Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊ​​​​​​​ያገረሸው የኮቪድ- 19 ሥርጭት የመጨመር ፍጥነቱ አሳሳቢ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

​​​​​​​ያገረሸው የኮቪድ- 19 ሥርጭት የመጨመር ፍጥነቱ አሳሳቢ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

ቀን:

  • በአዲስ አበባ በአንድ ቀን 839 ሰዎች ተይዘዋል

በኢትዮጵያ ባለፉት ሦስት ሳምንታት የኮቪድ-19 ሥርጭትአሳሳቢ ፍጥነት እየጨመረ መምጣቱን የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) በኮቪድ-19 ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በሰጡት  መግለጫ አስታውቀዋል።

ባለፉት ሦስት ሳምንታት የወረርሽኙ ሥርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የገለጹት ሚኒስትሯ፣ በሦስት ሳምንታት ውስጥኮቪድ-19 ናሙና ከሰጡ ሰዎች መካከል ቫይረሱ የተገኘባቸው በሳምንታዊ ምጣኔ ከነበረው 2.8 ወደ 7.4 በመቶ ከፍ ማለቱን ተናግረዋል።

በሽታው የሚገኝባቸው አማካይ ቁጥር በሳምንት ከነበረበት 831 በአራት እጥፍ በመጨመር ወደ 3,302 ከፍ ማለቱን ጠቁመዋል፡፡

ወደ ሕክምና ማዕከላት የሚገቡ ሕሙማን ቁጥር መጨመሩን፣ በፅኑ የታመሙ በነሐሴ 6 ቀን 2013 ዓ.ም. 353 መድረሳቸውን አክለዋል፡፡

ሥርጭቱ ይጨምር እንጂ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል የሚጠቀሙ ሰዎች ምጣኔ እየቀነሰ መጥቷል፡፡ እንደ ሚኒስትሯ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል የመጠቀም ሁኔታ በአዲስ አበባ 59 በመቶ ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ ከተሞች ደግሞ ወደ 20 በመቶ ወርዷል፡፡

የጥንቃቄ ጉድለቱ በሦስተኛው ዙር የወረርሽኙ ሥርጭት ወቅት ሌሎች አገሮች ያስተናገዱትን ከፍተኛ ጉዳት ዓይነት በኢትዮጵያ እንዲከሰት ምክንያት ስለሚሆን ኅብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መክረዋል፡፡

የኮቪድ-19 ክትባትን አስመልክተው እስካሁን 2,254,270 ዜጎች የመጀመሪያ ዙር እንዲሁም 300 ሺሕ በላይ ሁለተኛውን ዙር ክትባት አግኝተዋል ብለዋል።

በአዲስ አበባ ካለው ከፍተኛ የወረርሽኙ ሥርጭት አንፃር ዕድሜያቸው 35 በላይ፣ በክልሎች ደግሞ ዕድሜያቸው 55 ዓመት በላይ ለሆኑ እንዲሁም ተጓዳኝ የጤና ችግር ያለባቸውና ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ዜጎች ክትባቱ ይሰጣል ተብሏል።

የሥራ ባህሪያቸው ከበርካታ ሰዎች ጋር ለሚያገናኛቸው ሠራተኞችም እንዲሁ ክትባቱን በስፋት ተደራሽ ለማድረግ መታቀዱንበአዲስ አበባነሐሴ 7 በክልሎች ደግሞ ከነሐሴ 14 ቀን ጀምሮ እንደሚሰጥ ተናግረዋል። የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ ስደተኞችና የጎዳና ተዳዳሪዎችም የጤና ቢሮዎች በሚያመቻቹት መርሐ ግብር መሠረት ክትባቱን እንደሚሰጣቸው ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ አሳሳቢ ገጽታ

የኮቪድ-19 ሥርጭት ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ከሚያሳየው አንዱ በአዲስ አበባ በአንድ ቀን ብቻ 839 ግለሰቦች በቫይረሱ መያዛቸው መረጋገጡ ነው፡፡

በኮቪድ-19 ቫይረስ የተያዙ ግለሰቦች ቁጥር 100 ቀናት በኋላ ከፍተኛ ሆኖ በተመዘገበበት የአገሪቱ ክፍሎች 7,518 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 882 ግለሰቦች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። ይህ ማለት ናሙና ከሰጡ 100 ግለሰቦች 12 (12%) የኮቪድ-19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ ይህ ደግሞ 90 ቀናት በኋላ በኮቪድ-19 የመያዝ ምጣኔ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።

በተለይ አዲስ አበባ ነሐሴ 4 ቀን ከፍተኛውን በኮቪድ-19 የተያዙ ግለሰቦች ቁጥር ያስመዘገበች ሲሆን 6,211 ግለሰቦች ምርመራ ተደርጎላቸው 839 ግለሰቦች ላይ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። ናሙና ከሰጡ 100 ግለሰቦች 14 (14%) የኮቪድ19 ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

      በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በዚህ ፍጥነት እጨመረ ከሄደ የአልጋ፣ ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሣሪያና ኦክስጂን እጥረት ሊያጋጥመን ስለሚችል፣ ኅብረተሰቡም ይኼንን በመገንዘብ አሁንም የኮቪድ-19 የመከላከያ መንገዶችን ማስክ በማድረግ፣ የእጅን ንጽህና በተደጋጋሚ በመጠበቅበየትኛውም ቦታ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ የኮቪድ-19 ክትባት በመከተብ የወረርሽኙን ሥርጭትና መዛመት እንዲቆጣጠር የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጥሪውን አቅርቧል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...