Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበኢትዮጵያ አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰው የፀረ ተህዋስያን መድኃኒት  በጀርሞች መለመድ 

በኢትዮጵያ አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰው የፀረ ተህዋስያን መድኃኒት  በጀርሞች መለመድ 

ቀን:

የፀረ ተህዋስያን መድኃኒቶች የሰው፣ የእንስሳትና የዕፀዋት ጤና የሚያውኩትን ተህዋስያንን በመግደል ወይም መራቢያቸውን በማስቆም ከተላላፊ በሽታዎች የሚጠብቁ ብሎም የሚታደጉ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ መድኃኒቶች ጀርሞችን በመላመዳቸው ምክንያት ዓለምን አስጨንቀዋል፡፡

 ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣ በፀረ ተህዋስያን መድኃኒቶች በጀርም መለመድ ምክንያት  በዓለም በዓመት 750 ሺሕ ሰዎች ሕይወታቸውን ያጣሉ። ችግሩን መግታት ካልተቻለ ደግሞ 2050 .. 10 ሚሊዮን ሕዝብ የሞት ሰላባ ይሆናሉ።

በኢትዮጵያ የፀረ ተህዋስያን መድኃኒቶች በጀርሞች መላመድ ሳቢያ እየተፈጠሩ ያሉት ችግሮች አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸውንጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

‹‹በኢትዮጵያ በዓይን የማይታዩ ጀርሞች በተለይ የፀረ ተህዋስያን መድኃኒቶችን በመለማመድ የሚከሰተው ችግር አሳሳቢነቱ ከዓመት ዓመት እየጨመረ መጥቷል፤›› ያሉት የጤና ሚኒስትሯ  ሊያ ታደሰ (/ር) ናቸው፡፡

የዘንድሮውን የፀረ ተህዋስያን መድኃኒት በጀርሞች መለማመድን በማስመልከት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንትን ይፋ በተደረገበት መድረክ ላይ ሚኒስትሯ እንዳስገነዘቡት፣ በኢትዮጵያ መድኃኒቶችን በመለማመድ ከሚሞቱት ሰዎች መካከል በዋናነት የቲቢ፣ የኤችአይቪ፣ የልብና ሌሎችም ታማሚዎች ናቸው፡፡

የፀረ ተህዋስያን መድኃኒቶች በጀርሞች መለመድ ለሰውና ለእንስሳት፣ ለአካባቢና ለኢኮኖሚ ከፍተኛ ሥጋት እንደደቀነ ያወሱት ሚኒስትሯ፣ ጀርሞች ለፀረ ተህዋስያን ተብለው የሚሰጡ የተለያዩ መድኃኒቶችን የሚለማመዱት፣ መድኃኒቶችን በጥንቃቄ ካለመውሰድ እንደሆነ አመልክተዋል፡፡

እንደ አገር የፀረ ተህዋስያን መድኃኒቶች በጀርሞች መላመድ አሳሳቢነት እየጨመረ መጥቷል ያሉት፣ የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽነር ፍቃዱ በየነ (ፕሮፌሰር)፣ ችግሩን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ባለሥልጣኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት ይሠራል ብለዋል።

ለዓለም ከፍተኛ ሥጋት ከሆኑ ችግሮች አንዱ ነው ያሉት የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ መፍትሔ ለማምጣት መተባበር አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ሐኪሞች እንደሚያስገነዝቡት፣ በፀረ ተህዋስያን መድኃኒቶች በሽታ አምጪ ጀርሞች መላመድ ዋነኛ ምክንያቶች የፀረ ተዋህስያን መድሃኒቶችን በባለሙያ ምክር አለመጠቀም፣ የፀረ ተዋህስያን ቅሪት ያለበትን የእንስሳት ተዋፅዖ መመገብ፣ ጥራትና ጉድለት ያለባቸውና ሕገ ወጥ ፀረ ተህዋስያን መድኃኒቶችን ጥቅም ላይ ማዋል፣ የግልና የአካባቢ ንጽህና አጠባበቅ ጉድለት፣ የእንስሳት ጤና አጠባበቅ ጉድለትሲታመሙ በባለሙያ አለማስመርመር ናቸው።

ይህ ደግሞ ከእንስሳት ወደ ሰው፣ ከሰው ወደ እንስሳት የሚተላለፉ በሽታዎችን የሥርጭት መጠን ይጨምራል፡፡ የሰውንም ሆነ የእንስሳትን የሕመምና የሞት መጠንን እንዲሁም የሕክምና ወጪ እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ በመሆኑም ምርታማነትን በመቀነስ በአገር ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳርፋል።

እነዚህን በሽታ አምጪ ጀርሞች ለመከላከል በዓለምና በአገር አቀፍ ደረጃ በቅንጅት እየተሠራ ነው። የፀረ ተህዋስያን መድኃኒቶች በጀርሞች መላመድ፣ የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራን በቅንጅት ለማከናወን የሚያስችል ስትራቴጂክ ዕቅድ/ሰነድም ይፋ ሆኗል፡፡

ለዚህ ስትራቴጂክ ሰነድ መተግበሪያ የ22,794,540 ዶላር በጀት ማስፈለጉን ከሰነዱ ለመረዳት ተችሏል፡፡ እንደ ሰነዱ አቀራረብ ከዓምና ጀምሮ እስከ 2017 ዓ.ም. ድረስ የሚካሄውን የዚህን ዕቅድ አፈጻጸም የሚከታተል በፀረ ተህዋስያን አይበገሬነት ላይ አትኩሮ የሚንቀሳቀስ አማካሪ ኮሚቴ በአገር አቀፍ ደረጃ ተመሥርቷል፡፡ ኮሚቴው በሥሩ ሁሉን አቀፍ የሆነ ቴክኒካዊ ሥራ የሚያከናውኑ ስድስት የሥራ ቡድኖች እንዳሉት ለማወቅ ተችሏል፡፡

‹‹ግንዛቤን በመፍጠር የፀረ ተህዋስያን መድኃኒቶችን በጀርሞች መላመድን እንከላከል›› በሚል መሪ ቃል ከኅዳር 9 ቀን ጀምሮ ለአንድ ሳምንት የዘለቀው በተለያዩ ተቋማት (ጤና ሚኒስቴር፣ ግብርና ሚኒስቴር፣ የአካባቢና ደን ጥበቃ ኮሚሽን) ትብብር ሲሰጥ የቆየው የማስገንዘቢያ ፕሮግራም ዛሬ ኅዳር 15 ቀን ይጠናቀቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...