Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

በድንቃ ድንቅ መዝገብ የተመዘገቡት ባለ107 ዓመቶቹ መንትዮች

ትኩስ ፅሁፎች

ጊነስ የዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ዕድሜያቸው 107 ዓመታት 300 ቀናት የተሻገረውን ሁለት ጃፓናውያን መንትዮች ‹‹በሕይወት ያሉ አዛውንት መንትዮች›› ሲል መመዝገቡን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በዘገባው እንደተጠቀሰው፣ ኡሜኖ ሱሚያማ እና ኩሜ ኮዳማ ከዚህ ቀደም ኪን ናሪታ እና ጂን ካኒ በተሰኙ ጃፓናውያን ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን ሰብረዋል። ኡሜኖ እና ኩሜን የሚያውቋቸው ሰዎች ተግባቢዎችና ማኅበራዊ ሕይወትን የሚወዱ መሆናቸውን ይናገራሉ።

እ.ኤ.አ. ጥቅምት 5 ቀን 1913 በሾዶሺማ ደሴት የተወለዱትን ሁለቱን እህትማማቾች መመዝገቡን ጊነስ ይፋ ያደረገው መስከረም 10 ቀን 2014 ዓ.ም. በዋለውና በጃፓን ብሔራዊ በዓል በሆነው የአዛውንቶች ቀን ላይ ነው።

መንትዮቹ ከነሐሴ 25 ቀን 2013 ዓ.ም. (ሴብቴምበር 1 ቀን 2021) ጀምሮ የክብረ ወሰኑ ባለቤት በመሆናቸው ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።

የቢቢሲ ዘገባ አክሎ እንደገለጸው፣ የቀድሞው የክብረ ወሰኑ ባለቤቶች ኪን እና ጂን 107 ዓመታትና 175 ቀናት ክብረ ወሰኑን ይዘው ቢቆዩም፣ ኪን  በጥር 2000፣ በቀጣዩ ዓመት ደግሞ ጂን ሕይወታቸው አልፏል።

ፎቶ፡ ቢቢሲ

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች