Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናማዕድናት በሚመረቱባቸው ቦታዎች የሚስተዋል የፀጥታ ችግር ኩባንያዎች ለቀው እንዲወጡ እያደረገ መሆኑ ተገለጸ

ማዕድናት በሚመረቱባቸው ቦታዎች የሚስተዋል የፀጥታ ችግር ኩባንያዎች ለቀው እንዲወጡ እያደረገ መሆኑ ተገለጸ

ቀን:

በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ ማዕድናት ማምረቻ አካባቢዎች የሚታዩ የፀጥታ ችግሮች፣ አምራች ኩባንያዎቸን ለቀው እንዲወጡ እያደረጉ መሆናቸውን፣ አዳዲሶቹንም እንዳይገቡ  እንቅፋት እንደሆኑ የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ለአብነትም ባለፉት ስድስት ወራት ወደ ሥራ የገቡ አዳዲስ ኩባንያዎች የለም ያለው ሚኒስቴሩ፣ በቤንሻንጉል ጉምዝ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ ምዕራብና  በጋምቤላ ክልሎች አምራች ኩባንያዎች ተረጋግተው እንዳያመርቱ  የፀጥታ ችግሮች እንቅፋት እንደፈጠሩበት ገልጿል፡፡ 2014 በጀት ዓመት የመጀመርያ ስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማዕድንና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጥር 27 ቀን 2014 .ም.  ባቀረበበት ወቅት ነው ሚኒስቴሩ ይህንን ያስታወቀው፡፡

በስድስት ወራት ውስጥ አጠቃላይ 446 ኪሎ ግራም ወርቅ 282 ሚሊዮን ዶላር፣ ከጌጣጌጥና ከኢንዱስትሪ ማዕድናት 900,000 ዶላር ቢያገኝም፣ 2,220 ኪሎ ግራም ዕምነበረድ ለማግኘት አቅዶ በፀጥታ ምክንያት ምንም ዓይነት ምርት ማግኘት እንዳልተቻለ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

በሰሜን የአገሪቱ ክፍል በተካሄደው ጦርነትና በየጊዜው ከሚታዩ የፀጥታ ችግሮች በተጨማሪ በአንዳንድ አካባቢዎች የተደራጀ የሽፍታ እንቅስቃሴዎች በመኖራቸው፣ የማምረት ሒደቱን እንዳስተጓጎለበት ሪፖርቱን ያቀረቡት የሚኒስቴሩ የዕቅድ ዝግጅት ባለሙያ አቶ አብርሃም ሥዩም አስረድተዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የፀጥታ ችግሩን ለመፍታት 14 የተለያዩ የማዕድን ማውጫ ቦታዎች ከመከላከያ ሚኒስቴር፣ ከፌደራል ፖሊስ፣ ከብሔራዊ ደኅንነት መረብ ኤጄንሲናአርቲፊሻል ኢንቴሌጀንስ ጋር በመተባበር  የመግባቢያ ስምምነት ተካሂዶ የማዕድን ፖሊስ ለማቋቋም ስምምነት ላይ ተደርሶ ወደ ሥራ እንደተገባ አቶ አብርሃም ተናግረዋል፡፡

ለዚህም ለአገልግሎት 20 ፓትሮል መኪኖች ተገዝተው ለክልሎች መሰጠታቸውንና  በማዕድን ማውጫዎች የሚገኙ ኩባንያዎችና የማዕድናት ዓይነት መረጃ ለፀጥታ አካላት እንደተሰጠ፣ የፀጥታ ችግር ያለባቸው ቦታዎች ልየታ ተደርጎ በኦሮሚያ፣ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ፣ደቡብ ምዕራብ አካባቢዎች የፀጥታ ኃይሎች ፀጥታ ለማስፈን በመሰማራታቸው ባህላዊ አምራቾችን በከፊል ወደ ሥራ መመለስ  እንደተቻለ በሪፖርቱ ተጠቁሟል፡፡

ሚኒስትሩ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) የፀጥታ ጉዳይ በጣም ከፍተኛ ችግር እንደሆነ በመግለጽ፣ በእያንዳንዱ ትንንሽ ወረዳ በማዕድን ዘርፍ ላይ ያለው የፀጥታ ችግር ካልተፈታ የሲሚንቶና የብረት ፋብሪካዎች ችግር ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ ብለዋል፡፡ የወርቅ ምርትም አሁን እየተመረተ ካለው መጠን ሊወርድ እንደሚችል ጠቁመው፣ ‹‹ፓርላማው ዕገዛ ያድርግልን፤›› ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...