Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊከሮሽ ሃሻና ወደ ዕንቁጣጣሽ

ከሮሽ ሃሻና ወደ ዕንቁጣጣሽ

ቀን:

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመታቸውን መስከረም 1 ቀን 2014 ጀምረዋል፡፡ በባህላዊና በሃይማኖታዊ መንገድ ሁሉም በየፊናው አክብሮታል፡፡

በፀሓይና ጨረቃ ጥምር አቆጣጠር የሚቆጥሩት ቤተ እስራኤላውያን ‹‹ሮሽ ሃሻናህ›› ብለው የሚጠሩትን የዓመት መባቻቸውን ጳጉሜን 2 ቀን 2013 ሲያከብሩ ቲሽሪ (የጨረቃ ጥቅምት 1) 5782 ዓመተ ፍጥረት በማለት ነው፡፡

በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩት ቤተ እስራኤሎች በየምኩራቦቻቸው በመገኘት በዓሉ ቀንደ መለከት (ሼፋር) በመንፋት አክብረውታል፡፡

ኢትዮጵያውያን ቤተ እስራኤሎች አሮጌውን 5781 ዓመትን ሸኝተው፣ አዲሱን ዓመት 5782 ዓመተ ዓለምን ከሰኞ ምሽት (ጳጉሜን 1 ቀን 2013) እስከ ጳጉሜን 3 ድረስ በማክበር ነው የተቀበሉት፡፡ በዕብራይስጥ ‹‹ሮሽ ሃሻናህ›› በግእዝ ‹‹ርእሰ ዓመት›› በአማርኛ የዓመት መነሻ፣ ራስ ይባላል፡፡ ‹‹ሠረቀ ብርሃን›› (የብርሃን መውጣት) በመባል የሚታወቀው የአይሁድ አዲስ ዓመት ቲሽሪ 1 ቀን (የጨረቃ ጥቅምት 1 ቀን) ሼፋር (ቀንደ መለከት) የሚነፋበት ነው፡፡

በሮሻ ሃሻና ብርሃን ሠረቀ በተለይ ከሚባሉ ምግቦች ማር፣ ፖም የዓሣ ራስ፣ ቴምር፣ ካሮት ይገኙበታል፡፡ ዶቼቬሌ የነጋገራቸው የቤተ እስራኤላውያን የጥናትና ምርምር ማዕከል አባል አቶ መስፍን የምግቦቹን አንድምታ ገልጸውታል፡፡

tender

‹‹እነዚህ ምግቦች በዓውደ ዓመት የሚበሉት ለምሳሌ የአሣ ራስ፣ ራስ እንጂ እግር አይደለንም ለማለት፣ ማር መጭው ሕይወት ፈጣሪ እንደማር እንዲያጣፍጠው፣ ፖም ብዙ ፍሬዎች ስላለው ሕይወታችን እንደ ፖም ፍሬ እንዲያበዛና እንደ ማር እንዲጣፍጥ፣ ቴምር ጠንካራ ስለሆነ ጥንካሬን ለመመኘት፣ ካሮት ደግሞ አምላክ መልካም ፍርድን እንዲያስቀምጥ ለመመኘት ነው።››

መስከረም 1 ቀን የገባውን አዲስ ዓመት አስመልክቶ የመልካም ምኞት መልዕክት ካስተላለፉት የውጭ አገር መሪዎች መካከል ፕሬዚዳንት ባይደን ይገኙበታል፡፡

የፕሬዚዳንት ባይደን መልዕክት

‹‹ለኢትዮጵያና ለኤርትራ ህዝብ እንዲሁም በመቶ ሺዎች የምትቆጠሩ የኢትዮጵያና የኤርትራ ውርስ ያላችሁ አሜሪካዊያንን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ ዕንቁጣጣሽን ለምታከብሩ ሁሉ ጂልና እኔ የላቀ ምኞታችንንና መልካም አዲስ ዓመት እንመኝላችኋለን›› ሲሉ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በራሳቸውና በባለቤታቸው ስም መልዕክት ማስተላለፋቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

‹‹ለዕንቁጣጣሽ በዓል የፕሬዚዳንት ጆዜፍ አር ባይደን ጁኒየር መልዕክት››   በሚል ርዕስ በዋይት ሐውስ ቤተ መንግሥት ድረ ገጽ ላይ በወጣው መልዕክታቸው፣ ‹‹ኢትዮጵያዊያን አሜሪካዊያንና ኤርትራዊያን አሜሪካዊያን በመላ ዩናይትድ ስቴትስ ያሉ ማኅበረሰቦችን በማበልፀግ በአገራችን የየዕለት ሕይወት እያንዳንዷ ገፅታ ላይ ቁልፍ ናችሁ›› ማለታቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

‹‹ኮቪድ 19 ካደረሰው መጎዳትና ማጣት ጋር ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ግጭት ቤተሰቦቻችሁንና የምትወድዷቸውን ሁሉ እየጎዳ መሆኑን አውቃለሁ፤›› ያሉት ፕሬዚዳንት ባይደን ኢትዮጵያ ውስጥ በሲቪሎች ላይ እየደረሰ ነው ያሉት ጥቃት በጥልቅ እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል።

አፍሪካ ቀንድ ውስጥ ያሉ ግጭቶች ሁሉ ወደ ሰላማዊ መፍትሔ እንዲያመሩ አስተዳደራቸው በመላ አካባቢው ካሉ አጋሮች ጋር የነቃ የዲፕሎማሲ ጥረት እያደረገ መሆኑንም ባይደን አስታውቀዋል።

ፕሬዚዳንቱ በዚሁ የአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸው፣ ‹‹ታላቋና ኅብረ ስብጥሯ ኢትዮጵያ አሁን የተደቀኑባትን የመከፋፈል አደጋዎች እንደምታሸንፍና በድርድር የሚደረስበትን ተኩስ ማቆም ጨምሮ እየተካሄደ ላለው ግጭት መፍትሔ እንደምታበጅ እናምናለን፤›› ብለዋል ።

በአማርኛ ቃላት “መልካም አዲስ ዓመት” ያሉት ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በዓሉን ለሚያከብሩ ሁሉ “ይህ ዓመት ሰላምና ዕርቅ የሚወርድበት በመላ ኢትዮጵያና ኤርትራ እንዲሁም በመላው ዓለም፣ ቤተሰቦችና ማኅበረሰቦች ፈውስ የሚያገኙበት እንዲሆን እጸልያለሁ” ብለዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...