Monday, July 22, 2024

[የመንግሥት ሥራ አስፈጻሚ ተቋማት የሩብ ዓመት የሥራ እንቅስቃሴን አስመልክቶ በመንግሥት ተቋማት ክትትል ኮሚቴ የተዘጋጀ ሪፖርት ለክቡር ሚኒስትሩ እየቀረበ ነው] 

 

 • ክቡር ሚኒስትር በሪፖርቱ ለማሳየት እንደተሞከረው የመንግሥት ሥራ አስፈጻሚዎች የሚመሯቸው ተቋማት የዓላማ አንድነት ይጎድላቸዋልእርስ በእርስ ተናበው ሲሠሩም አይታይም። 
 • ሪፖርቱ የዚህ ችግር መገለጫዎችን ለምን አላካተተም?
 • አሁን የቀረበው የተጨመቀ ሪፖርት ስለሆነ ነው እንጂ ዝርዝሩን የያዘው ዋና ሪፖርት ላይ ተካቷል።
 • ማሳያዎቹ ምንድን ናቸው? እስኪ የተወሰኑትን ጥቀሱልኝ?
 • መልካም ክቡር ሚኒስትር፣ ለምሳሌ አንድ ተቋም ከሰሞኑ ለሥራ ጉብኝት በሚል ምክንያት ከተለያዩ ተቋማት የተወጣጡ ልዑካንን ይዞ ወደ ወጭ ያደረገው ጉዞ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የሌለውና ለጉዞው የወጣውም ወጪ በመንግሥት የውጭ ምንዛሪ ላይ እንደ መቀለድ የሚቆጠር ነው። 
 • የውጭ ምንዛሪ ላይ መቀለድ?
 • አዎ ክቡር ሚኒስትር፣ በውጭ ምንዛሪ ላይ ከመቀለድ ባለፈም የሰሜኑ ቀውስ በመንግሥት ላይ ትልቅ ወጪ እያስከተለ መሆኑን እንኳን ያላጤነ ብከነት ነው። 
 • ይህንን ያላችሁት በምን ምክንያት ነው? ለምንድነው ጉዞው መደረግ አልነበረበትም ያላችሁት?
 • ምክንያቱም በኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ፍላጎቱን ከገለጸ ኩባንያ ጋር ለሁለተኛ ጊዜ ስምምነት ከመፈራረም ውጪ ወደ ውጭ በተደረገው ጉዞ የተገኘ ነገር የለም።
 • ለሁለተኛ ጊዜ ምን ማለት ነው?
 • ይህ ኩባንያ የማዳበሪያ ፋብሪካውን በድሬዳዋ ለመገንባት ከኢትዮጵያ መንግሥት ስምምነት የፈጸመው ከአራት ዓመት በፊት ነበር። ወደ ትግበራ እንዲገባ ማድረግ እንጂ በድጋሚ ለመፈራረም ወደ ውጭ መጓዝ ጥቅም የለውም። 
 • ወደ ውጭ የሄደው ልዑክ ምን ይላል? ድጋሚ ለመፈራረም ለምን ፈለገ?
 • የመጀመርያው ስምምነት ከለውጡ በፊት የተፈረመ በመሆኑ ነው የሚሉት ልዑኩን ይዘው የሄዱት ባለሥልጣን።
 • ከለውጡ በፊት የነበረው መንግሥት የሚል የተደረገውን ስምምነት ስለሚጠራጠሩት ይሆን?
 • እንደዚያ እንዳይባል ከለውጡ በፊት የነበረውን ስምምነትም የፈረሙት አኚሁ ባለሥልጣን ነበሩ።
 • ምን?
 • እንደዚያ ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • ይህ ጉዳይ ለብቻው ምርመራ ይደረግበት። ሌላ ማሳያ ካለ ቀጥሉ።
 • ሌላው መጠቀስ ያለበት ጉዳይ በቅርቡ ማኅበረሰቡን ጭምር ያበሳጨው የአንድ የመንግሥት ተቋም ድርጊት ነው።
 • ምንድነው?
 • ይህ ተቋም በመዲናዋ የሚገኙ ሕንፃዎችን አስውባለሁ ብሎ በጡብ ድንጋዮች የተገነቡ ጥንታዊ ሕንፃዎችን ገጽታ የሚያበላሽ ቀለም በመቀባት በመንግሥት ላይ አላስፈላጊ ወጪ አስከትሏል።
 • ተቋሙ ይህንን ከማድረጉ በፊት ለምን ከባለሙያዎች ጋር አልተወያየም ነበር?
 • በዚህ ጉዳይ ላይ ኃላፊው ተጠይቀው ስህተት መፈጸማቸውን አምነዋል። 
 • ምን አሉ?
 • የተበላሹትን ሕንፃዎች ቀለም ለማስለቀቅና ወደ ቀድሞ ገጽታቸው ለመመለስ ከባለሙያዎች ጋር ምክክር እያደረግን ነውማስለቀቂያ ኬሚካል እንዲገዛም በጀት ተመድቧል ብለዋል።
 • ሌላ የቀረ ምን አለ
 • አንድም መሬት ፆም አያድርም ተብሎ የተጀመረው እንቅስቃሴም ዓላማው አፈንግጦ ታይቷል።
 • እንዴት?
 • ፆማቸውን ማደር የለባቸውም ተብለው የተለዩ የአዲስ አበባ ክፍት ቦታዎች ለግለሰቦች ተሰጥተው በርካታ መጋዘኖች ተገንብተው ተገኝተዋል። 
 • መጋዘኖቹ ለምን ዓላማ የሚውሉ ናቸው?
 • ክቡር ሚኒስትር መጋዘኖቹ ተገነቡ እንጂ ፆማቸውን ናቸው። 
 • ታዲያ ለምን ተገነቡ?
 • ለመያዣ ይመስላል፡፡
 • ምን ለመያዝ?
 • መቼም ፆም ለመያዝ አይሆንም። 
 • ምን ማለትህ ነው?
 • ግልጽ የሆነ መሬት ወረራ ነው ለማለት ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡ 
 • ይህንን የፈቀዱ ኃላፊዎቹ ምን ይላሉ?
 • ቦታዎቹ ፆማቸውን እንዳያድሩ በተባለው መሠረት የተላለፉ ናቸው ነው የሚሉት። 
 • አሁን ይኼ ምን ይባላል?
 • አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም፡፡
 • ግድ የለም ከመስከረም 24 በኋላ ይነቃል!

[ክቡር ሚኒስትሩ የውጭ ግንኙነት ዘርፉን አስመልክቶ እየተሰጠ ስላለው ሥልጠናና ሪፎርም ሪፖርት እየተቀበሉ ነው]

 • የውጭ ግንኙነት ዘርፍ ላይ የተዘጋጀው ሥልጠና እንዴት እየተካሄደ እንደሆነ  ገመገማችሁ?
 • አንዳንድ ያስተዋልናቸው ችግሮች ቢኖሩም፣ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • የተስተዋሉት ችግሮች ምንድን ናቸው?
 • በሥልጠናው ላይ ጎምቱ የሚባሉ ዲፕሎማቶች አለመገኘታቸውን አስተውለናል።
 • ለምን?
 • ጥሪውን እንዳልተቀበሉ ነው የተረዳነው። 
 • አልገባኝም?
 • ጥሪውን ተቀብለው ወደ አገር አልተመለሱም፣ በተመደቡበት አገር ቀርተዋል፡፡
 • ጥሩ ዋና ዕቅዳችን ተሳክቷል፣ ተዋቸው።
 • ምን ነበር ዕቅዱ ክቡር ሚኒስትር?
 • ወደ አገር እንዲመለሱ የተጠሩበት አንዱ ጉዳይ ዕቅዳቸውን ማክሸፍ ነበር።
 • ምን ነበር ዕቅዳቸው?
 • ኃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው እንደለቀቁ እያስወሩ በተመደቡበት አገር ጥገኝነት መጠየቅ ነበር ዕቅዳቸው።
 • ለምን? ምን ይጠቀማሉ?
 • የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለመፈጸም።
 • የምን ተልዕኮ?
 • የውጭ መዋቅራችንን በማፍረስ መንግሥት እየፈረሰ ነው የሚል ስሜት መፍጠር!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፍተኛ ትርፍ ቢያገኝም የውጭ ምንዛሪ ገቢው ቅናሽ ማሳየቱ ተጠቆመ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2016 የሒሳብ ዓመት ያሰባሰበው የውጭ ምንዛሪ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ የቅርብ ወዳጃቸው ከሆነች አንድ ባለሀብት የተደወለላቸውን ስልክ አንስተው በኮሪደር ልማቱ ላይ የምታቀርበውን ቅሬታ እየሰሙ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እኔ የኮሪደር ልማቱ ላይ ተቃውሞም ሆነ ጥላቻ እንደሌለኝ የሚያውቁ ይመስለኛል? በዚህ እንኳን አትታሚም።  የእውነቴን ነው ክቡር ሚኒስትር። አውቃለሁ ስልሽ? ለኮሪደር ልማቱ አዋጡ ሲባልም ያለማመንታት አምስት ሚሊዮን...

[ክቡር ሚኒስትሩ በችግኝ ተከላ ፕሮግራም ላይ ሳይገኝ ከቀረው አንድ የተቋማቸው ባልደረባ የሆነ የተቃዋሚ ፓርቲ አባልን አስጠርተው እያናገሩ ነው]

ለምንድነው በዚህ አገራዊ ፋይዳ ባለው ፕሮግራም ላይ ያልተገኘኸው? ክቡር ሚኒስትር ህሊናዬ አልፈቀደልኝም። መቃወምና መተቸት ብቻ ውጤት የሚያመጣ መስልዎህ ከሆነ ተሳስተሃል። አልተሳሳትኩም ክቡር ሚኒስትር? ቆይ የመጀመሪያ ዓመት የችግኝ ተከላ...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላነጋግርህ የፈለኩት ክቡር ሚኒስትር፡፡ እርስዎማ ቀጠሮ መያዝ አያስፈልግዎትም፣ ምን ገጠመዎት? እኔማ ምን ይገጥመኛል አንተኑ ልጠይቅህ እንጂ? ምን? እውነት ለመናገር የማየው ነገር አሳስቦኛል፡፡ ይንገሩኝ...