Tuesday, July 23, 2024

[ክቡር ሚኒስትሩ ከፖለቲካ አማካሪያቸው ጋር በሱዳን ስላለው ሁኔታ መረጃ እየተለዋወጡ ነው]

 • ክቡር ሚኒስትር የሱዳን የውስጥ ሽኩቻ በቀላሉ የሚቀረፍ አይመስለኝም። 
 • ልክ ነህ ቀላል ጉዳይ አይደለም፣ በእኛ በኩል የወጣውን መግለጫ ተመለከትከው?
 • ምን መግለጫ ወጣ?
 • አለቃ በሱዳን ስላለው ሁኔታ በዓረብኛ መግለጫ አውጥተዋል፡፡
 • እሱንማ አይቼዋለሁ፣ ጽሑፉ ብቻ ሳይሆን መልዕክቱንም በዓረብኛ ነው የጻፉት። 
 • ምን ማለትህ ነው?
 • መልዕክቱ ነቆራ አዘል ነው ማለቴ ነው። 
 • ችግራችሁን ያለ ውጭ ጣልቃ ገብነት እንደምትፈቱት አምናለሁ አሉ እንጂ ሌላ ነገር እኮ የለውም።
 • እሱ እኮ ነው ነቆራው።
 • የውጭ ኃይሎችን ጣልቃ ገብነት…?
 • አዎ። 
 • እንዴት?
 • እነሱ በቀጥታ ያለውን መልዕክት አይደለም የሚያነቡት።
 • ምን ብለው ነው የሚያነቡት?
 • የውጭ ኃይሎች ስለሚጋልቧችሁ ነው ቀውስ የገጠማችሁ ብለው ነው የሚያነቡት፡፡ 
 • ለነገሩ እውነታውም እንደዚያ ነው። 
 • ዋና መልዕክቱም አንደዛ ነው!

[ክቡር ሚኒስትሩ የፀጥታ ጉዳዮችን በተመለከተ ከአማካሪያቸው ጋር እየተወያዩ ነው]

 • በሰሜኑ አካባቢ ምን አዲስ ነገር አለ? 
 • እስካሁን የማጥቃት እንቅስቃሴ ባይጀመርም፣ በመልሶ ማጥቃት ቁልፍ ቦታዎችን ተቆጣጥረናል። 
 • በመልሶ ማጥቃት ቁልፍ ቦታዎች ተይዘዋል? 
 • አዎ ክቡር ሚኒስትር። በተለይ ማይጠብሪን መቆጣጠራችን ትልቅ ነገር ነው። 
 • ማይጠብሪ ደግሞ የት ነው?
 • ማይጠብሪ ነዋ ክቡር ሚኒስትር ወደ ላይኛው…
 • ማይፀብሪ ማለትህ ነው? 
 • ማይፀብሪ ነው እንዴ? ለነገሩ ዋናው መያዙ ነው። 
 • ኖ… ኖ… ልክ አይደለህም… እዚህ ግጭት ውስጥ ያስገባን አንዱ ነገር ስያሜ አይደል እንዴ? በትክክለኛ ስያሜው ነው መጥራት ያለብህ።
 • እሺ፣ አስተካክላለሁ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ጥሩ፣ በዋና ከተማችንና አካባቢውስ ምን የተለየ እንቅስቃሴ አለ? የመንግሥት ምሥረታው በሰላም እስኪጠናቀቅ ልዩ ጥንቃቄ መደረግ አለበት። 
 • በአንዳንድ አካባቢዎች የዘረፋ እንቅስቃሴዎች ከመኖራቸው ውጪ በአዲስ አበባም ሆነ በዙሪያዋ ጥሩ ዝግጅት ተደርጓል።
 • የት አካባቢ ነው የዘረፋ ችግር ያለው?
 • እንጾጾ አካባቢ፡፡ 
 • የት አካባቢ?
 • እንጾጾ!
 • እንጦጦ ማለትህ ነው?
 • አዎ፣ እንደዚያ ማለቴ ነው። 
 • ለምን እንጦጦ አላልክም ታዲያ?
 • ቅድም ‘ጠ’ ን አትጠቀም ስላሉኝ ነው።
 • እኔ… መቼ ነው ያልኩት?
 • ማይጠብሪ ስል እኔ! 

[ክቡር ሚኒስትሩ በጠዋት ቢሮ እንደገቡ የሞባይል ስልካቸው ጠራ! የሚያከብሩት የቀድሞ ወዳጃቸው ነበር የደወለው]

 • እንደምናለህ ክቡር ሚኒስትር?
 • ክቡር ሚኒስትር የምትለውን ነገር ተው ብልህ አልሰማ አልክ በቃ?
 • ሕዝብ የሰጠህን ማዕረግ እንዴት ብዬ አስቀራለሁ? አይሆንም።
 • ሕዝብ የሰጠህን ነው ያልከው? እያሾፍክ ነው አይደል?
 • ኧረ አላሾፍኩም?
 • የሕዝብ ተመራጭ እንዳልሆንኩ ታውቅ የለም እንዴ ታዲያ?
 • ቢሆንም ፓርላማው ሹመትህን ተቀብሎ አፅድቋል፣ ስለዚህ ሹመትህን ማክበር የግድ ነው። 
 • እሱስ ልክ ነህ ግን…
 • ለነገሩ አልፈርድብህም።
 • እንዴት?
 • ሕዝብ እንዲያገለግሉ መሾማቸውን ዘንግተው እንደተከራዩት ቤት ብድግ ብለው የሚለቁ ሹመኞች ያሉበት አገር አይደል።
 • አንዳንዶቹ ልጅነት ስለሚያጠቃቸው እንደዚያ ያደርጋሉ።
 • ይገባኛል፣ ከሥልጣን መውረዳችን ካልቀረ በማለት መንግሥትን ተቃውመው ለማምለጥ የሞከሩ አሉ።
 • ከምን ለማምለጥ ነው የሚሞክሩት?
 • ከማዕቀብ!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፍተኛ ትርፍ ቢያገኝም የውጭ ምንዛሪ ገቢው ቅናሽ ማሳየቱ ተጠቆመ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2016 የሒሳብ ዓመት ያሰባሰበው የውጭ ምንዛሪ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ የቅርብ ወዳጃቸው ከሆነች አንድ ባለሀብት የተደወለላቸውን ስልክ አንስተው በኮሪደር ልማቱ ላይ የምታቀርበውን ቅሬታ እየሰሙ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እኔ የኮሪደር ልማቱ ላይ ተቃውሞም ሆነ ጥላቻ እንደሌለኝ የሚያውቁ ይመስለኛል? በዚህ እንኳን አትታሚም።  የእውነቴን ነው ክቡር ሚኒስትር። አውቃለሁ ስልሽ? ለኮሪደር ልማቱ አዋጡ ሲባልም ያለማመንታት አምስት ሚሊዮን...

[ክቡር ሚኒስትሩ በችግኝ ተከላ ፕሮግራም ላይ ሳይገኝ ከቀረው አንድ የተቋማቸው ባልደረባ የሆነ የተቃዋሚ ፓርቲ አባልን አስጠርተው እያናገሩ ነው]

ለምንድነው በዚህ አገራዊ ፋይዳ ባለው ፕሮግራም ላይ ያልተገኘኸው? ክቡር ሚኒስትር ህሊናዬ አልፈቀደልኝም። መቃወምና መተቸት ብቻ ውጤት የሚያመጣ መስልዎህ ከሆነ ተሳስተሃል። አልተሳሳትኩም ክቡር ሚኒስትር? ቆይ የመጀመሪያ ዓመት የችግኝ ተከላ...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላነጋግርህ የፈለኩት ክቡር ሚኒስትር፡፡ እርስዎማ ቀጠሮ መያዝ አያስፈልግዎትም፣ ምን ገጠመዎት? እኔማ ምን ይገጥመኛል አንተኑ ልጠይቅህ እንጂ? ምን? እውነት ለመናገር የማየው ነገር አሳስቦኛል፡፡ ይንገሩኝ...