Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናገዥው ፓርቲ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውን የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች በአስፈጻሚነት ለማካተት ዝግጁ...

ገዥው ፓርቲ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውን የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች በአስፈጻሚነት ለማካተት ዝግጁ ነኝ አለ

ቀን:

ገዥው ብልፅግና ፓርቲ ቀደም ሲል በመንግሥት ኃላፊነት ከመደባቸው በተጨማሪ፣ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውን የፓርቲዎች አመራሮች ለማካተት ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በሐሳብ የሚታገሉ፣ ነገር ግን ብልፅግና ወይም ሥልጣን ላይ ያለ ሰው ሲሳሳት የተገኘችውን አጀንዳ እያስጮሁ ብሔርን ከብሔር ሃይማኖትን ከሃይማኖት፣ እንዲሁም ሰውን ከሰው የሚያጋጩ አብሪ ኮከብ መሆን እንደሌለባቸው፣ የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

በ2013 ዓ.ም. የተካሄደውን አገራዊ ምርጫ በበላይነት በማሸነፍ መስከረም 24 ቀን 2013 ዓ.ም. መንግሥት የመሠረተው የብልፅግና ፓርቲ፣ የተወሰኑ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮችን በካቢኔ ውስጥ ማካተቱ ይታወሳል፡፡

አሁንም ብልፅግና በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ሐሳብ፣ የሚነበብና የሚደመጥ ዕሳቤ ያላቸውን ፓርቲዎች በመንግሥት ሥራ ውስጥ ለማካተት ፈቃደኛ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በ2012 ዓ.ም. የተመሠረተው ገዥው የብልፅግና ፓርቲ ከመጋቢት 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት  አንደኛ ጉባዔውን በአዲስ አበባ ከተማ እያካሄደ ነው፡፡

በብልፅግና ጉባዔ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፓርቲው ፕሬዚዳንት፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎቸ በውስጣቸው ዴሞክራሲያዊነትንና አዳዲስ መሪዎችን ማፍራት እንዲለማመዱ፣ እንዲሁም በሐሳብ ልዕልና መነጋገር የሚችሉ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

 ከ1600 በላይ በድምፅ የሚሳተፉ የፓርቲው አባላት፣ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችና ከውጭ አገሮች 400 ተሳታፊዎች በሆኑበትና ዛሬ እሑድ መጋቢት 4 ቀን 2014 ዓ.ም. በሚጠናቀቀው የመጀመሪያ ጉባዔ፣ በርካታ ውሳኔዎችን በማሳለፍና ጠንካራ የፓርቲ አመራሮችን በመምረጥ ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡

ብልፅግና የአባልነት መዋጮ የሚያዋጡ ከ11 ሚሊዮን በላይ አባላት እንዳሉት የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፣ ፓርቲያቸው  በኢትዮጵያም ብቻ ሳይሆን በአፍሪካም ግዙፍ እንደሆነና ብልፅግና ፓርቲ ከኢሠፓ፣ ከመኢሶን፣ ከኢሕእፓ፣ እንዲሁም ከኢሕአዴግ የሚለየው፣ ‹‹መጤ በሆነ ዕሳቤ ሳይሆን መደመርን እንደ መንገድ በማድረግ ብልፅግናን መዳረሻ ያደረገ በመሆኑ ነው፤›› ብለዋል፡፡

በጉባዔው የቱርክ ጀስቲስ ኤንድ ድቨሎፕመንት ፓርቲ፣ የደቡብ አፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ፣ የጂቡቲ ፒፕልስ ራሊ ፎር ፕሮግረስ ፓርቲ፣ የደቡብ ሱዳን ኤስፒኤልኤም የኡጋንዳ ገዥ ፓርቲ ተወካዮች በጉባዔው ላይ ንግግር አድርገዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ኃላፊ ራሄል ባፌ (ዶ/ር) በጉባዔው መከፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ሊካሄድ የታሰበው አገራዊ ምክክር በመንግሥት ተቀባይነትና ሙሉ ድጋፍ የሚካሄድ በመሆኑ፣ የሒደቱን አካታችነትና ኮሚሽኑ ነፃ ሆኖ የሚሠራ መሆኑን ለማረጋገጥ፣ ገዥው ፓርቲ እጅግ የላቀ ታሪካዊ ድርሻ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡

ገዥው ፓርቲም ሆነ ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች በባለቤትነትና በኃላፊነት የሚጠበቅባቸውን ገንቢ ሚና በመወጣት፣ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ የአዲስ ምዕራፍ ጅምር እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ (ዶ/ር)፣ ‹‹ፓርቲያቸውና መንግሥታቸው ኢትዮጵያን የሚያጠናክር ሐሳብ ከምክክር መድረኩ እንዲወለድ የፀና ፍላጎታችን ነው፤›› ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...