Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ደንብ ባለመውጣቱ ምክንያት ከቅርሶች ገቢ መሰብሰብ አልቻልኩም አለ

የቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ደንብ ባለመውጣቱ ምክንያት ከቅርሶች ገቢ መሰብሰብ አልቻልኩም አለ

ቀን:

የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን፣ በመጀመርያ በ1960 ዓ.ም. እንዲሁም በ2006 ዓ.ም. ተሻሽሎ ቅርሶችን በብሔራዊና በክልል ቅርስነት ለመመደብ የወጣው አዋጅ፣  ከተለያዩ የቅርስ አገልግሎቶቸ መሰብሰብ የሚያስችለውን ገቢ እንዳያገኝ እንቅፋት እንደሆነበት አስታወቀ፡፡

ከአዋጁ በኋላ ደንብ መውጣት የነበረበት ቢሆንም ባለመውጣቱ ምክንያት ባለሥልጣኑ በገንዘብ ሚኒስቴር መመርያ መሠረት አንድ አገልግሎት ሰጪ ተቋም ከ50 ብር በላይ ማስከፍል የማይችል በመሆኑ፣ ከበርካታ አገልግሎቶቹ ገቢ መሰብሰብ እንዳልቻለ የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አበባው አያሌው (ረዳት ፕሮፌሰር) ገልጸዋል፡፡ 

ለአብነትም በሥራ ላይ ያለው የውጭ አገር ጎብኝዎች የሙዚየም መግቢያ ዋጋ 50 ብር መሆኑን፣ ክፍያው አሁን ካለው ወቅታዊ ዋጋ ጋር ሲታይ እዚህ ግባ የማይባል እንደሆነና ይህንን ዋጋ ለማሳደግ አለመቻሉን፣ እንዲሁም የስጦታ ዕቃዎች መሸጫ ቤቶች ለመክፈት አሁን በሥራ ላይ ያለው ሕግ ይገድባል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም በሥራ ላይ ያለው አዋጅ ወጥ የሆነ የቅርሰ አስተዳደር ሥርዓት ባለመዘርጋቱ፣ በፌዴራልና በክልል መንግሥታት ኃላፊነት ሥር የሚወድቁ ቅርሶችን የመጠገን፣ የመንከባከብ፣ የመመዝገብና የማልማት ኃላፊነትን ለይቶ መውሰድ እንደማይቻል ተናግረዋል፡፡

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ይህን ያሉት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የባለሥልጣኑን የተቋሙ የ2012 በጀት ዓመት የሒሳብ ኦዲት ሪፖርት በገመገመበት ወቅት ነበር፡፡

በመሆኑም ባለሥልጣኑ ደንብና መመርያ ማውጣት ስለማይችል ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የክፍያ ጣሪያ ማሻሻያ አድርጎ እንዲፀድቅለት ማቅረቡን በመጥቀስ፣ ፓርላማው ዕገዛ እንዲደርግለት አቶ አበባው ጠይቀዋል፡፡

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ መኖሪያ ቤት ምንም እንኳ ዕድሳት የተደረገለት ቢሆንም፣ ሙዚየም አድርጎ ለመክፈት መከናወን ያለባቸው ቅድመ ሥራዎች ባለመከናወናቸው፣ እንዲሁም ሙዚየም ሆኖ ከተከፈተ በኋላ ቤቱም ሆነ አካባቢው በጣም ጠባብ በመሆኑ፣ ለተሸከርካሪ ማቆሚያ ቦታ ስለሌለው ተጨማሪ ቦታ እንዲሰጣቸው ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

በሌላ ዜና በሰሜን የአገሪቱ ክፍል ሲካሄድ በነበረው ጦርነት የሕወሓት ታጣቂዎች በአማራና በአፋር ክልሎች በፈጸሙት ወረራ፣ በርካታ ቅርሶች መዘረፋቸውንና መውደማቸውን የጠቀሱት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፣ የደረሰውን ጉዳት የሚያጣራ ቡድን ተልኮ የመጀመርያ ጥናቱን ይዞ መመለሱን ተናግረዋል፡፡

ወደ ሰሜን ሸዋና ደቡብ ወሎ የተላከው አጥኝ ቡድን ተመልሶ የመጣ መሆኑን፣ ሪፖርቱ በቅርቡ ከቀረበ በኋላ የተጎዱና የተዘረፉ ቅርሶች በሚመለሱበት ሁኔታ ላይ ከጉምሩክ ኮሚሽንና ከፖሊስ ጋር ሥራዎች ይከናወናሉ ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...