Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናኢሰመኮ የምሥራቅ ወለጋ ዞን ኪራሙ ወረዳ ነዋሪዎች ደኅንነት ያሳስበኛል አለ

ኢሰመኮ የምሥራቅ ወለጋ ዞን ኪራሙ ወረዳ ነዋሪዎች ደኅንነት ያሳስበኛል አለ

ቀን:

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ኪራሙ ወረዳ የሚኖሩ ሰላማዊ ሰዎች ደኅንነታቸው አሥጊ ሁኔታ ውስጥ መሆኑ እንደሚያሳስበው፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ዓርብ መስከረም 14 ቀን 2014 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ በኪራሙ ወረዳ ቦቃ ቀበሌ መስከረም 7 እና 8 ቀን 2014 ዓ.ም. በተፈጸሙ ተያያዥ ጥቃቶች በአጠቃላይ 18 ሰዎች መገደላቸውን፣ እንዲሁም መስከረም 8 ቀን 2014 ዓ.ም. በውልማይ ቀበሌ በተፈጸመ ጥቃት 11 ሰዎች መገደላቸውን በነዋሪዎች እንደተነገረው ገልጿል፡፡

በኪራሙ ወረዳ ባለው አሳሳቢ የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት ከተለያዩ የወረዳው አካባቢዎች ተፈናቅለው በኖሌ ቀበሌ፣ በሀሮና በኪራሙ ከተሞች ተጠልልው የሚገኙ ከ40 ሺሕ በላይ ሰዎች ለወራት አስቸኳይ ሰብዓዊ ዕርዳታና ሌሎች ድጋፎችን ባለማግኘታቸው፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ መናገራቸውን ኮሚሽኑ በመግለጫው አክሏል፡፡

በአሁኑ ጊዜም ኪራሙ ወረዳን ከቡሬና ከነቀምት ጋር የሚያገናኙ ዋና ዋና መንገዶች፣ ለተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ዝግ መሆናቸውን ማረጋገጡን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በኪራሙ ወረዳ ያለውን የፀጥታ ሥጋት ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት፣ በነዋሪዎች ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት የሚያደርሱ ኃይሎችን ሕግ ፊት ለማቅረብ ተጨባጭ ዕርምጃዎችን እንዲወስዱ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡

“በተጨማሪም በግጭቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ሰዎችን ወደ ቀዬአቸው መመለሱ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ተፈናቃዮቹ ለከፋ ጉዳት ከመጋለጣቸው በፊት በአፋጣኝ ወረዳውን ከሌሎች አካባቢዎች የሚያገናኙ መንገዶች እንዲከፈቱና አስፈላጊው ሰብዓዊ ዕርዳታ መድረሱን እንዲያረጋግጡ ኢሰመኮ በጥብቅ ያሳስባል፤” በማለት ለፌዴራልና ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ማስታወቁን በመግለጫው አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ ነሐሴ 20 ቀን 2013 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ የኦነግ-ሸኔ ናቸው በተባሉ ታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት፣ ኪራሙ ወረዳ ውስጥ ከ150 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ሰዎችና ሌሎች ምንጮች እንደነገሩት ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡ በተጨማሪም ከነዋሪዎች የተውጣጡ ሰዎች ብሔርን መሠረት ባደረገ የአፀፋ ጥቃት 60 ሰዎች መገደላቸውን መግለጹ ይታወሳል፡፡

በወቅቱ ዋና ኮሚሽነሩ ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር)፣ በቅድሚያ የክልሉ የፀጥታ ኃይሎች ከፌዴራል የፀጥታ ኃይሎች ጋር እንዲቀናጁና የአካባቢውን ነዋሪዎች ደኅንነት እንዲያረጋግጡ፣ እንዲሁም የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ለጥቃቱ መፈጸም ክፍተት የፈጠረው የፀጥታ ኃይሎች ከአካባቢው መውጣት ምክንያት በአፅንኦት እንዲጣራ ጥሪ ማቅረባቸው አይዘነጋም፡፡    

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...