Wednesday, July 24, 2024

[ክቡር ሚኒስትሩ በተጋበዙበት የውይይት መድረክ ላይ ስለሚያደርጉት ንግግርና የሚነሱ ጥያቄዎችን እንዴት እንደሚመልሱ ከአማካሪያቸው ጋር ሆነው በቢሮዋቸው ዝግጅት እያደረጉ ነው]

 • ክቡር ሚኒስትር በቀላሉ ይወጡታል አይጨነቁ፡፡
 • ኧረ አልተጨነቅኩም፣ ለማንኛውም መዘጋጀቱ አይጎዳም ብዬ እንጂ ሳልዘጋጅ ላቀርበው የምችለው ነገር ነው። 
 • ልክ ነዎት፣ ስለሚናገሩት ነገር ቢያውቁም ጥንቃቄ ማድረግ ይበጃል። 
 • የምን ጥንቃቄ ነው የምታወራው? 
 • ማለቴ በውይይቱ የሚሳተፉት በዘርፉ ልምድ ያካበቱ ስለሆኑ ዝግጅት ማድረግዎ ተገቢ ነው ማለቴ ነው። 
 • በዘርፉ ልምድ ያካበቱ ከሆነማ የበለጠ ቀላል ይሆናል እንጂ፡፡
 • አይምሰልዎት፡፡
 • እንዴት?
 • ስለዘርፉ ጠንቅቀው የሚያውቁ ሰዎች ጉንተላ የሚጀምሩት በጥያቄ ነው። 
 • አልገባኝም?
 • እርስዎ ንግግር ሲያደርጉ የተስማሙ መስለው ያዳምጣሉ፡፡
 • ከዚያስ?
 • እርስዎ እንደጨረሱ ቀስ እያሉ እነሱ በዘርፉ ያካበቱትን ልምድ ተጠቅመው ከባድ ጥያቄዎችን ሊሰነዝሩ ይችላሉ፣ ጥንቃቄ ያስፈልጋል ያልኩት ለዚህ ነው ክቡር ሚኒስትር። 
 • እውነትህን ነው ባልተዘጋጀሁበት ወይም በማላውቀው ጉዳይ ላይ ጥያቄ ሊያነሱ ይችላሉ፡፡ 
 • እሱን እኮ ነው የምልዎት፡፡ 
 • እና ምን ማድረግ አለብህ ነው የምትለኝ?
 • መዘጋጀት ነው መፍትሔው ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ምንድነው የምታወራው? ምን ዓይነት ጥያቄ እንደሚነሳ አውቄ ነው ዝግጅት የማደርገው? 
 • ዝግጅት ማድረግ ያለብዎት ጥያቄውን ለመመለስ አይደለም እኮ?
 • እና ለምንድነው?
 • እንዴት አድርገው ጥያቄውን እንደሚያመልጡ ነው፡፡ 
 • ጥያቄውን ማምለጥ? እንዴት?
 • አይጨነቁ፣ ጥሩ ጥሩ ዘዴዎች አሉ፡፡
 • ለምሳሌ?
 • አንደኛው ቴክኒክ የተወረወረውን ከባድ ጥያቄ መልሶ መወርወር ነው፡፡
 • ምን ማለት ነው?
 • እርስዎ በጥሞና ያዳምጡኝ እንጂ አብራራዋለሁ ክቡር ሚኒስትር፡፡ 
 • እሺ ቀጥል፡፡
 • ወደ እርስዎ ከባድ ጥያቄ ሲወረወር እጅግ በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው ብለው አድናቆትዎን ይገልጻሉ።
 • እሺ ከዚያስ?
 • ከዚያ ለተነሳው ጥያቄ ማብራሪያ ከመስጠቴ በፊት ከቤቱ ሐሳብ መሰንዘር የሚፈልግ ካለ ዕድል ልስጥ ብለው መልሰው ይወረውሩታል። 
 • ሆሆሆ… እሺ?
 • ከቤቱ ጥያቄውን ያነሱት ሳይቀሩ እየተሯሯጡ መልስ ይሰጡበታል፡፡ 
 • ወይ ጉድ ማለፊያ ነው፣ ትክክለኛ መልስ ባይሆንስ?
 • ቴክኒኩ ለዚህም ይጠቅማል ክቡር ሚኒስትር።
 • እንዴት?
 • በዚህ ሒደት ወስጥ እርስዎ የማሰላሰያ ፋታና መነሻ ሐሳብ ያገኛሉ፡፡
 • ድንቅ ዘዴ ነው፣ ስሙን ምን ነበር ያልከው፡፡
 • መልሶ መወርወር! 

[ክቡር ሚኒስትሩ አመሻሹን ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲመለሱ ባለቤታቸው በትካዜ ውስጥ ሆነው ከመስቀል አደባባይ የሚተላለፈውን የቴሌቪዥን ትዕይንት እየተመለከቱ አገኟቸው

 • ምንድነው እንዲህ ቀልብሽን የሳበው
 • ቀልብሽን ነው ያልከው?
 • አዎ ቴሌቪዥኑ ላይ ተመስጠሻል እኮ? አሃ… በዓለ ሲመቱ እየተላለፈ ነው እንዴ እሱማ ይመስጣል፡፡
 • በዓለ ሲመቱማ አለፈ፡፡
 • መድረኩ የመስቀል አደባባይ አይደለም እንዴ?
 • መድረኩማ ነው፣ ፕሮግራሙ ግን ሌላ ነው፡፡
 • ምንድነው ፕሮግራሙ?
 • ፀሎት ነው፡፡ 
 • ፀሎት! የምን ፀሎት?
 • ፖለቲካው የተረጋጋ እንዲሆን ለፖለቲከኞቻችን አባቶች እየፀለዩ ነው። 
 • ጎሽ ጥሩ አድርገዋል፣ ለፖለቲካችን ፀሎት ያስፈልጋል፡፡ 
 • እሱ እኮ ነው ያስተከዘኝ።
 • ምኑ?
 • ለፖለቲካችን መፍትሔው ፀሎት መሆኑ?
 • ትክክል አይደለም እያልሽ ነው?
 • ወይ ጉድ… ለፖለቲካ ፀሎት?
 • ምናለበት?
 • እኔ ለፖለቲካ ችግር መፍትሔው ፖለቲካ እንደሆነ ነው የማውቀው። 
 • አንቺ ደግሞ ዝም ብለሽ መቃረን ትወጃለሽ፣ የሚፀልዩት ለፖለቲካው ብቻ ላይሆን ይችላል፡፡
 • ሌላ ለምን ሊሆን ይችላል?
 • ለፖለቲከኞችም ሊሆን ይችላል የሚፀልዩት፡፡
 • ለፖለቲከኞች ፀሎት? ለእነሱ ፀሎት አያስፈልግም፡፡
 • እና ምንድነው የሚያስፈልጋቸው?
 • ሁለት ሰባት፣ በሁለት ሰባት ካልሆነ የሰባ ሁለት ሰዓቱን መስጠት ነው፡፡
 • ምንድነው እሱ?
 • ፐርሶና ነን ግራታ!
 • ወይ ጉድ… አንቺ ጤነኛ አትመስይኝም፡፡
 • ብቻዬን ጤነኛ እንዴት ልሆን እችላለሁ ብለህ ነው?
 • ማለት?
 • ለፖለቲካ በሚፀለይበት አገር ማለቴ ነው!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...

ግለሰብ ነጋዴዎችን በአስገዳጅነት የንግድ ምክር ቤት አባል ለማድረግ ያለመው ረቂቅ አዋጅ ተከለሰ

በምትኩ የንግድ ተቋማት በአስገዳጅነት የንግድ ምክር ቤት አባል ይሆናሉ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ። ይህንን ደብዳቤ እየውና በጠየቁት መሠረት እንዲፈጸምላቸው አድርግ። ጉዳዩ ምንድነው? ከአንድ ክልል የቀረበ የትብብርና ድጋፍ ጥያቄ ነው። የምን ትብብር...

[ክቡር ሚኒስትሩ የቅርብ ወዳጃቸው ከሆነች አንድ ባለሀብት የተደወለላቸውን ስልክ አንስተው በኮሪደር ልማቱ ላይ የምታቀርበውን ቅሬታ እየሰሙ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እኔ የኮሪደር ልማቱ ላይ ተቃውሞም ሆነ ጥላቻ እንደሌለኝ የሚያውቁ ይመስለኛል? በዚህ እንኳን አትታሚም።  የእውነቴን ነው ክቡር ሚኒስትር። አውቃለሁ ስልሽ? ለኮሪደር ልማቱ አዋጡ ሲባልም ያለማመንታት አምስት ሚሊዮን...

[ክቡር ሚኒስትሩ በችግኝ ተከላ ፕሮግራም ላይ ሳይገኝ ከቀረው አንድ የተቋማቸው ባልደረባ የሆነ የተቃዋሚ ፓርቲ አባልን አስጠርተው እያናገሩ ነው]

ለምንድነው በዚህ አገራዊ ፋይዳ ባለው ፕሮግራም ላይ ያልተገኘኸው? ክቡር ሚኒስትር ህሊናዬ አልፈቀደልኝም። መቃወምና መተቸት ብቻ ውጤት የሚያመጣ መስልዎህ ከሆነ ተሳስተሃል። አልተሳሳትኩም ክቡር ሚኒስትር? ቆይ የመጀመሪያ ዓመት የችግኝ ተከላ...