Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች የራሳቸውንና የሠራተኞችን የሀብት ምዝገባ አጠናቀው እንዲያሳውቁ ማሳሰቢያ ተሰጠ

ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች የራሳቸውንና የሠራተኞችን የሀብት ምዝገባ አጠናቀው እንዲያሳውቁ ማሳሰቢያ ተሰጠ

ቀን:

ሁሉምመንግሥት ሠራተኞች ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ከዓመታት በፊት በፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ተግባራዊ የተደረገውን አሠራር በመቀየር፣ በቀጣይ ሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤት ኃላፊዎች በበላይነት እንዲቆጣጠሩትና እሰከ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ የራሳቸውንና የሠራተኞችን ሀብት ምዝገባ አጠናቀው ለኮሚሽኑ ሪፖርት እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጠ፡፡

ከዚህ ቀደም በመንግሥት ተቋማት የተሰየሙ የሥነ ምግባር መኮንኖች፣ በኮሚሽኑ አስተባባሪነት ሲያከናውኑት የነበረውን የሀብት ምዝገባ፣ ከቀናት በፊት በዋና ኮሚሽነሩ በተጻፈ ደብዳቤ እስከ ታችኛው የመንግሥት ዕርከን ድረስ የሚገኙ የመንግሥት ተቋማት ኃላፊዎችንና ሠራተኞችን ሀብት ምዝገባ አጠናቀው ሪፖርት እንዲያቀርቡ፣ ከየካቲት 21 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ማሳሰቢያ መሰጠቱን፣  በኮሚሽኑ የሀብት ማሳወቅና ምዘገባ ዳይሬክተር አቶ መስፍን በላይነህ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

በዋናነት 23 ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች በሥራቸው ያሉ ከፍተኛ አመራሮችንና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችን፣ንዲሁም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔንና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትን  ጨምሮ ሀብታቸውን በአዲሱ ዲጂታል ሥርዓት በማስመዝገብ፣ ለሌሎች የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች አርዓያ እንዲሆኑ ኮሚሽኑ መጠየቁን አቶ መስፍን አስረድተዋል፡፡

በተመሳሳይ ኮሚሽኑ በቅርቡ ለሕዝብ ይፋ ባደረገው ከወረቀት ነፃ የሆነ ሀብትን ለማስመዝገብ የሚያስችል የዲጂታል ምዝገባ ሥርዓት አማካይነት፣ ከዚህ ቀደም ሀብታቸውን ያስመዘገቡም ሆነ ያላስመዘገቡ በአዲሱ አሠራር እንዲያስመዘግቡ እንደሚገደዱ ተናግረዋል፡፡ በተቀመጠው መርሐ ግብር መሠረት ሀብታቸውን በማያስመዘግቡ ግለሰቦች ላይ ኮሚሽኑ በወንጀል ሕጉ መሠረት ተጠያቂ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡

አዲሱ አሠራር የመረጃ ጥራትና ተደራሽነትን የሚጨምር፣ ጊዜና ወጪ ቆጣቢ፣ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ለማስፈንና የጥቅም ግጭትን ለመከላከል የሚረዳ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

በአዋጅ ቁጥር 668/2002 መሠረት ማናቸውም ተሿሚዎች፣ ተመራጮችና የመንግሥት ሠራተኞች ሀብት እንዲያሳውቁና እንዲያስመዘግቡ፣ የሕግ ግዴታ የተጣለባቸው ሲሆን፣ ኮሚሽኑም የመዘገበውን መረጃ ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት ለሕዝብ ይፋ የማድረግ ሥልጣንና ኃላፊነትና እንደተሰጠው በግልጽ ተደንግጓል፡፡

ኮሚሽኑ በዚህ አዋጅ መሠረት ሀብታቸውን ባላስመዘገቡ በአሥር ሚኒስትር ደኤታዎችና በ174 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለሥልጣናት ላይ ምርመራ እንዲደረግባቸው፣ ለፌዴራል ፖሊስና ለፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ዝርዝር አስተላልፎ እንደነበር ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...