Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየወልቃይት አካባቢ ከተሞችን የኤሌክትሪክ እጥረት ይፈታል የተባለው ፕሮጀክት በውጭ ምንዛሪ ምክንያት መስተጓጓሉ...

የወልቃይት አካባቢ ከተሞችን የኤሌክትሪክ እጥረት ይፈታል የተባለው ፕሮጀክት በውጭ ምንዛሪ ምክንያት መስተጓጓሉ ተገለጸ

ቀን:

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በወልቃይትና ሁመራ አካባቢ በጦርነቱ ኤሌክትሪክ ለተቋረጠባቸውና የተፈጠረውን የኤሌክትሪክ አቅርቦት እጥረት ለመፍታት ያግዛል በሚል ከጥቂት ወራት በፊት አዲስ የኃይል መስመር ለመገንባት ከቻይና ኩባንያ ጋር የተፈራረመው ስምምነት፣ በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት መስተጓጎሉ ተገለጸ፡፡

ከአንድ ዓመት በላይ በሰሜኑ ኢትዮጵያ በተካሄደው ጦርነት የኤሌክትሪክ አገልግሎት የተቋረጠባቸውን የወልቃይትና ሴቲት ሁመራ ዞን አካባቢዎች ይሸፍናል የተባለውና ከጎንደር-ዳንሻ፣ ባዕከር እስከ ሁመራ እንደሚገነባ ታስቦ የነበረው የ132 ሺሕ ኪሎ ቮልት ተሻካሚ መስመር እንደታሰበለት መሄድ እንዳልቻለ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኰንን ለሪፖርተር ተናገሩ፡፡

ጦርነቱ ከመከሰቱ በፊት ከተከዜና ሽሬ የኃይል ማሠራጫ ጣቢያዎች ኃይል ያገኙ የነበሩት የወልቃይት፣ ሁመራ፣ ባዕከርና ዳንሻ አካባቢዎች የኃይል መነሻዎቻቸው በሕወሓት ቁጥጥር ሥራ ካሉ አካባቢዎች በመሆኑ፣ የተጠቀሱት ቦታዎች ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ውጪ እንደሆኑ የገለጹት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት የአማራ ክልል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰሎሞን ጣሰው ናቸው፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚው እንደሚሉት፣ ከወልቃይትና አካባቢው በተጨማሪ፣ የኃይል መስመር መነሻው አላማጣ የሆነ የ66 ሺሕ ኪሎ ቮልት የኃይል መስመር ሰብስቴሽን በቁጥጥር ሥር የዋለ በመሆኑ፣ የዋግ ሕምራ ዞንና የሰሜን ወሎ ከፊል አካባቢዎች በተለይም በላሊበላ፣ ቆቦና አቅራቢያው ያሉ ከተሞች የመብራት አገልግሎት ለወራት እንደተቋረጠባቸው ነው፡፡

የፌዴራል መንግሥቱ ከሕወሓት ኃይሎች ጋር ሲያደርግ የነበረው ጦርነት፣ በአመዛኙ ተጠናቆ በጦርነት የወደሙ የኤሌክትሪክ መሠረተ ለማቶች የተጠገኑ ቢሆንም፣ በተጠቀሱት አካባቢ አገልግሎቱን ለማቅረብ ፈታኝ መሆኑን አቶ ሰሎሞን አክለው ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...