መጠየቅ እንዳለበት ገልጸው፣ በጉምሩክ በኩል የሚጣለው ቀረጥ ደግሞ ኪሳራ ውስጥ እያስገባቸው እንደሚገኝ አክለዋል፡፡ የዋጋ ግምቱ ከጥሬ ዕቃ አስመጪዎች ጋር በተመሳሳይ አሠራር መስተናገድ የለበትም ብለዋል፡፡

ጥሬ ዕቃዎቹ ከተለያዩ አገሮችና አምራቾች በተለያየ ዋጋ ሊገዙ እንደሚችሉ ግምት ውስጥ በማስገባትም ማስተካከያ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን የዋጋ ጥናትና ትመና ዳይሬክተር አቶ አዲስ አየለ በበኩላቸው፣ የዋጋ ግምቱ የዓለም ንግድ ድርጅት የሚከተለውን የዋጋ ግምት መነሻ በማድረግ የሚሠራ መሆኑን ገልጸው፣ ጭማሪም ሆነ ቅናሽ ሲኖር ማስተካከያ እንደሚደረግበት አስረድተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በተለይ ከነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ጋር ተያይዞ ዋጋቸው በጨመሩ ምርቶች ላይም፣ ከየካቲት 20 ቀን 2014 .ም. ጀምሮ ማስተካከያ መደረጉን አብራርተዋል፡፡

አስመጪዎችም ይሁኑ አምራቾች የጥሬ ዕቃ መግዣ ዋጋ ሲያቀርቡ ከፍተኛ ቅናሽ አድርገው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ 90 በመቶ በላይ የሚሆኑትም በቶን 1,000 ዶላር በላይ የሚገዛውን የፕላስቲክ ጥሬ ዕቃ፣ በአምስትና በአሥር ዶላር እንደገዙት አድርገው ያቀርባሉ ብለዋል፡፡

ኮሚሽኑ የሚተገብረው የዋጋ ግምትለም አቀፍ ገበያውን መሠረት ያደረገ፣ እንዲሁም የዋጋ ዝርዝሩን የያዘ ዳታ ቤዝን በመጠቀም በመሆኑ ልዩነት የሚፈጥር አለመሆኑን ተናግረዋል::

የፕላስቲክ ውኃ ዘርፉ 134 አምራቾችን ያቀፈ እንደሆነ 4.5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚንቀሳቀስበትና በቀጥታና በተዘዋዋሪ 126,000 በላይ ለሆኑ ሰዎች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን የኢትዮጵያ ውኃ፣ ለስላሳ መጠጦች፣ አትክልትና ፍራፍሬ አምራቾች ማኅበር መረጃ ያሳያል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች