Monday, April 15, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የግብር ከፋይ ቅሬታዎችን ይፈታል የተባለ መመርያ ተዘጋጀ

ተዛማጅ ፅሁፎች

የገቢዎች ሚኒስቴር የሒሳብ መዝገብ አያያዝ መመርያ ቁጥር 152/2011 በማሻሻል፣ በብድር አሰጣጥና በካፒታል ማሳደግ ምዝገባ ሒደት ላይ እየተፈጠሩ ያሉ ቅሬታዎችን ለመፍታት ያስችላል የተባለ ረቂቅ ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

ከአራት መታት በፊት የወጣው የሳብ አያያዝ መመበሥራ ላይ ከዋለ ጊዜ ጀምሮወቅቱ ከውልና ማስረጃ፣ እንዲሁም ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር ያለው አሠራር የተቃረነ እንደሆነ በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ኦዲት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ አበበ ገልጸዋል።

አሁን በሥራ ላይ የሚገኘው መመርያ ከታክስ አስተዳደርርዓት ጋር የሚጣረስና ወቅቱ ከሚፈልገው የቢዝነስ ተለዋዋጭነት ጋር የሚጋጭ መሆኑን በመጥቀስ፣ በተለይ በብድርና በካፒታል ማሳደግ ምዝገባ ሒደት ላይ ችግሮች ማጋጠማቸውን ተናግረዋል።

አዲሱ መመርያ ከፋይናንስ ተቋማት ብድር በሚወሰድበት ወቅት ገንዘቡ በቀጥታ ለተጠየቀበት ሥራ መዋሉ መረጋገጥ እንዳለበት ያዛል። በተጨማሪም ከፋይናንስ ተቋማት ውጪ በመንደር ውል የሚወሰዱ ብድሮች በግብር ሰብሳቢው አካል ዕውቅና ያገኛሉ ተብሏል።

መመርያው በ2011 ዓ.ም. ከመውጣቱ በፊት የነበሩ የሒሳብ መዝገቦችን ኦዲት ማድረግ ቅሬታ ሲፈጥር የነበረ ሲሆን፣ በአዲሱ መመርያ መሠረት ግን ቀደም ሲል የነበሩ የሒሳብ ሰነዶች አይመለከታቸውም፡፡

ስለሰነድ አቀራረብና ሰነድ ተሟልቶ ባልቀረበ ጊዜ ሊኖር ስለሚገባው አሠራር፣ እንዲሁም ከውልና ማስረጃና ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በተያያዘ የካፒታል ማሳደግ ምዝገባ ለማድረግ የሚሰጠው ጊዜ በቂ ሳይሆን ሲቀር፣ በግብር ከፋዮች ላይ ጫና የሚያሳድሩ ሆነው መገኘታቸውን አቶ ብርሃኑ ገልጸዋል።

በዚህም መሠረት በካፒታልነት እንዲመዘገብ ጥያቄ ቀርቦበት ያልተመዘገበ ሒሳብ፣ በገቢነት ተመዝግቦ ግብር እንዲከፈልበት የሚደረግ በመሆኑ፣ ይህም ግብር ከፋዮችን የሚጎዳ መሆኑን አብራርተዋል።

አዲሱ መመርያ በተለይም የአክሲዮን ማኅበራት ጠቅላላ ጉባዔያቸውን አድርገው ካፒታል እንዲያድግ ከወሰኑበት ጊዜ ጀምሮ ባለው አንድ ዓመት ውስጥ፣ በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴርና በውልና ማስረጃ እንዲያስመዘግቡ የሚያዝ ሲሆን፣ በተሰጠው ጊዜ ውስጥ ካልተጠናቀቀ ተጨማሪ ጊዜ ታሳቢ እንዲደረግ የሚጠይቅ ነው

አዲሱ መመርያ ከውልና ማስረጃ፣ እንዲሁም ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር ንግግር እየተደረገበት እንደሚያገኝ የገለጹት አቶ ብርሃኑ፣ ከአንድ ወር በኋላ ፀድቆ ወደ ሥራ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች