Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ መምጣቱ ተጠቆመ

በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ መምጣቱ ተጠቆመ

ቀን:

በመድኃኒትና የሕክምና መሣሪያ እጥረት 18 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገልጿል

በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ መምጣቱን የተባበሩት መንግሥታት ሰብዓዊ ዕርዳታዎች ማስተባባሪ ሕፈት ቤት እ.ኤ.አ. ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 4 ቀን ድረስ የሰበሰበውን መረጃ መስከረም 27 ቀን 2014 .. ይፋ ባደረገው ሪፖርት አስታወቀ፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያ የሚከሰተውን አስቀድሞ ለመገመት አዳጋች እየሆነ እንደመጣም የጠቆመው ጽሕፈት ቤቱ፣ በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ፍላጎት እንደጨመረና ጦርነቱ ወደ አጎራባች ክልሎች አማራና አፋር ከተስፋፋ ወዲህ፣ ድጋፍ የሚጠብቁ ሰዎች ቁጥር እንደናረ ገልጿል።

የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ዕርዳታዎች ማስተባባሪ ሕፈት ቤት (ኦቻ)፣ ከሰኔ አጋማሽ አንስቶ በትግራይ ክልል የመሠረታዊ አቅርቦቶች ዋጋ እጅግ ከፍተኛ በሚባል ደረጃ መናሩንና የሕክምና መሣሪያ እጥረት ፈታኝ መሆኑን አብራርቷል፡፡

በአይደር ሆስፒታል ውስጥ አንድ ሕፃንን ጨምሮ 18 ሰዎችሄሞዲያሊሲስ ካቲተር› በማጣታቸው መሞታቸውንም አስታውቋል፡፡ እንደ ኦቻ ሪፖርት፣ በሽረ የነዳጅ ዋጋ 2,300 በመቶ የጨመረ ሲሆን፣ በመቀሌና በሌሎች ከተሞችም ገበያ ላይ የአስፈላጊ ቁሳቁሶች እጥረት መከሰቱን አክሏል፡፡ መሠረታዊ የምግብና ሌሎችም አስፈላጊ ቁሳቁሶች ዋጋ መናር ነዋሪዎችን እየፈተነ መሆኑን፣ ሥራቸውን ያጡ አቅመ ደካማ ሰዎች የመግዛት አቅማቸው መቀነሱን፣ በተለይም ከሰኔ ወዲህ ሲቪል ሠራተኞችና ሌሎችም ተቀጣሪዎች ደመወዛቸው ስለተቋረጠ መሠረታዊ አቅርቦት ለማሟላት መቸገራቸውን በሪፖርቱ አስረድቷል።

በባንኮች በቂ ገንዘብ ባለመኖሩ ከነዋሪዎች በተጨማሪ የሰብዓዊ ዕርዳታ ድርጅቶች ሠራተኞችም ለወራት ደመወዝ እንዳልወሰዱና ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ምግብ ነክ ያልሆኑና በዕርዳታ የተሰጧቸው ቁሳቁሶችን እየሸጡ ምግብ እየገዙ ስለመሆናቸው ታማኝ ሪፖርቶች እንደጠቆሙት ኦቻ ጠቁሟል፡፡

ከአማራና አፋር ክልሎችም ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን በሪፖርቱ ገልጾ፣ በአማራ ክልል ከሰሜን ጎንደር፣ ከማዕከላዊ ጎንደር፣ ከደቡብ ጎንደርና ከደቡብ ወሎና ከአዊ ዞኖች የተፈናቀሉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች አፋጣኝርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ጠቁሟል

ኦቻ ኢትዮጵያ ባወጣው ሪፖርት፣ የሰብዓዊርዳታ አቅርቦትን የፈተነው የነዳጅ እጥረት ከትግራይ ክልል 75 በመቶ ያህል አካባቢ ለዕርዳታ ተደራሽ ቢሆንም፣ ከኤርትራ ጋር በሚያዋስነው ሰሜናዊ ክፍል፣ በምዕራብና በሰሜን ምዕራብ በኩል የፀጥታ ሁኔታው አስተማማኝ ስላልሆነ እስካሁን ዕርዳታ ለመስጠት አለመቻሉን ጠቁሟል።

በሌላ በኩል በትግራይ ክልል ያለው የነዳጅና የገንዘብ እጥረት የዕርዳታ አቅርቦቱን እንዳስተጓጎለም አክሏል፡፡ በአፋር ክልል በኩል ከሰመራ ወደ አቤላ፣ ከዚያም ወደ መቀሌ የሚወስደው መንገድ ብቻ ለዕርዳታ ክፍት መደረጉደቱን እንዳስተጓጎለ ጠቁሞ፣ በአማራና በአፋር ክልሎች አሁንም ድረስ ግጭት ያለባቸው አካባቢዎች ስላሉ ዕርዳታ ለማቅረብ ፈተና እንደገጠመው ድርጅቱ አስታውቋል። እ.ኤ.አ. ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 5 ቀን ድረስ በአፋር በኩል 80 የሰብዓዊ ዕርዳታ የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ መግባታቸውን፣ ከሐምሌ ወር ወዲህ ወደ ክልሉ የተላኩ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች በአጠቃላይ 686 መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡ ይህም አጠቃላይ ከሚፈለገው 12 በመቶ ብቻ መሆኑንና ኦቻ በላካቸው 80 ተሽከርካሪዎች ማድረስ የተቻለው ምግብ፣ ውኃ፣ አልሚ ምግብና የንፅህና መጠበቂያ ብቻ መሆኑን አስረድቷል፡፡

ሆኖም ግን እጅግ አስፈላጊ የሆኑ የሕክምና መሣሪያዎችና ነዳጅ ለመውሰድ እንዳልተፈቀደ፣ ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ትግራይ ነዳጅ የተላከው ከዘጠኝ ሳምንታት በፊት መሆኑንና አሁን ላይ ስምንት ነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪዎች ሰመራ ላይ ከመንግሥትቃድ እስኪሰጣቸው እየተጠባበቁ መሆኑን አክሏል።

የረድዔት ድርጅቶች እንደሚሉት በክልሉ ያለውን የዕርዳታ ፍላጎት ለማሟላት በየቀኑ 100 ሰብዓዊ ዕርዳታ የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች መድረስ አለባቸው። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የአውሮፓብረት ለሁለተኛ ጊዜ የሰብዓዊርዳታ የጫኑ አውሮፕላኖችን ወደ ትግራይ መላኩን አስታውቋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...