Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበጦርነቱ በቴክኒክና የሙያ ተቋማት ላይ ከአሥር ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት መውደሙ...

በጦርነቱ በቴክኒክና የሙያ ተቋማት ላይ ከአሥር ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት መውደሙ ተገለጸ

ቀን:

የሕወሓት ታጣቂዎች በአማራና በአፋር ክልሎች ገብተው በቆዩባቸው ጊዜያት፣ በቴክኒክና በሙያ ተቋማት ላይ ከአሥር ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት መውደሙንና መዘረፉን፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

በተጠቀሱት አካባቢዎች በጦርነቱ የደረሰውን ጉዳት ስድስት አባላት ያሉት የሙያተኞች ቡድን በማቋቋም ዝርዝር ጥናት መካሄዱን የጠቀሱት ሚኒስትሯ፣ በዚህ ጥናት መሠረት ከፍተኛ ውድመትና ዝርፊያ ከደረሰባቸው ተቋማት ውስጥ የቴክኒክና የሙያ ዘርፍ አንዱ እንደሆነ አአስታውቀዋል፡፡

የቴክኒክና የሙያ ተቋማት በውስጣቸው የሚገኙ መሣሪያዎች ግዙፍና  በቀላሉ የማይገኙ በመሆናቸው፣ በሙያተኛ የታገዘ ዘረፋ እንደተካሄደባቸው ሚኒስትሯ አስረድተዋል፡፡

የሙያ ተቋማቱ እጅግ በጣም ከባድና መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን፣  አሁን ባሉበት ደረጃ አገልግሎት መስጠት የሚችሉና የማይችሉ ተብለው ተለይተው በጉዳታቸው ልክ ዕገዛ እንደሚደረግላቸው አክለው ገልጸዋል፡፡

በደሴ፣ በኮምቦልቻ በወልዲያና መሰል ትልልቅ የቴክኒክና የሙያ ተቋማት ውስጥ የነበሩ ማሽነሪዎችን ለመግዛት ገንዘብ ቢገኝ እንኳን፣ ማሽነሪዎቹን በአጭር ጊዜ ውስጥ ገዝቶ ወደ አገር ለማስገባት ከባድ ነው ብለዋል፡፡ ይሁን እንጂ ሠልጣኞች ከትምህርት ውጪ ሆነው በቆዩ ቁጥር ላላስፈላጊ የጤና ችግር እንዳይዳረጉ፣ በአስቸኳይ ሥልጠና እንዲጀምሩ እየተሠራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2014 ዓ.ም. ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸሙን ሰኞ ጥር 30 ቀን 2014 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቅርቦ ነበር፡፡

በስድስት ወራት ውስጥ በክልሎች ለ1.5 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታሰቦ፣ ለ1.1 ሚሊዮን ዜጎች መፍጠር መቻሉን ሚንስትሯ ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጂ አብዛኛው የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው ዜጎች 70 በመቶ የሚሆኑት በቅጥር ወይም በመንግሥት ተቋማት፣ በግዙፍ ፕሮጀክቶች፣ በኢንቨስትመንትና በአገልግሎት ዘርፍ መሰማራታቸው ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል በስድስት ወራት ውስጥ ከ10.9 ቢሊዮን ብር በላይ የብድር ድጋፍ  ለ128  ሺሕ አነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ለመስጠት ታቅዶ፣ 15 ሺሕ አካባቢ ወይም የዕቅዱን 12 በመቶ ብድር ማግኘታቸውን፣ ከታሰበው አጠቃላይ ገንዘብ 4.2 ቢሊዮን ብር ብቻ ማሠራጨት እንደተቻለ ተገልጿል፡፡

ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ከ31 ሺሕ በላይ ዜጎች ወደ ተለያዩ አገሮች በተለይም ወደ መካከለኛው ምሥራቅ በቤት ሠራተኝነት ሠልጥነው እንደተላኩ፣ በመጪዎቹ ወራት ወደ አውሮፓና እስያ አኅጉራት ተመሳሳይ ሠራተኞች ሠልጥነው ለሥራ እንደሚላኩ ወ/ሮ ሙፈሪያት ተናግረዋል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...