Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበአንድ ሳምንት ውስጥ በኮቪድ-19 ሕይወታቸውን ያጡት ቁጥር ወደ 89 ከፍ አለ

በአንድ ሳምንት ውስጥ በኮቪድ-19 ሕይወታቸውን ያጡት ቁጥር ወደ 89 ከፍ አለ

ቀን:

  • ከ15 እስከ 24 ዓመት ዕድሜ ክልል የሞት መጠን እየጨመረ መጥቷል

በተለያዩ አገሮች ለተከሰተው ሦስተኛው የኮቪድ-19 ማዕበል እንደ ዋና ምክንያት የሚጠቀሰው ኮቪድ-19 ራሱን ወደ ተለያዩ አዳዲስ የቫይረስ ዓይነቶች መቀየሩ ነው፡፡ ከእነዚህም መካከል በተለይም ‹‹ዴልታ›› የሚባለው የቫይረስ ዓይነት መሠራጨቱ ሲሆን፣ ይህ የዴልታ ቫይረስ በኢትዮጵያ መኖሩን ለመለየት የሚያስችል የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡

የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጽጌረዳ ክፍሌ (ዶ/ር) ነሐሴ 25 ቀን 2013 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፣ ‹አልፋ› እና ‹ቤታ› የተባሉ የቫይረስ ዓይነቶች በአገሪቱ መኖራቸው በላቦራቶሪ ቢረጋገጥም፣ አስፈሪው የዴልታ ቫይረስ መኖሩን ለማረጋገጥ ሥራዎች እየተተገበሩ ናቸው፡፡

እንደ ዋና ዳይሬክተሯ ማብራሪያ፣ በአሁኑ ጊዜ ያለው የኮቪድ-19 አገራዊ ሁኔታን በተመለከተ፣ በኮቪድ-19 የመያዝ ምጣኔ ከስድስት ሳምንታት በፊት ዝቅተኛ የነበረ ሲሆን፣ 1.6 በመቶ ሆኖ እንደተመዘገበና ነገር ግን አሁን በተያዘው ሳምንት ቁጥሩ በመጨመር በአማካይ ወደ 16.5 በመቶ ከፍ ብሏል፡፡

 ሰባት ሳምንት በኋላ ወደ ሕሙማን ክፍል የሚገቡ ሕሙማን ቁጥር ከፍ ብሏል፡፡ ይኼውም ከሰባት ሳምንት በፊት 180 ግለሰቦች ፅኑሙማን ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው የነበረ ሲሆን፣ አሁን ግን ቁጥሩ በመጨመር 602 ግለሰቦች ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም 180 ሰዎች መካከል 11 የሚሆኑት ሰውራሽ አጋዥ የመተንፈሻ መሣሪያ ይፈልጉ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሳምንት ግን ወደ 82 ግለሰቦች ማደጉን ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

 በኮቪድ-19 ሕይወታቸውን የሚያጡ ግለሰቦችም ስድስት ሳምንታት በፊት 11 የተመዘገበ ሲሆን፣ በአሁኑ ሳምንት ግን ወደ 89 ከፍ ብሏል፡፡ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ከሰባት ሳምንታት በፊት 487 የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሳምንት 10,058 ደርሷል፡፡  ከሳምንታት በፊት በኮቪድ-19 ምክንያት ተመዝግቦ የነበረው ሞት 85 በመቶ በላይ የሚሆኑት 45 ዓመትድሜ ያላቸው ሰዎች ሲሆኑ፣ አሁን ባለው ወቅታዊ መረጃ ግን 15 እስከ 24 ዕድሜ ክልል ያሉትን ወይም ሁሉንም የዕድሜ ክልሎችን ያካተተ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

በመሆኑም በሆስፒታሎች የአስተኝቶ ማከሚያ ክፍሎች፣ አጋዥ የመተንፈሻ መሣሪያ እጥረት እያጋጠመ፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከዕለት ወደ ዕለት በከፍተኛ ደረጃ ከመሠራጨቱም በላይ ሰብዓዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ችግሮችን እያስከተለ እንደሚገኝ ነው ዋና ዳይሬክተሯ የተናገሩት፡፡

በዚህም የተነሳ የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከልና የሚያስከትለውን ሞት ለማስቆም የሚከተሉትን የመከላከያ ዘዴዎችን መተግበር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው፣ ከዘዴዎቹም መካከል ለመጪው የአዲስ ዓመትና ሌሎች ሕዝባዊናይማኖታዊ በዓላት የሚፈጠሩ መሰባሰቦችን ማስቀረት፣ ሁሉም ተቋማት ደንበኞቻቸውን የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶችን እንዲተገብሩ ማድረግ፣ የኮቪድ-19 ምልክቶች ሲታዩ ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ ምርመራ ማካሄድና የኮቪድ-19 ክትባትን መከተብ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

ከዚህም ሌላ በበዓል ወቅት ለዕርድ የምንጠቀምባቸውን ማንኛውንም ቁሳቁሶች ንፅህናቸውን እንዲጠበቁ ማድረግና ንክኪዎችን መቀነስለግብይት ከቤት ውጪ ስንንቀሳቀስ ማስክ ማድረግ፣ የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘር መያዝ፣ በበዓል ወቅት ከሌሎች ሰዎች ጋር ያለንን ማኅበራዊ ግንኙነት መቀነስ፣ ያልበሰሉ የምግብ ተዋጽኦዎችን እንደ ጥሬ ሥጋ፣ ያልተፈላ ወተትና ሌሎችን ከመመገብ መቆጠብ፣ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በመመርያ 803/2013 .ም. ላይ የተቀመጡ ድንጋጌዎችን ተግባራዊ ማድረግ ከመላከያ ዘዴዎች ተጠቃሾች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡  

እንደ ጽጌሬዳ ክፍሌ (ዶ/ር) ማብራሪያ፣ በዓለማችን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ ሰብዓዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ አድርሷል፡፡ ይህም ተፅዕኖ ለሚቀጥሉትመታት እንደሚቀጥልና በተለይ ጉዳቱ በታዳጊ አገሮች ላይ የከፋ ሊሆን እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

ወረርሽኙ በዓለም ላይ ከተከሰተ ጀምሮ በአገር ደረጃ ሁሉን አቀፍ የተቀናጀና ጠንካራ የመከላከል፣ የቁጥጥርና ምላሽራዎች በትኩረት ተግባራዊ በመደረጋቸው የሰው ሞት ቁጥርና አገራዊ ቀውስ ከነበሩ ትንበያዎች አንፃር በእጅጉ መቀነስ ተችሏል፡፡ ለእነዚህ ውጤቶች መገኘት መንግሥትና ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለወረርሽኙ የሰጡት ትኩረትና የነበራቸው ቁርጠኝነት፣ ከፍተኛ ቅንጅትና የኅብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎና ርብርብ ዋነኛ ምክንያቶች መሆናቸውንም ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

ሆኖም ካለፉት ስድስት ወራት ወዲህ በወረርሽኙ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነስ ጋር ተያይዞ፣ በሁሉም ባለድርሻ አካላት የተሰጠው ትኩረት እየቀነሰ መምጣት፣ ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ወጥቶ የነበረው መመርያ 30/2013 ሲጣስ መቆየቱ፣ በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ይታዩ የነበሩ ጠንካራ የመከላከያ ዘዴዎች ትግበራ እጅጉን መቀነሱ፣ መመርያውን ያላገናዘቡ ስብሰባዎች፣ ሥልጠናዎች፣ የምርቃት ፕሮግራሞች፣ በተጨናነቀ መልኩ አገልግሎት የሚሰጡ ምግብ ቤቶች ለበሽታው መሠራጨት ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥሩ ነው ዋና ዳይሬክተሩ የገለጹት፡፡

 ካፊቴሪያዎች፣ የመዝናኛ ቦታዎችና የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫዎች ከፍተኛ ቁጥር ያለውዝብ የሚሳተፍባቸው ሃይማኖታዊና ሕዝባዊ የአደባባይ በዓላት፣ ሠልፎች፣ ስፖርታዊና ማኅበራዊ ክንውኖች፣ እንደ ለቅሶ፣ ሠርግና ሌሎች ማኅበራዊነ ሥርዓቶች ኮቪድ-19 ወረርሽኝ የሌለ እስኪመስል ድረስ እየተከናወኑ መሆናቸው፣ የማስክ አጠቃቀም እየቀነሰ መምጣትና ቸልተኝነት ለበሽታው መሠራጨት ምቹ ሁኔታዎች መሆናቸውን ነው ያመለከቱት፡፡

በሌላ ዜና ኅብረተሰቡ በሕገ ወጥ መንገድ ከሚቀርቡ የኮቪድ-19 ክትባቶችም ሆነ መድኃኒቶች ራሱን መጠበቅ እንዳለበት የጤና ሚኒስቴር ማሳሰቢያ ሰጥቷል። የኮቪድ-19 ክትባቶች ለኅብረተሰቡ በመንግሥታዊ ጤና ተቋማት ብቻ በነፃ የሚሰጡ መሆኑን አውቆ ከሕገ ወጦች ራሱን መጠበቅ እንዳለበት ማሳሰቢያ የሰጠው ሚኒስቴሩ፣ ሰሞኑን በአራዳ ክፍለ ከተማ፣ ደጃች ውቤ ሠፈር አካባቢ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባቶችን በሕገ ወጥ መንገድ ሲገበያዩ የነበሩ በአዲስ አበባ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን አስታውሷል፡፡

በሕገ ወጥ መንገድ ክትባቶቹን ለመገበያየት መሞከር በአያያዙና በአወሳሰዱ ላይ እክል የሚፈጥር በመሆኑና ጉዳቱ የከፋ ስለሚሆን ኅብረተሰቡ ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ፣ ሕገወጦችንም በመከታተል ማጋለጥ ይኖርበታል ያለው የጤና ሚኒስቴር፣ ክትባቱ ለወደፊት በግል ጤና ተቋማት መሰጠት ሲጀመር አስቀድሞ እንደሚያሳውቅ ገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...