Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለተፈናቃዮች ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ መድኃኒቶችና ግብዓቶች መሠራጨታቸው ተገለጸ

ለተፈናቃዮች ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ መድኃኒቶችና ግብዓቶች መሠራጨታቸው ተገለጸ

ቀን:

በአማራና በአፋር ክልሎች በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ተፈናቃዮችና በግጭቱ አካባቢ ለሚኖሩ ማኅበረሰቦች አገልግሎት የሚውሉ ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ልዩ ልዩ ዓይነት መድኃኒቶችና ግብዓቶች እየተሠራጩ መሆኑን፣ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስትሯ (ዶ/ር) ሊያ ታደሰ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለጹት፣ በአሸባሪነት በተፈረጀው ሕወሓት ምክንያት ከ1.9 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለጤና አገልግሎት ችግር ተዳርገዋል፡፡

በሁለቱ ክልሎች የተፈጠረውን የመድኃኒትና የሕክምና ግብዓቶች ክፍተት ለመሙላት፣ በአማራ ክልል ከ186 ሚሊዮን ብር በላይ፣ በአፋር ክልል ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የመድኃኒትና የሕክምና ልዩ ልዩ ግብዓቶች እየተሠራጩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ተጨማሪ መድኃኒቶችንና ግብዓቶችን ከአገር ውስጥ ከውጭ ግዥ ለመፈጸም እየተሠራ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

ከመድኃኒትና ከግብዓት ድጋፍ በተጨማሪ ለድንገተኛ ሕክምና አገልግሎት እንዲውል ለአማራ ጤና ቢሮ 23 ሚሊዮን ብር፣ ለአፋር ጤና ቢሮ 3.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ መደረጉንም ገልጸዋል፡፡

ለተፈናቃይ እናቶችና ሕፃናት የሥርዓተ ምግብና አልሚ ምግቦችን ተደራሽ ለማድረግ አስፈላጊው ጥረት፣ እንዲሁም ለሁሉም ተፈናቃዮች በተጠለሉባቸው አካባቢዎች በጤና ባለሙያዎች የጤና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ሚኒስትሩ ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

ከሚኒስትሯ ማብራሪያ ለመረዳት እንደተቻለው በአማራ ክልል እስካሁን ድረስ ከ1,837,642፣ በአፋር ክልል 1121.158 ሰዎች ተፈናቅለዋል፡፡ በአማራ ክልል ካሉት ተፈናቃዮች መካከል 256,000 ያህሉ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት፣ እንዲሁም 71,641 የሚሆኑት ደግሞ ነፍሰ ጡርና የሚያጠቡ እናቶች ናቸው፡፡ ከዚህም ሌላ 87 በመቶ ያህሉ ተፈናቃዮች ከማኅበረሰቡ ጋር ከ160,300 ተፈናቃዮች ጊዜያዊ በመጠለያ ማዕከላት ተጠልለው ይገኛሉ ብለዋል፡፡ በአፋር ክልል የሚገኙ አብዛኞቹ ተፈናቃዮች በ11 መጠለያዎች ተጠልለው እንዳሉና በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል 193,040፣ በኦሮሚያ 559,122 ተፈናቃዮች እንደሚኙና ለሁሉም ተፈናቃዮች ተገቢው ድጋፍ እየተሰጠና ድጋፉንም የማጠናከር ሥራ እየተከናወነ እንደሆነ ነው የተናገሩት፡፡ 

‹‹በጤና መሠረተ ልማት ላይ የደረሰው የጉዳት መጠን በጥልቀት በሚያሳይ መልኩ ዝርዝር ዳሰሳ በሒደት ላይ ቢሆንም፣ እስካሁን ባለው መረጃ ቀላል የማይባሉ ተቋማት ዝርፊያና ውድመት ደርሶባቸዋል፡፡ በርካታ የጤና ባለሙያዎች ሥራቸውን ለማቆም ተገደዋል፡፡ በተያያዘም የድንገተኛ ሕክምና አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩት አምቡላንሶችም ተዘርፈዋል፣ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ከአገልግሎት ውጪ ሆነዋል፤›› ብለዋል፡፡

እንደ ጤና ሚኒስትር ገለጻ በአማራ ክልል በሚገኙ አምስት (በሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ በሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ በዋግ ህምራ) ዞኖች 20 ሆስፒታሎች፣ 277 ጤና ጣቢያዎች፣ 1162 ጤና ኬላዎች በአሁኑ ጊዜ አገልግሎት እየሰጡ አይደሉም፡፡ ከእነዚህም ውስጥ 14 ሆስፒታሎች፣ 153 ጤና ጣቢያዎችና 642 ጤና ኬላዎች የተዘረፉ ወይም የተጎዱ ናቸው፡፡ ከዚህም ሌላ በአፋር አንድ ሆስፒታል፣ አሥር ጤና ጣቢያዎችና 38 ጤና ኬላዎች አገልግሎት ያቋረጡ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ስምንት ጤና ጣቢያዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...