Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊአስገዳጅ መመርያ የሚሻው ቀሳፊው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ

አስገዳጅ መመርያ የሚሻው ቀሳፊው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ

ቀን:

  • ከሰኞ እስከ ሐሙስ 160 ሰዎች ሞተዋል

የኮቪድ-19 ቫይረስ አደገኛ ዝርያ የሆነው ‹‹ዴልታ›› ኢትዮጵያ ውስጥ መኖሩ ይፋ ከሆነና ከተረጋገጠ ውሎ አድሯል፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ኅብረተሰቡ ለዚህ በሽታ የሚሰጠው ትኩረት እየላላ መምጣትና የሚያሳየው መዘናጋት ለቫይረሱ መስፋፋትና መሠራጨት አስተዋጽኦ አበርከቷል፡፡ ይህ ዓይነቱም ሁኔታ ሕይወታቸው የሚያልፍ የሕሙማን ቁጥር በየጊዜው እያሻቀበ እንዲመጣ አድርጓል፡፡  

በኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መረጃ መሠረት ሰኞ መስከረም 10 ቀን 2014 ዓ.ም. 34፣ ማክሰኞ መስከረም 11 ቀን 43፣ ረቡዕ መስከረም 12 ቀን 47፣ ሐሙስ መስከረም 13 ቀን 37፣ በድምሩ 160 ሰዎች በኮቪድ-19 ቫይረስ ለሕልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል፡፡ በአጠቃላይ እስከ ሐሙስ መስከረም 13 ቀን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 338,306 ሲደርስ፣ ከበሽታው ያገገሙትም 305,223 ሰዎች ናቸው።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት በፅኑ የሚታመሙና ሕይወታቸው የሚያልፍ ሕሙማን ማሻቀቡን ያመለከቱት የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (/ር)፣ ለከባድ ሕመም የሚዳርገውና ለሞት የሚያበቃው አደገኛው የዴልታ ዝርያ በኢትዮጵያ በከፍተኛ ፍጥነት ቢስፋፋም፣  በኅብረተሰቡ ዘንድ እየተወሰደ ያለው የመከላከያ ዕርምጃ ግን አነስተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

‹‹ይህንን ከባድ ሁኔታ ጉዳቱን ለመቀነስ አንዱ ቁልፍ መከላከያ ዘዴ ክትባት በመሆኑ ከዚህ በፊት የነበረው የክትባት አሰጣጥ መመርያ ተሻሽሎ፣ ዕድሜያቸው 18 እና ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ሁሉ ክትባት እተሰጠ ነው፡፡ ስለሆነም ክትባቱን መውሰድ አደገኛውን ዴልታ ዝርያም ሆነ ሌሎቹን ዝርያዎች የመከላከል አቅማቸው ከፍተኛ እንዲሆን ያግዛል፤›› ብለዋል፡፡

የትምህርት ቤቶች መከፈት፣ ልዩልዩ በዓላትና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ምረቃና ሌሎች ለቫይረሱ ሥርጭት አጋላጭ ሁኔታዎች በቀጣይ ያሉ አሳሳቢ ሁኔታዎች መሆናቸውን የጠቀሱት ሚኒስትሯ ከዚህ አሳሳቢ ሁኔታ በመነሳት ማኅበረሰቡና የሚመለከታቸው ተቋማት በሙሉ መመርያ 803/2013 እንዲተገብሩ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የተለያዩ ሰዎች በሰጡት አስተያየት መንግሥት አስገዳጅ መመርያዎችን ማውጣትና ይህን በማያከብሩት ላይ ጠበቅ ያሉ ዕርምጃዎች ካልተወሰደ ሰው ያልቃል የሚል እምነት አላቸው፡፡ በተለይም እያስጨነቃቸው ያለው ትምህርት ቤቶች ሲከፈቱ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆቻቸው ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል የሚለው ጉዳይ ነው፡፡ ባለፈው የነበረው የቀን ፈረቃ አሁን አይኖርም የሚል ወሬም አለ፡፡ ከዚህ አኳያ ሰው ማዳን ከሁሉ ሊቀድም ይገባል ይላሉ፡፡

በሽታው እንዳይሠራጭ ፊት መንግሥት ትልቅ የቁጥጥር ሚና ይጫወት እንደነበር፣ አሁን ግን ሁሉ ነገር ወደ ቀድሞ ቦታው እንደተመለሰ፣ ታክሲዎችና ሎንችኖች ጠቅጥቀው እንደሚጭኑ፣ ማስክ ሳያደርጉ የሚገቡ እንደማይከለከሉ፣ ማስክ አለማድረግን እንደ መብት የሚቆጥሩም እንዳሉ አስተያየት ሰጪዎቹ ገልጸው፣ አንዳንድ ግለሰቦችም በሽታውን ከፖለቲካና ከሃይማኖት ጋር በማገናኘት ለማወናበድ እንደሚንቀሳቀሱ አስረድተዋል፡፡

››ስብሰባዎች፣ ሰላማዊ ሠልፎች ያለጥንቃቄ ይካሄዳሉ፡፡ የበሽታው መስፋፋት እጅግ በጣም አሥጊ ነውና መንግሥት የፊቱን ጥንካሬ ቢላበስና ቁጥጥር ቢያደርግ መልካም ነው፡፡ በሽታውን ማሠራጨትና ከዘመናዊ ሕክምና ራስን ማሸሽ አሳዛኝ የጊዜው ክስተት ነውና ይታሰብበት፤›› ሲሉም ተደምጠዋል፡፡  

የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እያንዳንዱ ግለሰብ፣ ቤተሰብ፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የጤና ባለሙያዎች፣ መምህራንና ሌሎችም  ባለድርሻ አካላት ተደጋግሞ የሚገለጹትን የመከላከያ መንገዶችን እንዲተገብሩ አሳስቧል፡፡

 

‹‹ከኮቪድ ተጠበቁ!››

እርስዎ የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶችን በአግባቡ እየተገበሩ ነው?

  • ማስክ ሳያደርጉ በፍፁም አይንቀሳቀሱ!
  • የእጅዎን ንፅህና በአግባቡ ይጠብቁ!
  • በቂ የአየር ዝውውር በሌለበትና ሰው በተሰበሰበበት ቦታ አይገኙ!

ይኼንን በመተግበር ራስዎንና ቤተሰብዎን ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ይታደጉ።

አራቱ ‹‹›› ሕጎች

  • መራራቅ፡አካላዊ ርቀት መጠበቅ!
  • መታጠብ፡እጅን በተደጋጋሚ በውኃና በሳሙና መታጠብ!
  • መቆየት፡አስገዳጅ ካልሆነ ቤት ውስጥ መቆየት!
  • መሸፈን፡ከቤታችን ወጥተን ስንንቀሳቀስ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) መጠቀም!

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...