Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

ከሚከተሉት እንስሳት ፖለቲከኞች የትኛውን ይመርጣሉ?

ትኩስ ፅሁፎች

አንበሳ – በአስፈሪ መልኩና አስጠሊታ የሆነ ጠረን ባለው ግሳቱ ባካባቢው በሚገኙ ፍጡራን ላይ ፍርኃትን በማሳደር ከበረቴን ያገኘ ሲሆን፣ ባለቤቱ ሁሉንም ሥፍራዎች እንድትሠራ፣ እንድታስብና ፖሊሲዎቹን እንድትፈጽም ፈቃድ የሰጠ ፍጡር ነው፡፡ የንግድ ምልክቱንና ሎጎውን በሚገባ በማስተዋወቁ ገንዘብ በቀላሉ የሚያስገኝለት ሆኗል፡፡ ብዙውን ጊዜ በጅቦች የሚጻፍለትን የምረጡኝ ዘመቻ ንግግር ይጠቀማል፡፡

ሚዷቋ – ግርማ ሞገስና ውበትን የተላበሰችው ትላልቅ ቡናማ ዓይኖች ያሏት ሚዳቋ ከፍና ዝቅ ባለ ደረጃ የሚገኙ ምርጥ ፖለቲከኞች ጓደኛ ነች፡፡ በወንድ አንበሶች የምትደነቀውና በሴት አናብስት የምትታደነው እንስሳ ምቾት ባላቸው፣ ሞቃታማና ከፍተኛ ሹመት ባለባቸው ቦታዎች ልትገኝ ችላለች፡፡

ዝሆን – ባንዳንዶች ዘንድ የተከበረው ይህ እንስሳ ወፍራም ቆዳ ያለውና በንዴት ጥቃት የማድረስ አቅም ያለው፣ በጊንዲላ ካምፖች የሚሠራ፣ ልጆችን በጀርባው የሚሸከም፣ በራሱና በተቀናቃኞቹ ላይ ውኃና ጭቃ ጅራፉን የሚረጭና ኦቾሎኒ መብላት የሚወድ ነው፡፡ ይኼ ሁሉ ጥንካሬ እያለው ታዲያ ትናንሽ በራሪ ነፍሳት ሳይቀር የሚያጨናንቁት ነው፡፡

ፈረስ – ከጥንት ጀምሮ የሰው ልጅ እውነተኛ ወዳጅ የሆነው ፈረስ አሁን ይግልቢያ ንጉሥ ነው፡፡ ንግሥናው ግን እምብዛም ገንዘብ አያስገኝለትም፡፡ መፈለግና ጠቃሚ መሆኑ እንዲታወቅለት ይፈልጋል፡፡ ካለ እርሱ ዘመቻ መሄድ አይቻልም፡፡ በልቡ ወደ ሰረገላ ወይም ጋሪ መጎተት ሥራው መመለስ ይፈልጋል፡፡ ነገር ግን ካሮት ከተቀለበ ምንጊዜም መፈክሮችን ተሸክሞ ቢዞር ቅር አይለውም፡፡

ድመቶች – እጅግ በጣም ራስ ወዳድ የሆኑት ድመቶች የራሳቸው የሆነውን የሚያውቁና ለነርሱ ቀሪው ሁሉ ትርጉም የሌላቸው ናቸው፡፡ ሕይወታቸውን ለማሻሻል የማያደርጉት ነገርና የማይፈነቅሉት ድንጋይ የሌለ ሲሆን፣ ሥር ነቀል ለውጦችን በሚደረጉ ጊዜ በቀላ የሚረበሹ፣ የሚይዘና የሚጨብጡት የሚጠፋቸው ናቸው፡፡ በመካከለኛው መደብ መራጮች ተለቅ ባለ የሲኒ ማስቀመጫ ትኩስ ወተት በቀላል ሊገዙ ይችላሉ፡፡

ውሾች – ቻይ፣ ንቁ፣ ቀናተኞችና አስፈላጊ ሲሆን ቁጡና አደገኛ እንዲሁም ጭራቸውን እየቆሉ በመለማመጥ የሰው ልጅ ምርጥ ጓደኛ የመሆን ክብር ተጎናጽፈዋል፡፡ በተፈጥሮ የሽያጭ ሠራተኞች በመሆናቸው የማግባባት ሥራን ለመፈጸምና ማመቻቸት እንዲሁም ተቃዋሚን አነፍንፎ የማግኘት ፀጋን የታደሉ ናቸው፡፡ እምብዛም በጮሌነታቸው የማይታወቁት እኒህ እንስሳት አብዛኛውን ጊዜ የምርጫ ዘመቻ ሥራ አስኪያጆች ይሆናሉ፡፡

ቺምፓዚ (ሰው የሚመስል ዝንጆሮ) – በፖለቲካ ጠቃሚ መሣሪያ ቢሆንም ይህን ዝንጆሮ የትውልድ ዝርያዎቹ ወይም ቢጤዎቹ ምን እንደሚፈልጉ አይገባውም፡፡ አንደኛ የወረርሽኝ ተባዮችን የመሸከም ሙያ አለው፡፡ አንበሳ ያለውን ሁሉ የሚፈጽምም ነው፡፡

የበረዶ ድብ – በርጋታውና በብቸኝነቱ የሚደሰተው ይህ ድብ ብዙዎችን የሚያስቀና ሕይወትና በሕይወት የመቀጠል ስትራቴጂዎችን አዳብሯል፡፡ ረዥም ሰዓቶችን በተመስጦ በማሳለፍ የኢኮኖሚ ጽንሰ ሐሳቦችን አዳብሮች ጥቅም ላይ እንዲውሉ የሚያግባባና ሐሳቦቹ ውጤታማ ባይሆኑ ኃላፊነትን የማይቀበል ነው፡፡ ይህ ሐሳብ አፍላቂ ጭንቅላት ፈጽሞ ወደ ፖሊሲ ሥራ እንዲቀርብ ሊቀድለት አይገባም፡፡ ነገሮችን በተግባር መተርጎም ምን ማለት እንደሆነ ሊገባው አይችልም፡፡

* * *

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች