Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበአማራ ክልል በጦርነቱ ምክንያት ከተፈናቀሉ ዜጎች ውስጥ 1.2 ሚሊዮን ያህሉ ወደ ቀዬአቸው...

በአማራ ክልል በጦርነቱ ምክንያት ከተፈናቀሉ ዜጎች ውስጥ 1.2 ሚሊዮን ያህሉ ወደ ቀዬአቸው መመለሳቸው ተነገረ

ቀን:

በአፋርና በአማራ ክልሎች 12.7 ሚሊዮን ዜጎች የዕለት ደራሽ ምግብ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል

ከሐምሌ 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በበርካታ የአማራ ክልል አካባቢዎች ሕወሓት ባደረገው ወራራ ምክንያት ከመኖሪያ ቀዬአቸው ከተፈናቀሉት ዜጎች ውስጥ፣ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑት ወደ  ቀደመ  መኖሪያቸው መመለሳቸቸው ተገለጸ፡፡

የፌደራል መንግሥት በትግራይ ክልል ሲያደርግ የነበረውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ የተናጠል ተኩስ በማድረግ፣ ከክልሉ በወጣ በጥቂት ቀናት ውስጥ፣ በአማራ ክልል ወረራ ያካሄዱት የሕወሓት ታጣቂዎች፣ በሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች፣ በዋግ ህምራ ዞን፣ በሰሜንና በደቡብ ጎንደር ዞኖች፣ በኦሮሚያ ልዩ ዞንና በከፊል የሰሜን ሸዋ ዞን ከ1.4 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተፈናቅለው እንደነበር የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽነር አቶ ዘለዓለም ልጃለም ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ሕወሓት በሰሜን ጎንደር አልፎ አልፎ በሚያደርገው ትንኮሳ ምክንያት በቅርቡ እንደሚመለሱ ከሚጠበቁትና በደባርቅ መጠለያ ውስጥ ከሚገኙት 200 ሺሕ ተፈናቃዮች ውጪ፣ በሌሎች አካባቢዎች በመጠለያ የነበሩት ተፈናቃዮች ሙሉ በሙሉ መመለሳቸውን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡

ወደ ቀዬአቸው ከተመለሱት ውስጥ 460 ሺሕ የሚደርሱትን የክልሉ መንግሥት በራሱ የትራንስፖርት ወጪ ቀሪዎቹን ደግሞ በባለሀብቶች፣ በዞንና በወረዳ አስተዳዳሮች ጥረት፣ እንዲሁም ተፈናቃዮች በራሳቸው ወጪ ወደ ቀዬአቸው እንደተመለሱ አክለው ተናግረዋል፡፡

በጦርነቱ ከተፈናቀሉት በተጨማሪ በአማራ ክልል ቀደም ሲል ከወራት በፊት በአጣዬ ከተማ በተቀሰቀሰ ግጭት የተፈናቀሉ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የቤንሻንጉል ነፃ አውጪ ነኝ እያለ በሚንቀሳቀሰው ኃይል የተፈናቀሉ፣ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል በኦነግ ሸኔ ጥቃት ደርሶባቻው ተፈናቅለው በአማራ ክልል በመጠለያ የሚገኙ ዜጎች ቁጥር 900 ሺሕ መድረሱን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡

በሕወሓት ወረራ ምክንያት ተፈናቅለው ወደ ቀዬአቸው የተመለሱትን ጨምሮ ተወረው በነበሩ አካባቢዎች በደረሰው ዝርፊያ፣ ውድመትና የኢኮኖሚ ቀውስ ሳቢያ በክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር 11.4 ሚሊዮን መድረሱን አክለዋል፡፡

ወደ ቀዬአቸው የተመለሱ ዜጎች ወደ አምራችነት እስኪገቡና መቋቋም እስኪችሉ ድረስ ለመመገብ በየወሩ 1.2 ሚሊዮን ኩንታል ምግብ የሚያስፈልግ ቢሆንም፣ አሁን መቅረብ የቻለው 426 ሺሕ ኩንታል ምግብ ብቻ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ክልሉ የመልሶ ማቋቋምና ግንባታ ሥራ በማከናወን ከሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተወጣጡ ባለሙያዎችና ጉዳት የደረሰባቸው ተቋማት መሪዎች  የተካተቱበትና ስድስት ቡድን የያዘ የአጥኚዎች ስብስብ፣ በአጠቃላይ በጦርነቱ የደረሰውን ጉዳት እያጠና መሆኑን ኮሚሽሩ ተናግረዋል፡፡ የጥናቱ ውጤት ሲደርስ ዜጎችን እንዴት ማቋቋምና አካባቢዎቹን መልሶ መገንባት እንደሚቻል ዕቅድ በማውጣት ወደ ሥራ ይገባል ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ በአፋር ክልል በሕወሓት ወረራ ምክንያት ከ423 ሺሕ በላይ ዜጎች ከመኖሪያ ቀዬአቸው ተፈናቅለው እንደሚገኙና የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀዬአቸው ለመመለስ፣ ከፌደራል መንግሥት ጋር እየተሠራ መሆኑን የአፋር ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽነር አቶ መሐመድ ሁሴን ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

የተፈናቀሉ ዜጎች ከመመለሳቸው በፊት ቀድሞ ይኖሩበት በነበረው አካባቢ የነበረው መሠረተ ልማት በታጣቂዎች በመውደሙ ምክንያት ተፈናቃዮችን ለመመለስ መሠረተ ልማቶች ቀድመው መስተካከል ስላለባቸው የጤና አገልግሎት፣ የውኃ አቅርቦትና ሌሎች ቅድሚ የሚሰጣቸው አገልገሎቶች እየተሟሉ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽነሩ በአፋር ክልል ከ1.3 ሚሊዮን ዜጎች የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ገልጸው፣ እነዚህ ዜጎች ወደ ቀዬአቸው ሲመለሱ ቢያንስ የስድስት ወራት ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ፣ ይህንን ለማሟላት ከመንግሥትና ከዕርዳታ ድርጅቶች ጋር በመነጋጋገር ለማቅረብ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...