Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየህዳሴ ግድብ ኃይል ለማመንጨት ሲቃረብ የግብፅና የሱዳን ተቃውሞ ጊዜ ያለፈበት መሆኑን የውጭ...

የህዳሴ ግድብ ኃይል ለማመንጨት ሲቃረብ የግብፅና የሱዳን ተቃውሞ ጊዜ ያለፈበት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

ቀን:

ግንባታው ከተጀመረ አሥር ዓመታት ያስቆጠረው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ የመጀመርያዎቹ ሁለት ተርባይኖች ማመንጨት ሊጀምሩ በተቃረቡበት ወቅት፣ ከግብፅና ከሱዳን የሚሰማ ማንኛውም ዓይነት ፉከራና ድንፋታ ጊዜ ያለፈበት ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ኤሌክተሪክ ማመንጨት የሚጀምርበትን ቀን ይህ ነው ብሎ መነገር ባይቻልም፣ በጣም በቅርብ ጊዜ እንደሚጀምር ለጋዜጠኞች የገለጹት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ (አምባሳደር)፣ የግድቡ ጉዳይ ሊለወጥ የማይችልና ያለቀ ነገር በመሆኑ፣ የታችኛው ተፋሰስ አገሮች ከዚህ ካለቀ ጉዳይ ጋር አብረው መቆም አለባቸው ብለዋል፡፡

በ42ኛው የዓረብ ባህረ ሰላጤ አገሮች የትብብር ምክር ቤት አባላት በኅዳር 2014 ዓ.ም. በሳዑዲ ዓረቢያ ባደረጉት ስብሰባ መጨረሻ ላይ ባወጡት የአቋም መግለጫ፣ የሱዳንና የግብፅ የውኃ ደኅንነት የዓረብ አገሮች የደኅንነት ጉዳይ ስለሆነ አስገዳጅ የሆነ ሕጋዊ ስምምነት እንደሚስፈልግ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

በተመሳሳይ የግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ በግብፅ ሻርማልሼክ እ.ኤ.አ. ከጃንዋሪ 2 እስከ 5 ቀን  2022 በተካሄደ ዓመታዊ የዓለም የወጣቶች ፎረም፣ ኢትዮጵያ በግድቡ ላይ በምታካሂደው የውኃ አሞላልና የማመንጨት ሒደት  ሕጋዊ የሆነ ስምምነት እንፈልጋን የሚል ንግግር አድርገው ነበር፡፡

ዲና (አምባሳደር) ሐሙስ ጥር 5 ቀን 2014 ዓ.ም. በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ፣ ከዚህ በኋላ ግድቡ ሲያመነጭ ለግብፆችም ሆነ ለሱዳኖች ጠቃሚ ከመሆኑም በላይ፣ በሚመነጨው ኃይል ሌሎችም አገሮች ተጠቃሚ እንዲሆኑ እነዚህ አገሮች ቢሠሩ መልካም እንደሆነና ነገር ግን የሦስትዮሽ ድርድሩ ይቁም ማለት አይደለም ብለዋል፡፡

‹‹ሱዳንና ግብፅ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ከጀመራቸሁ ችግር ይፈጠራል፣ ሰማዩ ይገለባበጣል የሚሉት ነገር አዲስ አይደለም፡፡ ቀድሞውንም ሙሌት ከጀመራችሁ  አደጋ ይፈጠራል፣ ጉድ ይፈላል፤›› ሲሉ እንደነበር በመግለጽ፣ ይህ ፉከራ የተለመደ ቢሆንም አሁን ግን ያረጀና ጊዜው ያለፈበት ሆኗል ብለዋል፡፡

በህዳሴ ግድቡ ውኃው ተርባይኑን አንቀሳቅሶ አልፎ ስለሚሄድ መጠኑ ስለማይቀንስ፣ ሱዳኖች የግድቡ ኃይል ማመንጨት መጀመር ሊያስደስታቸውና ሊያከብሩት ይገባል ብለው፣ ‹‹ወታደራዊ ኃይሉም ዝም ብሎ አብዶ ነው እንጂ  ብዙ ነገር ሊሠሩበት ይችላሉ፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

በሰኔ 2013 ዓ.ም. ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌቱን ባጠናቀቀው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣ ሁለት እያንዳንዳቸው 375 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ያላቸው ተርባይኖች ተከላ  በመከናወኑ፣ የኃይል ማመንጨት ሥራውን በቅርቡ እንደሚጀመር ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...