Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከ3,887 በላይ የሳይበር ጥቃቶች መሰንዘራቸው ተገለጸ

በኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከ3,887 በላይ የሳይበር ጥቃቶች መሰንዘራቸው ተገለጸ

ቀን:

  • መላው ዓለም በአንድ ዓመት በተከሰቱ የሳይበር ጥቃቶች 2.5 ትሪሊዮን ዶላር ኪሳራ መድረሱ ተነግሯል

በኢትዮጵያ የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነትና የጥቃት ሙከራ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱንና በ2012 .ም. 1087 አደገኛ የሳይበር ጥቃቶች መድረሳቸውን፣ ባለፈው ዓመት በ2013 ዓ.ም ደግሞ ጥቃቱ በ150 በመቶ ጨምሮ ወደ 2,800 ከፍ ማለቱንና በሁለቱ ዓመታት በድምሩ ከ3,887 በላይ የሳይበር ጥቃቶች መሰንዘራቸውን፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ሰኞ ጥቅምት 1 ቀን 2014 ዓ.ም. አስታወቀ፡፡

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ሹመቴ ግዛው (ዶ/ር)፣ ‹‹የሳይበር ደኅንነት የጋራ ኃላፊነት ነው! እንወቅ! እንጠንቀቅ!›› በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ ሁለተ ጊዜና በዓለም 18 ጊዜ የሚከበረው የሳይበር ደኅንት ወር በሸራተን አዲስ ሲከፈት እንደተናገሩት፣ የሳይበር ደኅንነት ወር የግንዛቤ ማስጨበጫ ወር ነው፡፡ ዓለም በሳይበር ምኅዳር ምክንያት አንድ መንደር በሆነችበት በዚህ ዘመን ስለሳይበርና የሳይበር ደኅንነት ምንነት፣ የዘርፉን ባህሪያት፣ አዎንታዊና አሉታዊ ጎኖቹና ተፅዕኖዎቹን በአግባቡ ማወቅና መረዳት ከምንጊዜውም በላይ ወሳኝ ጉዳይ እየሆነ መጥቷል ብለዋል፡፡ ምክንያቱም የሳይበር ምኅዳሩ እየፈጠረ በመጣው ከፍተኛ ተፅዕኖ ምክንያት የኃያላኑም ሆነ በማደግ ላይ ያሉት አገሮች ዋነኛ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የማኅበራዊ መወዳደሪያ መድረክ ሆኗል ሲሉም አክለዋል፡፡ የሳይበር ምኅዳር ሁሉን አቀፋዊመሆን ይዞ የመጣውን አያሌ መልካም ዕድሎች የመኖራቸውን ያህል፣ በተቃራኒው ደግሞ ለአገሮች ሉዓላዊነትና ለሕዝቦች ደኅንነት የሥጋት ምንጭ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያም በተለያዩ መንገዶች የሳይበር ምኅዳሩ አካል እንደ መሆኗ መጠን ዘርፉ ይዞት የመጣውን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ከድኅነት ለመውጣት በሚደረገው ርብርብ እንደ መስፈንጠሪያ ኃይል (Springboard) ሆኖ የሚያግዝ፣ ብዙ ዕድሎችን የሚፈጠርና በርካታ የዕድገት አማራጮችንም የሚሰጥ መሆኑን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡ የሳይበር ምኅዳሩ ተለዋዋጭ፣ ውስብስብና ድንበር የለሽ መሆኑ፣ ሊደርስ የሚችል ጥቃትን በመከላከል ህልውናንና ተወዳዳሪነትን ለማረጋገጥ ተጠቃሚነትንና የጎንዮሽ ጉዳቱን የመቋቋም አቅምን በእኩል ደረጃ ተመጋግብው እንዲሄዱ ማድርግ እንደሚያስፈልግም አክለዋል፡፡

በርካታ ዓለም አቀፋዊ ተቋማት የየራሳቸው የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነትና ጉዳት ትንበያ ቀመር እንዳለቸው የገለጹት ሹመቴ (ዶ/ር)፣ የዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም (World Economy Forum) ዓመታዊ የሥጋት ሪፖርትን መመልከት ቢቻል፣ ከአምስቱ በዓለም ላይ ከተጋረጡት ዋና ዋናጋቶች መካከል አንዱ የሳይበር ጥቃት ነው ብለዋል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2020 ብቻ በተከሰቱ የሳይበር ጥቃቶች በዓለም ላይ 2.5 ትሪሊዮን ዶላር ኪሳራ ማጋጠሙን፣ በቀጣይ እስከ 2025 ኪሳራው ወደ ስድስት ትሪሊዮን ዶላር ከፍ እንደሚል ይኼው የፎረሙ ትንበያ እንደሚያሳይ አብራርተዋል፡፡

ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ባወጣው ዘገባ በባንኮች ላይ ብቻ ባነጣጠሩ ጥቃቶች እ.ኤ.አ. በ2016 የነበረው የ600 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ 2020 አንድ ትሪሊዮን ዶላር በላይ መድረሱን ጠቁመው፣ ችግሩ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ በሳይበር ደኅንነት ምክንያት ባንኮችን እያስወጣቸው ካለው ዘጠኝ በመቶ ጠቅላላ ዓመታዊ ገቢያቸው እስከ 50 በመቶ ድረስ ከፍ ሊል እንደሚችል ገልጾ IMF ማስጠንቀቁን አስታውሰዋል፡፡

በኢትዮጵያም የሳይበር ጥቃት ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረው፣ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት፣ ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ አንደኛና ሁለተ ዙር የውኃ ሙሌቶች፣ በ2013 ዓ.ም. የተካሄደው አገራዊ ምርጫና በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል እየተካሄደ ያለው የሕግ ማስከበርና የህልውና ዘመቻ ዋና ዋና ምክንያቶች መሆኑን ሹመቴ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

በአገሪቱ ቁልፍ መሠረተ ልማቶችና ተቋማት እንዲሁም በዜጎች ላይ የሚደርሰው የሳይበር ጥቃት ከዓመት ወደ ዓመት እየጨመረመምጣቱን፣ እንደ አገር ችግሩን የሚመጥን ቅድመ ዝግጅት ካልተደረገና ዘላቂ መፍትሔ ካልተቀመጠ የአገሪቱ ሰላም፣ ልማትና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳድርና በአገር ህልውና ላይ አደጋ ሊጋርጥ እንደሚችል አስረድተዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ተቋማትም ሆነ ኅብረተሰቡ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን የመጠቀም ልምዱ እያደገ የመምጣቱን ያህል፣ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የሳይበር ጥቃቶችን የመከላከል አቅሙና የሳይበር ደኅንነት ግንዛቤው በሚፈለገው መጠን ባለማደጉ ለከፍተኛ አደጋ ሊጋለጥ ስልሚችል፣ አንዱ ለሌላው እንደሚያስፈልግ ሹመቴ (ዶ/ር) አክለዋል፡፡

‹‹ጥናቶቻችን እንደሚያመለክቱት አብዛኛዎቹ ተቋማት ሥራቸውን በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ ከሚሰጡት ትኩረት አንፃር የቴክኖሎጂውን ደኅንነት ለመጠበቅና ሊያጋጥሙ የሚችሉ አደጋዎችን ለመከላከል የሚያደርጉት ጥረት እጅግ አነስተኛ ነው፤›› በማለት ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡ ለአደጋዎች መጋለጥ ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም በግንባር ቀደምነት የሚጠቀሰው ግን በተቋማትም ሆነ በኅብረተሰቡ ውስጥ ያለው የሳይበር ደኅንነት የግንዛቤ ማነስ መሆኑን ጥናቶች ሲያመላክቱ፣ የተቋማትንና የኅብረተሰቡን የሳይበር ደኅንነት ንቃተ ህሊና የሚያሳድጉ ተግባራትን ማከናወን የአገሪቱን የሳይበር ደኅንነት አቅም ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑን በመረዳት፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) የተለያዩ የሳይበር ደኅንነት ንቃተ ህሊና ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት፣ የግንዛቤ ማስጨበጫና የሳይበር ደኅንነት ንቃተ ህሊና ግንባታ ሥራዎችን ሲሠራ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡ ሳይበርኛ በሚል በሚዲያ የሚተላለፉ ፕሮግራሞች ለአብነት ያህል ተጠቃሽ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

ሆኖም የሳይበር ደኅንነት ንቃተ ህሊናን ማሳደግና ደኅንነትን ማስጠበቅ በአንድ ተቋም ብቻ ሊከናወን የሚችል ተግባር ስላልሆነ የመንግሥትና የግል ተቋማት፣ መገናኛ ብዙኃን፣ የጥበብ ሰዎች፣ የትምህርትና የምርምር ተቋማትና ሌሎችም ጉዳዩ የሚመለከታችሁ አካላት ሁሉ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡ የኢዜማ መሪና የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)ን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ተጋባዥ እንግዶች በውይይቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...