Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናከሸዋሮቢት ወደ ዝዋይ ተወስደው የነበሩ ከሁለት ሺሕ በላይ ታራሚዎች በቅረቡ ወደ ነበሩበት...

ከሸዋሮቢት ወደ ዝዋይ ተወስደው የነበሩ ከሁለት ሺሕ በላይ ታራሚዎች በቅረቡ ወደ ነበሩበት ይመለሳሉ ተባለ

ቀን:

  • በማረሚያ ቤቱ ከ48 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት መውደሙ ተገለጸ

በሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋሮቢት ከተማ በሚገኘው የሸዋሮበት የፌደራል ማረሚያ ቤት በሕወሓት ወራረ ምክንያት ጥቃት እንዳይደርስባቸው ወደ ዝዋይ ተወስደው የነበሩ 2,100 ታራሚዎች፣ በቅርቡ ሙሉ ለሙሉ ወደ ነበሩበት እንደሚመለሱ ተገለጸ፡፡

በጦርነቱ ምክንያት በማረሚያ ቤቱ ከነበሩ ታራሚዎች መሀል የጠፋና  ያመለጠ እሰረኛ እንደሌለ ለሪፖርተር የገለጹት የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገረመው አያሌው፣ በተቋሙ ወድሞና ተዘርፎ የነበረው አብዛኛው ሥራ ተጠናቆ ታራሚዎችን የመመለስ ሥራ ተጀምራል ብለዋል፡፡

የሕወሓት ታጣቂዎች ሸዋሮቢት ከተማን ከመቆጣጠራቸው ከሁለት ቀናት በፊት ኮሚሽኑ ታራሚዎች በማረሚያ ቤቱ ቢቆዩ ሊደርስ የሚችለውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ እስረኞች ቀድመው እንዲወጡ መደረጉን አስረድተዋል፡፡

ይሁን እንጂ ታጣቂዎቹ የሸዋሮቢትን ከተማ ለአሥር ቀናት ያህል በተቆጣጠሩበት ጊዜ፣ በማረሚያ ቤቱ ላይ ከፍተኛ የሆነ ውድመትን ማድረሳቸውን አቶ ገረመው አክለው ገልጸዋል፡፡

በተለይም የሕግ ታራሚዎችን ለማረምና ለማነፅ አግልግሎት ይሰጡ የነበሩ የማሠልጠኛ ቁሳቁሶች መውደማቸውን የተናገሩት ኃላፊው፣ የመዝናኛ ክበባትን፣ የእንስሳት ተዋጽኦ ማቀነባበሪያ ማሽኖችን፣ የሕግ ታራሚዎችን ምግብና አልባሳት፣ የሕክምና መስጫ ክሊኒክ፣ ታራሚዎች የፍርድ ሒደታቸውን ባሉበት ቦታ ሆነው የሚከታተሉበትን ፕላዝማ፣ ቢሮዎችና የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶች፣ የአባላትና የታራሚ መኖሪያ ቤቶች መዘረፋቸውንና መውደማቸውን ገልጸዋል፡፡

በማነፅና ተሃድሶ ልማት፣ በጥበቃና ደኅንነት፣ በመሠረታዊ ፍላጎትና በሰው ሀብትና ፋይናንስ ዘርፍ ሥር የወደሙና የተዘረፉ ንብረቶች ግምት ከ48 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

የአገር መከላከያ ሠራዊትና ሌሎች ጥምር የፀጥታ አካላት በወሰዱት የማጥቃት ዘመቻ፣ ቡድኑ አካባቢውን ለቆ እንደወጣ የማረሚያ ቤት ፖሊስ አባላትና የደረሰውን ውድመት የሚያጣራ ኮሚቴ ተደራጅቶ መግባታቸውን፣ የተዘረፉ ንብረቶችም እየተመለሱ መሆናቸውን አቶ ገረመው ገልጸዋል፡፡

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...