Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበበጎ አድራጎት ስም ገንዘብ እየሰበሰቡ ለግል ጥቅም የሚያውሉ አካላት መበራከታቸው ተገለጸ

በበጎ አድራጎት ስም ገንዘብ እየሰበሰቡ ለግል ጥቅም የሚያውሉ አካላት መበራከታቸው ተገለጸ

ቀን:

በመንግሥት አካላትና በተወሰኑ ግለሰቦች ደረጃ ለበጎ አድራጎት በሚል ከሕዝቡ ገንዘብ በመሰብሰብ ለግል ጥቅም የሚያውሉ መበራከታቸውን፣ የሲቪል ማኅበረሰቦች ድርጅት ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

የባለሥልጣኑ የሕግ ክፍል ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ምስጋናው ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ባለሥልጣኑ ከቅርብ  ጊዜ ወዲህ በየአካባቢው ከሕዝብ በዓይነትና በገንዘብ  ድጋፍ በማሰባሰብ ለግል ጥቅም የሚያውሉ አሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ባለሥልጣኑ ከሕዝብ በርካታ ጥቆማዎችን እየተቀበለ ነው ብለዋል፡፡

ለአብነትም  ለአገር መከላከያ ሠራዊት፣ በጦርነት ወይም በድርቅ ለተጎዱና  ለተቸገሩ ዜጎች ዕርዳታ እናሰባስባለን  በሚል  ሰበብ ድጋፍ ካሰባሰቡ በኋላ፣  የተወሰነውን ብቻ በመስጠት ቀሪውን ለግል ጥቅማቸው የሚያውሉ እንዳሉ ባለሥልጣኑ ከሕዝብ የደረሰው ጥቆማ ያሳያል ብለዋል፡፡ እንዲሁም ሙሉ በሙሉ የሚባለውን ድጋፍ ለራሳቸው የሚጠቀሙት እንዳሉም በጥናት መረጋገጡን  አስታውቀዋል፡፡

‹‹የተወሰኑ ሰዎች ገንዘብ በድጋፍ መልክ አደረስን ብለው ሪፖርት ለማድረግ ይመጣሉ፡፡ ነገር ግን መሬት ያለው ሁኔታ ሲጣራ ተደረገ ከተባለው ድጋፍ ጋር የማይገናኝ ሁኔታ እየገጠመ ነው፤›› ሲሉም አክለዋል፡፡

በ2011 ዓ.ም. ተሻሽሎ በወጣው የሲቪል ማኅበረሰብ  ድርጅቶች  አዋጅ ቁጥር 1113/11 መሠረት  ማንኛውም የበጎ  አድራጎት  ኮሚቴ  በባለሥልጣኑ  ሳይፀድቅ፣  ገንዘብም  ሆነ  ንብረት  ማሰባሰብ  ወይም  ማናቸውም ድርጊት መፈጸም እንደማይችል ተደንግጓል፡፡

ያለ ፈቃድ የሚሰማሩ የበጎ አድራጎት ኮሚቴዎች በአዋጁ መሠረት የተከለከሉ ቢሆንም፣ የሕዝቡን  የመረዳዳት ባህልና የበጎ አድራጊነት ትውፊት ለመጠበቅ ሲባልና በሕጉ ላይ በቂ ግንዛቤ እስኪፈጠር በሚል፣ እስካሁን  ጠንካራ ወደ ሆነ የቁጥጥር ሥርዓት አለመገባቱን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ ባለሥልጣኑ  ከየካቲት 3 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ለበጎ አድራጎት ዓላማ  ለመሰማራት ከስድስት ወራት እስከ አንድ ዓመት የሚያገለግል የባለሥልጣኑን የፈቃድ ደብዳቤ ሳይዙ  ሲንቀሳቀሱ በሚገኙ አካላት ላይ፣ አስተዳደራዊና ሕጋዊ ዕርምጃ እንደሚወስድ ባለሥልጣኑ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡

ለበጎ አድራት ሥራ በሚል በባንክ አካውንት፣ በድረ ገጽ፣ በመንገድ ላይ በመኪና እንዲሁም በሌሎች መንገዶች  ገንዘብ የማሰባሰብ እንቅስቃሴ መኖሩን የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ ባለሥልጣኑ በሕዝብ ስም የሚሰበሰብ ገንዘብ ያለአግባብ እንዳይባክን የመጠበቅና የመከላከል ግዴታ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

ስለዚህም የግለሰቦች ገንዘብ ያላግባብ ተሰብስቦ ለግል ጥቅም እየዋለ በመሆኑ፣ ባለሥልጣኑ ከዚህ በኋላ ያለ ፈቃድ ሲንቀሳቀስ በተገኘ አካል ላይ አስተዳደራዊ ዕርምጃ እንደሚወስድ፣ ወይም በወንጀል ጉዳይ ተጠያቂ እንዲሆን ወደ ዓቃቤ ሕግና ፖሊስ እንደሚመራ አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...