Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየመንግሥት ተቋማት ለሕዝብ የሚያቀርቡት መረጃ ትክክለኛነት የሚረጋገጥበት አስገዳጅ ሥርዓት እንዲዘረጋ ተጠየቀ

የመንግሥት ተቋማት ለሕዝብ የሚያቀርቡት መረጃ ትክክለኛነት የሚረጋገጥበት አስገዳጅ ሥርዓት እንዲዘረጋ ተጠየቀ

ቀን:

በርካታ የመንግሥት ቋማት ለፓርላማው የሚያቀርቡትአፈጻጸም ሪፖርትም ሆነ በሌላ በኩል ለሕዝብ የሚያደርሱት መረጃ ከአዘገጃጀቱ እስከ አቀራረቡ ድረስ የተዓማኒነት ችግር ያለበት በመሆኑ፣ መረጃው ደረጃውን የጠበቀ መሆኑንና ትክክለኛነቱን አስገዳጅ ሥርዓት እንዲዘረጋ ተጠየቀ፡፡

አገራዊ የልማት ዕቅዶችን፣ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን ለማዘጋጀት፣ ለመከታተልና ለመገምገም የሚረዱ አስተማማኝና ደረጃቸውን የጠበቁ ወቅታዊ መረጃዎችን በአገር አቀፍ ደረጃ መረጃ አመንጪ ከሆኑ ተቋማት በመሰብሰብ፣ መረጃዎችን፣ የማጥራት ሥራ ለብሔራዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ኃላፊነት ቢሰጠውም፣ አስገዳጅ የሆነ ሥርዓት ባለመዘርጋቱ የተቋማትን መረጃ ትክክለኛነት ለማረጋገጥ እንዳልቻለ ተገልጿል፡፡

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራቱ ይገዙ በተቋማት የሚታየው አጠቃላይ የመረጃ አዘገጃጀትና ጥራት ችግር ያለበት ከመሆኑም በላይ፣ እነዚህ ተቋማት ወደ ኤጀንሲው የሚያመጡት መረጃ ጥራቱና ደረጃው ታይቶና ተገምግሞ በድጋሚ አስተካክለው እንዲመጡ ተነግሯቸው ከሄዱ በኋላ፣ ተመሳሳይ የሆነ ችግር ያለበት መረጃ ይዘው እንደሚመጡ ተናግረዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ እንዳብራሩት፣ ኤጀንሲው መረጃን የማጣራትና የማደራጀት ኃላፊነት ቢሰጠውም፣ ተቋማትን የሚያስገድድበት ሥርዓት ባለመኖሩ ‹‹ለሥራችን ትልቅ ችግር ፈጥሮብናል፣ በመሆኑም ቋሚ ከሚቴው ያግዘን፤›› ብለዋል፡፡

በዚህም የተነሳ የመንግሥት ተቋማት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባም ሆነ በቋሚ ኮሚቴ እንዲገመገም የሚያቀርቡት ሪፖርት ትክክለኛነት ሳይረጋገጥ አቅርበው ከመሄድ ውጪ፣ መረጃውን ከየት አመጣህ ብሎ የሚጠይቅ አካል አለመኖሩን አብራርተዋል፡፡

‹‹ሁሉም ተቋም አፈጻጸሜ ነው ብሎ አቅርቦ ይሄዳልነገር ግን የሚረጋገጥበት (Autenticate) አሠራር የለም፤›› ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ በመረጃ ሰጪውና ተቀባዩ መካከል ባለው ግንኙነት አንድ ተቋም የተሳሳተ መረጃ ሲያቀርብ፣ ወዲያውኑ ተጠያቂ የሚያደርግ ሥርዓት መዘርጋት እንደሚያስፈልግ አክለው ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ተቋማት ስለሚሠሩት ሥራ መረጃ ለመስጠት ፍላጎት ስለሌላቸው፣ ከደረጃ በታች የሆነ መረጃ የመላክ አባዜ የተጠናወታቸውን አካላት ከዘመኑ ጋር የሚሄድ መረጃ ለማግኘት የሚረዳ አሠራር እንዲዘረጉ ጠንካራ የሆነ ሕግና ሥርዓት እንዲዘጋጅ ጠይቀዋል፡፡

አቶ ቢራቱ ይህን የተናገሩት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰኞ ጥር 23 ቀን 2014 .ም.፣ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት፣ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ የዘላቂ ልማት ግቦች መረጃዎችን ለማደራጀት ያደረገውን ዝግጅት አፈጻጸም ክዋኔ ኦዲት ላይ ውይይት ባደረገበት ወቅት ነው፡፡

በመረጃ አሰጣጥ በአገር ደረጃ እየታየ ያለው ችግር አስገዳጅ በሆነ ሕግ ካልታሰረ በስተቀር፣ ኤጀንሲው የትኛውንም ተቋምአገራዊ ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ግምገማ ለማድረግ መረጃ ሲጠይቅ መረጃ አያገኝም፣ ወይም በሚፈለገው ደረጃና ጥራት እየቀረበለት እንዳልሆነ ዋና ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡

በሌላ በኩል በአገር አቀፍ ደረጃ ለመረጃ አያያዝና አስፈላጊነት ያለው ግንዛቤ በጣም ዝቅተኛ ስለመሆኑ፣ ለአብነትም በየደረጃው የሚገኙ የመንግሥት ሥራ አስፈጻሚ አካላት ዛሬ የሰጡትን መረጃ ነገ ሲመጡ አሳንሰውት ወይም ጨምረውበት፣ ወጥነትናዓማኒነት በሌለው መንገድ እንደሚያቀርቡ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ደኤታ / ጥሩማር አባተ ተናግረዋል፡፡

ለአብነትም በአሁኑ ጊዜ ሚኒስቴሩ የስድስት ወራት የተቋማት ሪፖርት እየገመገመ እንደሆነ፣ በዚህ ግምገማ ላይ የተወሰኑ ተቋማት ሪፖርት ሲላክና ተከፍቶ ሲታይ ሦስትና አራት ዓይነት ሆኖ እንደሚመጣ / ጥሩማር ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ መረጃው ለፖሊሲ አውጭዎች ወይምውሳኔ ሰጭ አካላት እንደ ግብዓት መነሻ ሆኖ እንዲያገለግል በሚፈለግበት ጊዜ፣ ለማምጣት ፈቃደኛ የማይሆኑ አንዳንድ ተቋማት መኖራቸውን ጠቅሰው ምክር ቤቱ ጠንካራ ክትትል እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

የፌዴራል ምክትል ዋና ኦዲተር / መሠረት ዳምጤ በበኩላቸው የኤጀንሲውን የኦዲት ሪፖርት አስመልክተው በሰጡት አስተያየት፣ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ በኢትዮጵያ ተቀባይነት ያላቸውና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ..አ. 2016 እስከ 2030 ድረስ ድህነትን ጨርሶ ማጥፋትንና የአየር ንብረት ለውጥን መታገል የሚሉ ዕቅዶች የተካተቱበት የዘላቂ ልማት ግብ አፈጻጸም ላይ፣ ወጥ የሆነ አመላካች አስተዳደራዊ መረጃ አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡

ወጥ የሆነ ሥርዓት ባለመዘርጋቱ ምክንያት አገሪቱ ተስማምታ ቃል የገባችባቸውን ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን ለመገምገም ከባድ ከመሆኑም በላይ፣ በ2030 አስመዘግበዋለሁ ብላ ያሰበችው ዕቅድ ላይ ለመድረስ አስቸጋሪ እንደሚሆንባት አስረድተዋል፡፡

የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ዳይሬክተር አቶ መስፍን በላይነህ፣ በአገር ደረጃ ከዘላቂ ልማት ግቦች ጋር በተገናኘም ሆነ ከሌሎች አገራዊ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ ደረጃውን የጠበቀና ጊዜውን ማዕከል ያደረገ መረጃ ሊያግባባ በሚችል መንገድ መቅረብ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

በተጨማሪም ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ የሚያዘጋጃቸው መረጃዎች የአገሪቱ መሪ ዕቅዶች መነሻ በመሆናቸው፣ መረጃው ሲጠናቀር በኃለፊነት አገርን በማስቀደም መሆን እንዳለበት በመጥቀስ ተቋሙ በተቋቋመበት ዓላማ መሠረት ደረጃውን ጠብቆ ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...