Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜና‹‹በተጠናቀቀው 2021 የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ለስውር ጫና ተጋልጦ ነበር›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

‹‹በተጠናቀቀው 2021 የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ለስውር ጫና ተጋልጦ ነበር›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ቀን:

ከጥቂት ቀናት በፊት የተጠናቀቀው የአውሮፓውያኑ ዓመት 2021 በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ እንቅስቃሴ ላይ በጭንብልና በሽፋን የተቀነባበሩ ግፊቶች የበዙበት እንደነበር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ (አምባሳደር) ገለጹ፡፡

ቃል አቀባዩ ሐሙስ ታኅሳስ 28 ቀን 2014 ዓ.ም. ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የተገባደደው የአውሮፓውያኑ ዓመት በዲፕሎማሲው መስክ ትልቅ ጫና የነበረበት ነገር ግን ኢትዮጵያ ያሸነፈችበት ዓመት ነበር ብለዋል፡፡

ለአብነትም የህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድርን በአፍሪካውያን እንዳይፈታ አጀንዳውን በመጥለፍ በኢትዮጵያ ላይ ተፅዕኖና ግፊት መደረጉን፣ የሰሜን ኢትዮጵያ የሕግ ማስከበር ዘመቻን እንደ ጭምብል በመጠቀም በሰብዓዊ መብት ጥሰትና በሰብዓዊ ዕርዳታ ተደራሽነት ስም በኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ሥራ ላይ ከፍተኛ ጫና የተደረገበት ዓመት እንደነበር ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል የሱዳን ወታደራዊ አገዛዝ የኢትዮጵያን ድንበር አልፎ በመያዙ ምክንያት ምዕራባውያኑ የተፈጠረውን ሁኔታ ለተፅዕኖ ማሳደሪያ ሲጠቀሙበት መቆየቱን፣ በሰብዓዊ ጥሰት ምርመራ ረገድም ቢሆን ምንም እንኳ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ተቋማትን በማካተት ምርመራ ብታደርግም፣ አግባብ ያልሆኑ በርካታ ክሶች እንደተሰነዘሩ አስረድተዋል፡፡

‹‹ኢትዮጵያ አሸንፋለች ሲባል ጉራ አይደለም፤›› ያሉት ቃል አቀባዩ፣ ከነበሩት ዘመቻዎች መካካል የህዳሴ ግድብ ድርድርን ከአፍሪካ ማዕቀፍ ወስደው በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የደኅንነት ሥጋት ተብሎ እንዲታይ የቀረበውን ጉዳይ፣ ኢትዮጵያ አሽንፋ ወደ አፍሪካ ኅብረት መመለስ መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡  

እንዲሁም ምዕራባውያኑ የሰሜን ኢትዮጵያን ጉዳይ አንዴ ወደ አውሮፓ ኅብረት፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ወደ ተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መድረክ ለመውሰድ ያደረጉት ጥረትና በሱዳንና በኢትዮጵያ ድንበር በሱዳን ወታደራዊ አገዛዝ አማካይነት የአካባቢ ጦርነት ለመክፈት የነበራቸው ዕቅድ ከሽፏል ብለዋል፡፡

አሁን የተጀመረው 2022 የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ አጀንዳ ሉዓላዊነትና ነፃነት ማስጠበቅና ማስከበር ላይ ያተኮረ ይሆናል ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...