Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልበኢትዮጵያ በዓመቱ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ሕፃናት ከነርቭ ዘንግ ክፍተት ጋር ይወለዳሉ

በኢትዮጵያ በዓመቱ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ሕፃናት ከነርቭ ዘንግ ክፍተት ጋር ይወለዳሉ

ቀን:

የነርቭ ዘንግ ክፍተትና የጭንቅላት ውኃ መቋጠር (ስፓይና-ቢፊዳ ኤንድ ኃይድሮ ሲፋለስ) በፅንስ ላይ በቅድመ ወሊድ ወቅት ሊከሰቱ የሚችሉና ለሕይወት አስጊ የሆኑ የጤና እክሎች ናቸው፡፡ የነርቭ ዘንግ ክፍተት ተጠቂ ቢሆኑ የመንቀሳቀስ እክል፣ የስሜት ማጣት፣ የሽንትና ሰገራ የመቆጣጠር ችግሮችና ትምህርት ነገሮችን የመረዳት እክልን እንደሚያስከትል መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

የጭንቅላት ውኃ መቋጠር ብቻውን እንዲሁም የነርቭ ዘንግ ክፍተትና የጭንቅላት ውኃ መቋጠር በመጣመር ኢትዮጵያ ውስጥ የመከሰት ምጣኔውና ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት የሞት ምጣኔ ያለው አበርክቶት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል፡፡ ከእነዚህም የጤና ችግሮች ጋር የተወለዱ ሕፃናት ለተለያዩ ተጓዳኝ የጤና እክሎች እንደሚጋለጡ፣ ከእነዚህም ውስጥ የነርቭ ሥርዓት ጋር ተያይዞ የእንስቅቃሴ ውስንነት (ፓራላሲስ) የሽንትና ዓይነምድር መቆጣጠር አለመቻልና የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት እንደሚጠቀስ ነው መረጃዎች ያመላከቱት፡፡

የጤና ሚኒስቴር የክሊኒካል ሰርቪስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አባስ ሀሰን (ዶ/ር) የተጠቀሱት መረጃዎች ትክክለኛና በእውነት ላይ የተመሠረቱ መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡ እንደ ዳይሬክተሩ አነጋገር በኢትዮጵያ በየዓመቱ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ሕፃናት ከነርቭ ዘንግ ክፍተት ጋር ይወለዳሉ፡፡ ፅንስ በተከሰተ በመጀመርያዎች ሦስት ወራት ውስጥ የፎሊክ አሲድ እጥረት ያጋጥማል፡፡

እነዚህን የጤና ችግሮች ለመቅረፍ በቅድመ እርግዝናና በእርግዝና ወቅት የመከላከል ሥራዎች፣ ጊዜውን የጠበቀ የልየታ ሥራ፣ የቀዶ ሕክምና አገልግሎትን ተደራሽነት መጨመርና የዘርፈ ብዙ ክብካቤ ሥራዎችን ማከናወን ወሳኝ ድርሻ አላቸው፡፡ ነገር ግን ሥራዎቹን ለአብዛኛው የኅብረተሰብ ክፍል ለማዳረስ አዳጋች ሆኖ እንደቆየ ነው የተናገሩት፡፡

በተጨማሪም በኅብረተሰቡ ዘንድ በመከላከል ዙሪያ ያለው ግንዛቤ አናሳ መሆን፣ ከችግሮች ጋር ተያይዞ የሚመጣ መገለልና ማሸማቀቅ ተገቢውን ሕክምና በተገቢው ጊዜና ሥፍራ ለማግኘት ተጨማሪ ተግዳሮት መሆናቸውን ከዳይሬክተሩ ማብራሪያ ለመረዳት ተችሏል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ከአጋር ድርጅቶች  ጋር በመተባበር በቅድመ እርግዝናና በእርግዝና ወቅት የፎሊክ አሲድ እንክብል አቅርቦትንና ተጠቃሚነትንም ለማሻሻል በእናቶችና አፍላ ወጣቶች ፕሮግራም አማካይነት እየሠራ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም በምግብና ሥርዓተ ምግብ ስትራቴጂው ላይ እንደተቀመጠው ማኅበረሰቡ የተሰባጠረ ምግብ መመገብ እንዲያዘወትር በማኅበረሰብ ደረጃ እንዲሁም በጤና ተቋማት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ በማከናወን ላይ መሆናቸውንም ነው የገለጹት፡፡

የነርቭ ዘንግ፣ የጤና ሚኒስቴር

ምግብን በጥቃቅን ንጥረ ምግቦች የማበልፀግ ሥራም እንደ አንድ ስትራቴጂ በማስቀመጥ ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡ በእርግዝና ወቅትም በፅንስ ላይ የሚታይ ከአፈጣጠር ጋር የተያያዙ ችግሮችን በመጀመርያው ሦስት ወራት ለመለየት እንዲያስችል የአልትራሳውንድ ምርመራን ተደራሽ ለማድረግ የአልትራሳውንድ መሣሪያዎች ግዥ፣ ሥርጭትና በአጠቃቀም ዙሪያ ሥልጠናዎችን ለአዋላጅ ነርሶች የመስጠት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

በአሥር ዓመቱ  ፍኖተ ካርታም ላይ እንደተቀመጠው በነርቭ ዘንግ ክፍተትና የአዕምሮ ውኃ መቋጠር እንዲሁም ከፍተኛ ሕክምና ለሚያስፈልጋቸው የጤና ችግሮች ተገቢው የስፔሻሊቲና ሰብስፔሻሊቲ ባለሙያ የማፍራትና አስፈላጊው የሕክምና መሣሪያና የመድኃኒት አቅርቦትን ለማቅረብ ታቅዶ በሁለተኛው የጤና ሴክተር ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ በማካተት ወደ ተግባር መገባቱን ዳይሬክተሩ አብራርተዋል፡፡

‹‹እኛ እንደ ባለሙያ አገልግሎት በምንሰጥበት ጊዜ ከምናያቸው ነገሮች የተለያዩ ነገሮችን መገንዘብ ብንችልም የነርቭ ዘንግ ክፍተትና የአዕምሮ ውኃ መቋጠር ችግር ምን ያህል ከባድ እንደሆነ የሚያውቁት/የሚረዱት ችግሩ የገጠማቸው ቤተሰቦችና ልጆች ናቸው፤›› ያሉት የኢትዮጵያ ኒወሮሰርጂካል ሶሳይቲ ፕሬዚዳንት አቤኔዘር ትርሲት አክሊሉ (ዶ/ር) ናቸው፡፡ 

ለዚህ ዓይነቱ ችግር መፍትሔው ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ እንደሚወሳው መከላከል ላይ በቂ ሥራ ማከናወን መሆኑን ገልጸዋል፡፡ መከላከሉ ሦስት ደረጃዎች እንዳሉት፣ ከእነዚህም መካከል የመጀመርያ ደረጃ መከላከል በሽታው ከመከሰቱ በፊት ወላድ ወይም ነፍሰ ጡር እናቶች የፎሊክ አሲድ ንጥረ ነገር በብዛት መወለድ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

ባደጉ አገሮች ተሞክሮ ውጤታማ ሆኖ የተገኘውን ይህን ዓይነት የመከላከል ዘዴ መጠቀም የችግሩን መጠን እንዱቀንስ ያደርገዋል፡፡ የችግሩ መቀነስ ደግሞ የተጠቁት ልጆች የሚያጋጥማቸው ችግር ከባድነትን እየቀነሰ እንደሄደ የሚያደርገው መሆኑን ከዳይሬክተሩ ማብራሪያ ለመረዳት ተችሏል፡፡

ሁለተኛው የመከላከል ዘዴ በእርግዝና ወራት ችግሩ መኖሩን የማወቅና ለቀጣይ ሕክምናዎች ቤተሰቡን ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግ፣ ሦስተኛው መከላከያ ደግሞ ችግሩ ከተፈጠረ በኋላ ለልጆችና ለቤተሰቦቻቸው ትክክለኛ የሆነ እንክብካቤ ማድረግ ይህንን ማድረግ ጥቅሙ ልጆች ላይ ከችግሩ ጋር ተያይዞ የሚመጡ ተዛማጅ ነገሮችን ለማስቀረት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ነው ያመለከቱት፡፡

በነርቭ ዘንግ ክፍተትና በአዕምሮ ውኃ መቋጠር ላይ የሚሠራ ‹‹ሆፕ – ኤስቢኤች›› የተባለ ግብረሰናይ ድርጅት መሥራችና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቤዛ በሻዳ፣ ‹‹የነርቭ ዘንግ ክፍተትና የአዕምሮ ውኃ መቋጠር በሕፃናትና በተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ላይ የሚያስከትለው ጫና በእጅጉ የተወሳሰበና ተስፋ የሚያስቆርጥ ነው፤›› ብለዋል፡፡

ይህ ዓይነቱ በሽታ ከፍተኛ በሚባል መልኩ ትኩረት ከሚቸራቸው የጤና ችግሮች ውስጥ ተመድቦ የተቀናጀ የመከላከል ሥራ ካልተከናወነ እንዲሁም ከችግሩ ጋር ለተወለዱ ሕፃት የሕክምናና የድጋፍ አገልግሎት ካልተደረገላቸው በስተቀር የሚያስከትሉት የአጭርና የረዥም ጊዜ አሉታዊ ተፅዕኖ ከፍተኛ እንደሆነ ነው የተናገሩት፡፡

ከነርቭ ክፍተትና ከአዕምሮ ውኃ መቋጠር ጋር አብረው የሚወለዱ ሕፃናት አያይዘውም እስከ 100,000 ይደርሳሉ፡፡ በዚህም የተነሳ ለእነዚህ ሕፃናት የሚያስፈልጋቸው የጤናና ልዩ ልዩ ድጋፎችን ለማቅረብ እጅግ አድካሚና ብዙ ጥረቶችን የሚጠይቅ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

አሁን ያሉት ጤና ተቋማት የተጠቀሱትን አገልግሎት ለመስጠት መድረስ የሚችሉት እስከ 10,000 ለሚሆኑ ሕፃናት ሲሆኑ ቀሪዎቹ 90,000 ሕፃናት ምን እንደሚያጋጥማቸው መገመትና መረዳት እንደማያዳግትና ከዚህ አንፃር በበርካታ ጥናቶች ተደግፎ ውጤታማ የሆነው ምግብን የማበልፀግ ሥራ ላይ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

እንደ ሥራ አስኪያጁ አባባል የፎሊክ አሲድ በቅድሚያ በመውሰድ እናቶች ለእርግዝና ዝግጁ እንዲሆኑ ማድረግና የጤና ተቋማት በተለየ ለዚህ ዓይነቱ አገልግሎት የተለዩ የልቀት ማዕከላት መሠረታዊ የብዝኃ ዲስፒሊን አልግሎቶችንና ሌሎችንም ድጋፎች የመስጠት ኃላፊነት አለባቸው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የምግብ ሳይንስና ሥርዓተ ምግብ ዳይሬክተር ማስረሻ ተሰማ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ ባለፉት አሥር ዓመታት በተላላፊ በሽታ ሳቢያ ይከሰት የነበረው የሕፃናት ሞት መጠን እየቀነሰ ቢመጣም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መረጃዎች እንደሚያስረዱት ከወሊድ ጋር ተያይዞ በሚመጣ ችግር ሳቢያ የሞት መጠኑ እየጨመረ መጥቷል፡፡

ለሞት መጠኑ መጨመር ትልቅ አስተዋጽኦ ከሚያደርጉት የጤና ችግሮች መካከል በወላድ እናቶች ደም ውስጥ በቂ የሆነ የፎሊክ አሲድ አለመኖር መሆኑን መረጃዎችን በማጣቀስ ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡ በ2011 ዓ.ም. አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም ክልሎች በተካሄደው ጥናት ከወላድ እናቶች መካከል በሆዳቸው ወይም በደማቸው ፎሊክ አሲድ የተገኘባቸው  40 ከመቶ ብቻ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ የጥቃቅን ንጥረ ነገሮች እጥረት (ማይክሮ ኒውትረንት ዴፊሼንሲ ከፍተኛ የሆነ የጤና ችግር እያስከተለ እንደሚገኝ የጠቆሙት የሥርዓተ ምግብ ዳይሬክተሩ ይህንን መሠረት ያደረገ አገር አቀፍ የሥርዓተ ምግብ ፖሊሲና ስትራቴጂዎች መቅረፅ፣ በተለይም ከስትራቴጂዎቹ መካከል የተሰባጠረ (ዳይቨርስፋይድ) ምግብ መጠቀም ዘላቂ መፍትሔ እንደሆነ አመልክተዋል፡፡

የነርቭ ዘንግ ክፍተትና የአዕምሮ ውኃ መቋጠር በኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ ጥቅምት 25 ቀን 2014 ዓ.ም. የተከበረው ‹‹የጤና መብቶችዎን ይጠይቁ›› በሚል መሪ ቃል ነው፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...