Monday, May 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

‹‹እኔ አዲስ አበባ በተገኘሁበት ቀን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሥራ ምክንያት ከአዲስ አበባ ውጪ ስለነበሩ በቅርብ ጊዜ አገኛቸዋለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ›› ሰማንታ ፓወር፣ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት ዋና ኃላፊ

የአሜሪካ መንግሥት ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት የሆነው ዩኤስኤአይዲ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት ሰማንታ ፓወር፣ ሰሞኑን በሱዳንና ኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት አድርገዋል። ለአራት ቀናት ከቆየው የሥራ ጉብኝታቸው ውስጥ ሦስቱን ቀናት በሱዳን ያሳለፉት ሰማንታ ፓወር፣ ከትግራይ የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን የሚገኙባቸውን የተለያዩ የስደተኛ ካምፖች ጎብኝተዋል፡፡ በሱዳን ያለውን የዴሞክራሲ ሽግግር በተመለከተም ከአገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር መክረዋል። የሱዳን ጉብኝታቸውን ሲያጠናቅቁም በካርቱም ለሚገኙ ለሱዳንናዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተው ነበር። በሱዳን በሰጡት መግለጫ በኢትዮጵያ ከትግራይ ክልል ቀውስ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ያነሱ ሲሆን፣ ከትግራይ ክልል የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የሚገኙባቸውን ካምፖችም እንደጎበኙ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት በሁመራ በኩል በንፁኃን ላይ ጭፍጨፋ መፈጸሙን የሕወሓት ኃይልና የፕሮፓጋንዳ አጋሮቹ ሐሰተኛ መረጃ እንደሚነዙ የደኅንነት መረጃዎች እንደ ደረሱት ሰማንታ ፓወር ለዚህ ጉብኝት ወደ ሱዳን ከመምጣቸው ሁለት ሳምንት ገደማ አስቀድሞ ይፋ አድርጎ የነበረ ሲሆን፣ ኃላፊዋ የሱዳን ጉብኝታቸውን በጀመሩበት ቀንም እጃቸውን ታስረው የተገደሉ ሰዎች አስከሬኖች በኢትዮጵያናሱዳን ድንበር ወንዝ ውስጥ ተጥለው መገኘታቸውን ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች መዘገባቸው ይታወሳል። ሰማንታ ፓወር የሱዳን ጉብኝታቸውን አጠናቀው በሰጡት መግለጫ ካነሷቸው ጉዳዮች አንዱ ከትግራይ ክልል የተፈናቀሉ ስደተኞች የደረሰባቸውን ኢሰብዓዊ ድርጊት የተመለከተ ነበር። በሱዳን በሚገኙ የስደኛ ማቆያ ካምፖች ተጠልለው የሚገኙ በበርካታ ሺዎች የሚቆጠሩ ከትግራይ ክልል የተፈናቀሉ ስደተኞችን እንዳነጋገሩ፣ ከአንድ ስደተኛ በሰሙት እማኝነትም ዘግናኝ ግድያዎች በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል መፈጸማቸውን እንደተረዱ ገልጸዋል። በሱዳን የስድተኛ መጠለያ ካገኟት አንድ እንስት አንደበትም፣ በስደት ላይ የነበሩ ሲቪል ሰዎች ተይዘው እጃቸው ወደኋላ እየታሰረ ግድያ እንደተፈጸመባቸው በዓይኗ ማየቷን እንደነገረቻቸውና በኋላም እጃቸው ወደኋላ የታሰሩ አስከሬኖች መገኘታቸውን የሚገልጹ የዜና ዘገባዎችን ተመልክተው፣ እንስቷ ስደተኛ የነገረቻቸው ግድያ ሊሆን እንደሚችል እንዳሰቡ ገልጸዋል።  የዩኤስአይዲ ዋና አስተዳዳሪዋ ሰማንታ ፓወር የሱዳን ጉብኝታቸውን አጠናቀው ማክሰኞ ሐምሌ 27 ቀን 2013 ዓ.ም. አዲስ አበባ ደርሰው፣  በነበራቸው የአንድ ቀን ጉብኝትም ከሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ጋር  በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ቀውስ ላይ መክረዋል።  በዚሁ ዕለት ጉብኝታቸውን ሲያጠናቅቁም ለአገር ውስጥና በአዲስ አበባ ለሚገኙ የውጭ ጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተው ነበር። ሰማንታ ፓወር ከሚዲያዎች ጋር ባደረጉት የአንድ ሰዓት ገደማ ቆይታ ሪፖርተር ታድሞ ነበር። ኃላፊዋ በመጀመርያ በአንድ ቀን የኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ወቅት የተመለከቱትንና ከዚሁ ጋር የተገናኙ ጉዳዮችን የተመለከተ ገለጻ ለጋዜጠኞች አድርገዋል። ‹‹የረዥም ጊዜ አጋራችንና የአካባቢው ወሳኝ ወደሆነችው አገር መምጣቴ ለእኔ ትልቅ ነገር ነው። ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ የመጣሁበት ጊዜ ሩቅ አልነበረም፡፡ እ.ኤ.አ. 2016 በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአሜሪካ አምባሳደር ሳለሁ በቀድሞ የኢትዮጵያ መንግሥት እስር ላይ የነበሩስት እስረኞችን ጨምሮ፣ በመላው ዓለም ኢፍትሐዊ በሆነ መንገድ እስር ላይ የሚገኙ ሴት የፖለቲካ እስረኞች እንዲለቀቁ ዘመቻ በጀመርኩበት ወቅት ነበር። ዛሬ ግን እ.ኤ.አ. 2016 ለውጥን ተከትሎ እነዚህን ሦስት ሴት የፖለቲካ እስረኞች ጨምሮ፣ በአሥር ሺሕ የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞች ነፃ የሆኑባት ኢትዮጵያ መጥቻለሁ። ቢሆንም ዛሬም ብሩህ ቀን አይደለም፡፡ ይልቁንም ለዘጠኝ ወራት በዘለቀው ግጭት ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ ደርሶ ̀5̀.2 ሚሊዮን ያህል ሰዎች እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ። የአሜሪካ መንግሥት ለተጎጂዎች ሰብዓዊርዳታ ማድረስ  በሚቻልበትና እንዲሁም የፖለቲካ እስረኞች እንዲለቀቁ መንግሥትን እያግባባ ቢሆንምነገሮች አልተቀየሩም። የኢትዮጵያዝብ እንዲያውቀው የምፈልገው ነገር አንደኛውን ተዋጊ ወገን ለመደገፍ ሳይሆንመርህን መሠረት አድርገን ከእናንተና ከመንግሥታችሁ ጋር መሥራትና ችግሩን መፍታት እንደምንፈልግ ነው። መርሆቹም ለውስጣዊ ግጭት ወታደራዊ ዕርምጃ መፍትሔ እንደማይሆንና ሁሉም ተዋጊ ኃይሎች አፋጣኝ የተኩስ አቁም አድርገው ስለርቀ ሰላም፣ እንዲሁም ወታደሮችና የሚሊሺያይሎች ከአጎራባች ክልል ስለማስወጣት ንግግር ወደ መጀመር መግባት አለባቸው የሚሉ ናቸው። በሁለት ወገኖች የተጀመረውን ግጭት አሜሪካ በከፍተኛጋት ነው የምትመለከተው ሲሆን የሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ኃይሎች ወደ አጎራባች ክልሎች መስፋፋትን ተከትሎ በግርድፉ እንደምንገምተው 76 ሺሕ የሚሆኑ ከአፋር ክልል፣ 150 ሺሕ የሚሆኑ ደግሞ ከአማራ ክልል ተፈናቅለዋል። ሌሎቹ መርሆች የሰብዓዊ ዕርዳታራተኞች በነፃነት ሥራቸውን እንዲሠሩ መሆን አለበት፡፡ የማስፈራራትም ሆነ የጥቃትላማ መሆን አይገባቸውም፡፡ ከፍተኛ አደጋ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ለመርዳትናይወት ለመታደግ ይችሉ ዘንድ የዕርዳታ መንገዶች ክፍት ሊሆኑላቸው ይገባል የሚሉት ናቸው። ዛሬ ጠዋት ከመዲናዋ ብዙም የማይርቅ አንድ የዩኤስአይዲ ማዕከልን ጎብኝቻለሁ። መጋዘኖቹ አገልግሎት ላይ መዋል ባልቻሉ በስንዴ፣ በምስርናአተር፣ እንዲሁም በጭነት መኪናዎች የተሞሉ ነበሩ። ምክንያቱም እነዚህን የምግብ ዕርዳታዎች በአስቸኳይ ማግኘት ያለባቸው የትግራይ ክልል ነዋሪዎች ለማድረስ ባለመቻሉ ነው።ርዳታውን ለተረጂዎች ለማድረስ መንግሥት ያስቀመጠውን የተራዘመነ ሥርዓት ማለፍ የሚጠይቅናርዳታውን ለማጓጓዝ በተፈቀደው ብቸኛው የአፋር ክልል ኮሪደርም ውጊያ በመኖሩ አልተሳካም። አሁን አጽንኦት የምሰጠው የተኩስ አቁም እንዲደረግና መንገዶች ሁሉ ለሰብዓዊርዳታ ክፍት መሆን አለባቸው የሚለውን መርህ ነው። ማንነታቸውና ድጋፋቸው ለማንም ይሁን ለማን አሜሪካ ለኢትዮጵያውያን ታስባለች፣ ትጨነቃለች። ዛሬ የተወሰኑ የጤናው ዘርፍ የአገር ውስጥ አጋሮቻችንን የመጎብኘትድልም የነበረኝ ሲሆን፣ ለዓመታት በተከናወኑ ሥራዎች በኅብረተሰብ ጤና በኩል ስለተመዘገበ አበረታች ውጤት አብራርተውልኛል። ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አመራርና ለአሜሪካ ድጋፍ ምሥጋና ይሁንና ወባን በመከላከል ረገድ ከፍተኛ መሻሻል ታይቷል፤›› ሲሉ ሰማንታ ፓወር ከላይ የተቀመጠውን ገለጻ ካደረጉ በኋላ፣ ሪፖርተርን ጨምሮ መግለጫውን እንዲታደሙ ከተጋበዙ ጋዜጠኞች ለቀረቡ ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን እንደሚከተለው ተሰናድቷል። 

ጥያቄ፡- ስለመግለጫው አመሠግናለሁ። በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሕወሓትን ለመግለጽ ‹‹አረም››፣ ‹‹ካንሰር›› እና ‹‹በሽታ›› የሚሉ ቃላትን በመጠቀማቸው እየተወቀሱ ነው። ባለፈው ሳምንት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዘር ማጥፋት መከላከል ልዩ አማካሪ የእነዚህ ቃላት አጠቃቀም እንዳሳሰባቸውና ነገሩ በቀጣይ በትግራይም ተጨማሪ፣ እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎችም ጥቃቶች ሊፈጸሙ የሚችሉበትድል ከመኖሩ ጋር አገናኝተውታል። የዘር ማጥፋትን በተመለከተ ከፍተኛ ኃላፊ እንደመሆንዎ የእነዚህን ዓይነት የቃላት አጠቃቀም መንግሥትን ከሚመራ አካል ሲሰሙ ምን ያስባሉ? ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይን የማግኘትድል ቢኖርዎ ምን ይሏቸው ነበር?

ሰማንታ ፓወር፡- ከሰላም ሚኒስትሯ ጋር በተገናኘሁበት ወቅት ይህንኑ ጉዳይ የሚመለከቱ ነጥቦችን አንስቼ የነበረ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩንም ባገኛቸው ኖሮ ይህ በእርግጠኝነት አንዱ የማነሳው ጉዳይ ነበር። የተጠቀሱት ግጭት ቀስቃሽ የሆኑ ትርክቶችና ሰብዓዊነትን የሚያወርዱ አገላለጾች፣ በተለይም በተለያዩ የበይነ መረብ አውታሮችና ኅትመቶች ላይ ልታገኟቸው የምትችሏቸው በዕርዳታራተኞች ላይ ያነጣጠሩ አደገኛ ንግግሮችም አሳሳቢ ናቸው። ከፍተኛ ችግር ውስጥ ላሉ ሰዎች ምግብና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን ለማቅረብ ከመሞከር በቀር ምንም ያላደረጉ የዕርዳታራተኞች ላይ የተፈጸሙ አሰቃቂ ጥቃቶችን ተመልክተናል። እናም የተገለጸውይነት ሰብዓዊነትን የሚያወርድ አገላለጽና ትርክት በተደጋጋሚ ታሪክ እንደታየው ውጥረትን በማካረር፣ ዘርን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን ወደ ማስከተል ያመራል። ስለዚህም አሜሪካ ጥሪ እያቀረበች ያለችው የተኩስ አቁም ተደርጎ ወደ ውይይት እንዲገባ ነው። እነዚህ አደገኛ ትርክቶች ተጠናክረው በቀጠሉ ቁጥር ወደ ድርድር ጠረጴዛ መምጣት እጅግ ከባድ ይሆናል። ዓላማው ምንም ይሁን ምን ለኅብረተሰቡ እንድታሳስቡ የምላችሁ እነዚህን አደገኛ የጥላቻ አገላለጾችና ትርክቶችሚጠቀሙና የሚቀበሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች፣ ግጭት ሊያጭሩናይልን በእጃቸው አድርገው ወደ ጥቃት ዕርምጃዎች ሊገቡ መቻላቸውን ነው። እንደማስበው የሰላም መምጣት ሁላችንም የምንጋራው ግብ ነው፡፡ እናም ቃላት ወሳኝ ናቸው። እጅግ አስፈላጊ የሆነው ነገር የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ እየከረረ የመጣውን መወነጃጀላቸውን አቁመው፣ ሁሉን አቀፍ የሆነ ሰላም ለማምጣትና የንፁኃንን ሥቃይ ለማስቆም ወሳኝ የሆነው ውይይት ላይ ቢያተኩሩ ነው።

ጥያቄ፡- ጥያቄዬ እየተዋጉ ካሉይሎች ጋር የተደረገ ንግግርን ይመለከታል። ካገኟቸው የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር የተነጋገሩት ነገር አለሌላው ደግሞ  በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ዕርዳታ ማድረስን ይመለከታል። እንደ እርስዎ ግምገማ ሰብዓዊ ዕርዳታ እንዳይደርስ መንገድ የዘጋው ማን ነው?

ሰማንታ ፓወር፡- እንደምታውቀው ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፊልትማን ከሌሎች ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመሆን እዚህ መሬት ላይ ተዋናይ ከሆኑ ቡድኖች ጋር ተከታታይ ንግግሮችን በማድረግ፣ እነዚህይሎች ወደ ሰላም እንዲመጡ ያላሰለሰ ጥረት እያደረጉ ነው። ከሰላም ሚኒስትሯ ጋር በነበረኝ ውይይት ዓላማዬ የነበረው በእሳቸው የሥልጣን ወሰን በሆነ ደረጃ የሰብዓዊ ፍላጎት በእጅጉ እየጨመረ መምጣቱንና ቀናት በሄዱ ቁጥር ነገሩ እየከፋ መሆኑን መወያየት ነበር። የውይይታችን ማጠንጠኛም ይኼው ነበር፡፡ እናም እንዳያችሁት በጉዳዩ የአሜሪካ አቋም አፋጣኝ የተኩስ አቁም፣ የሚመለከታቸውይሎች በወታደራዊይል ከያዟቸው ቦታዎች እንዲወጡ መሆኑን አጽንኦት ሰጥቼ ተናግሬያለሁ፡፡ ይህ አቋማችን ግልጽና ይፋዊ መሆኑን እንደገና አረጋግጣለሁ። ሁኔታዎቹ ተሟልተውና ተደርገው ማየት አለባችሁ። እነዚህ ነገሮች ውይይቶች ውጤት እንዲያመጡ ወሳኝነት አላቸው። ነገር ግን በፖለቲካው በኩል የልዩ መልዕክተኛችንን ሚና፣ እንዲሁም ዕርዳታ ማድረስ አሁንም እጅግ አሳሳቢ ከመሆኑ አንፃር ትኩረቴ የነበረው የጥያቄው ሁለተኛ ክፍል ላይ ነበር። እናም የአኃዝ ማስረጃ እጠቅሳለሁ። ምናልባትም ሰምታችሁ ሊሆን እንደሚችለውጁላይ አጋማሽ ላይ ተመድ በወቅቱ የነበረውን የዕዳርታ ፍላጎት ለሟሟላት በየሳምንቱ 500 እስከ 600 ተሽከርካሪዎች ዕርዳታ ትግራይ መግባት ነበረበት። የዛሬ መረጃ የለኝም፣ ግን ከሁለት ቀናት በፊት 153 ዕርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ትግራይ መግባት ችለዋል፡፡ እናም ከሁለት ቀናት በፊት (ከጁላይ አጋማሽ እስከ ኦገስት 2 ቀን ድረስ) እንደ ተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከሆነ ያስፈልግ የነበረው የ1,500 ተሽከርካሪ ጭነት ነበር፡፡ ግን ትግራይ መድረስ የቻለው 153 ማለትም ከሚያስፈልገው አሥር በመቶ ያህሉ ብቻ ነበር ማለት ነው። እናም እንደማስበው የአሠራር ለውጦች እንዳሉ ዓይተናል።

ለምሳሌ መሟላት ያለባቸው ሰነዶችን፣ ጊዜንና ፈቃድን በሚመለከት ማስተካከያዎች የተደረጉ ቢሆንም መጓተቶች አሉ፡፡ ልዩ ምግቦችና ሌሎች የዕርዳታቃዎች ማጓጓዝ አለመቻላችን ሲታይ፣ ተስፋ ያደረግነውን ያህል ለውጥና ማስተካከያ አለመደረጉን እንገነዘባለን። እናም ይህ ከሚኒስትሯ ጋር ያደረግኩት አንዱ ወሳኝ ጉዳይ ነበር። ዩኤስኤአይዲ በጤናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው ሥራ፣ በተለይም በኮቪድናግብርና የተወያየንባቸው ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ነበሩ። እናም አሁንም ዕርዳታ ለማድረስ ነገሮች ቀላል እንጂ ከባድ እንዳይሆኑ፣ መንገዶች ክፍት እንዲሆኑና ድጋፍ የሚሹ እናቶችን ለመድረስ ጭነታቸውን ሞልተው ዝግጁ የሆኑ ተሽከርካሪዎች ትግራይ መድረስ እንዲችሉ መንግሥትን እንጠይቃለን። እስኪ አስቡት ወላጆች ምግብ ያልበሉ ልጆቻችሁ ሲመለከቷችሁ የሚሰማችሁን አስቡት። እናም የምለው በአጋሮቻችን በኩል እነዚህንፃናት መመገብ እንችላለን፡፡ ይህም የሚሆነው ግን ምግብ ትግራይ መድረስ እስከቻለ ድረስ ብቻ ነው። አሁን ይህንን ምግብ ወደ ትግራይ ለማድረስ መንገዶች ክፍት ይሆናሉ ብዬ በፅኑ አምናለሁ። ሌላ ማለት የምፈልገው ነገር ቢኖር የሕወሓት ወታደራዊይል እየተንቀሳቀሰመሆኑ፣ እነዚህ ዕርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ሊያልፉ በሚችሉባቸው አካባቢዎች እንቅስቃሴው ካለ ዕርዳታውን ማዳረስ አሁንም ይደናቀፋል። ስለዚህ የመንገዶች ደኅንነት መረጋገጥ አለበት። ስለዚህም የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ እጅግ አሥጊ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ንፁኃን ዜጎች ዕርዳታ ያገኙ ዘንድ ቅድሚያ ይሰጡ ዘንድ እጠይቃለሁ።

ጥያቄ፡- በሥራ ዘመንዎ ኢፍትሐዊነትን በመቃወምና በመታገል ስመ ጥር ነዎት። ነገር ግን ብዙዎች በተለይም ኢትዮጵያውያን በሕወሓት የተፈጸሙ ጥቃቶችን ዓይተው እንዳላየ እንዳለፉ ይሰማቸዋል። ይህ የሚሰነዘርብዎ ወቀሳ መሠረት ያለው ወቀሳ ነው ይላሉ? እዚህ ላይ ምን አስተያየት አለዎት? ከዘጠኝ ወራት በፊት ኖቬምበር ላይ ሕወሓት በመከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ካወገዙት መካከል አሜሪካ ቀዳሚ ነበረች። የአሜሪካ መንግሥት አሁንም ወገንተኝነቱ ከእውነት፣ ከሰላምና ከፍትሕ ጋር እንደሆነ እየገለጸ ቢሆንም ብዙኃን ኢትዮጵያውያን ለሕወሓት በመወገን መጥፎ አቋም በመያዙ በባይደን አስተዳደር የመከዳት ስሜት አድሮባቸዋል። ስለዚህስ ምን መልስ አለዎት? እርስዎ ሕወሓት ፀብ አጫሪ ነው፣ በተለይም ከአጎራባች አማራ ክልል ጋር ባለው ሁኔታ ብለው ያምናሉ?

ሰማንታ ፓወር፡- በመጨረሻ ስለተጠየቀው ጥያቄ በመክፈቻ ንግግሬና በሰጠሁት አስተያየት፣ የሕወሓት ወታደራዊ እንቅስቃሴ ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ ገልጫለሁ። የሕወሓት ወታደራዊ መስፋፋት በአማራናአፋር ክልሎች ያስከተለው በአሥር ሺዎች የሚገመቱ የንፁኃን መጠነ ሰፊ መፈናቀል እንዳሳሰበን፣ በመክፈቻ ንግግሬ ላይ አስታውቄያለሁ፡፡ የዚህ ዓይነቱ ወታደራዊ ጥቃት በአፋጣኝ ቆሞ የሚመለከታቸው አካላት ወደ ንግግር መግባታቸው እጅግ አስፈላጊ ነው። የመጀመሪያውን ጥያቄ በሚመለከት ስለምመራው ድርጅት ዩኤስኤአይዲ ልናገር መጀመርያ። ድርጅቱ ከኢትዮጵያውያን ጋር ሥራ የሚሠራው ስለብሔራቸውና ስለፖለቲካ ምንም ሳይጠይቅ ነው። ይልቁንም ጥያቄው ስላለው የትምህርት፣ የግብርና ዕቅድ፣ ዲጅታላይዜሽን፣ አስተዳደር፣ የሕግ የበላይነትና ሲቪል ማኅበራት፣ እንዲሁም ስለቲቢና ወባ መድኃኒቶች ነው። ሕይወቴን ሙሉ ወዳጅነት ላለኝ የኢትዮጵያን ሕዝብ የሚረዳ የዚህ ድርጅት አካል በመሆኔ ክብር ይሰማኛል። እዚህ ላይ አንዳንድ ማስረጃዎችን ለማስቀመጥ ያህል ባለፈው ዓመት ብቻ አሜሪካ በዩኤስኤአይዲ በኩል  720 ሚሊዮን ዶላር የሰብዓዊ፣ እንዲሁም 340 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ የጤና ድጋፍን ጨምሮ ለኢትዮጵያዊያን ወዳጆቻችን አንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚሆን ድጋፍ አድርገናል። በትግራይ ብቻ ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያ ትልቁ የሰብዓዊ ድጋፍ ለጋሾች ነን።

እናም ከሰላም ሚኒስትሯ ጋር በሕወሓት ወታደራዊ እንቅስቃሴ ምክንያት የተፈናቀሉትን በምንረዳበት ሁኔታ ላይ ተነጋግሬአለሁ። ዩኤስኤአይዲና አጋሮቻችን የምንሠራው ይህንን ነው፡፡ ችግር ላይ ያሉ ንፁኃን ኢትዮጵያውያንን መርዳት እንፈልጋለን። በእርግጥም በሐሳብ ደረጃ ደግሞ የኢትዮጵያ ልማት ላይ ማተኮርና ዜጎቻችሁ ዕርዳታ የሚሹበት ሁኔታ እንዳይፈጠር እናስባለን። ከዕርዳታ ግንኙነት ወደ ንግድ ግንኙነት ለመሸጋገር የሚያስችሏችሁ ሁኔታዎች፣ ዕውቀትና ወጣት ኃይል አላችሁ። እኛ እንደ አድማስ የምንመለከተው ይህንን ነው። ነገር ግን ግጭቶች በመሀል እየገቡ ለኢኮኖሚ ልማት፣ ለግብርና መርሐ ግብሮች መዋል የነበረባቸው ድጋፎች ለሰብዓዊ ዕርዳታ እየዋሉ ነው። ሁሉም ድጋፋችን ሕዝባችሁ አጋርና ባለድርሻ የሚሆንበት ዘላቂ ኢንቨስትመንት ላይ እንዲሆን ነው የምንፈልገው። ሕወሓትን ለሚመለከተው ጥያቄ አንድ ገልጽ መሆን ያለበት ነገር ቢኖር፣ አሜሪካ ለሕወሓት አመራር የተኩስ አቁምና የፖለቲካ ድርድር ግጭቱን የማስቆም ብቸኛው አማራጭ እንደሆነ ማስገንዘባችንን ነው። በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ያለው ሕወሓትን ያለ ማመንና ጥላቻ መሠረቱ የሕወሓት 27 ዓመታት ሥርዓት እንደሆነም ገልጸንላቸዋል። እናም መጀመርያ ንግግሬ ላይ እንዳልኩት ይህ ጉዳይ በኦባማ አስተዳደር ወቅት በይፋና በግል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የግለሰቦች ክብርና ሰብዓዊ መብት እንዲረጋገጥ፣ እንዲሁም ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ እንዲደረግ፣ ሲቪል ማኅበራት በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ ምኅዳሩ እንዲሰፋ ስነጋገር ነበር። እናም በምሄድበት ሁሉ በሥራዬ ሁሌም አቋሜ የማይዋዥቅ ነው። ዛሬ ኢትዮጵያ መጥቼ ብዙዎችን በማግኘቴ አጋሮቻችንን እንዲሁም የመንግሥት ኃላፊዎችን በማግኘቴ ክብር ይሰማኛል። በማኅበራዊ ሚዲያ ከፍተኛ የሆነ የተዛባ መረጃ ፍሰት በመኖሩ፣ እዚህ በአካል ተገኝቼ አስፈላጊውን ንግግር ማድረጌ ወሳኝ ነው። እዚህ በዋሽንግተንም ያሉ ባልደረቦቼ እንደሚያደርጉት ምንም ዓይነት ወገንተኝነት ሳናሳይ የሰብዓዊ መብት፣ የዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ድጋፍ ሕግን መርህ አድርገን እነዚህን መርሆች ወደ ጎን ላሉ ወይም ለጣሱ ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ መርሆቹን እንዲያከብሩ ጥሪ ማድረጌን እቀጥላለሁ።  መንግሥትን የሚመራው አካል ሌላ ቢሆን ኖሮም ኢትዮጵያውያን ሰዎች አላስፈላጊ በሆነ ሁኔታ አደጋ ውስጥ እየወደቁና እየተሰቃዩ እያየሁ ዝም እንድል የሚፈልጉ አይመስለኝም። እናም እዚህ መምጣቴና መነጋገሬ መሬት ላይ ያሉ አጋሮቻችን የሰጡን ተጨባጭ መረጃዎች፣ በተለይም የዕርዳታ መስተላለፊያ መንገዶች መዘጋትን በሚመለከት ላይ የተመሠረቱ መሆናቸውን ነው። ሕወሓት መንገድ እየዘጋ ከሆነ ያን የመናገር ኃላፊነት አለብን፡፡ የአማራ ሚሊሺያ ንፁኃንን እየጎዳ ወይም መንገድ እየዘጋ ከሆነ ያንንም የመናጋር ኃላፊነት አለብን። የኤርትራ ኃይሎች አሁንም ትግራይ ውስጥ ካሉና ሰብዓዊ ጥቃቶችን እፈጸሙና የዕርዳታ ተሽከርካሪዎችን ዕቃ እያስወረዱ ከሆነ ይህንንም መናገር አለብን። እንደማምነው ይህ እውነቱን እንዳወቅን የምንገልጽበት ፍፁም ትክክለኛና ነፃ አቋማችን ነው።

ጥያቄ፡- ከትግራይ ባለሥልጣናት ወይም ከሕወሓት ሰዎች ጋር የመነጋገር ዕድል ነበር? ሌላው ጥያቄ ትርክቶችን ይመለከታል። ትርክቶችን ብቻም ሳይሆን በትገራይ ተወላጆች ላይ ማስፈራሪያዎችና እስራትም እየተፈጸሙ ነው። ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ሲገናኙ እነዚህን ለማንሳት ሞክረዋል? እንደሚመስለኝ ኢትዮጵያ ከመምጣትዎት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይን የማግኘት ዕቅድ ነበረዎት። ተሳካልዎት? ምን ነበር የውይይታችሁ ነጥቡ?

ሰማንታ ፓወር፡- እንደገና ለመግለጽ ይህ በጣም ውስን ጉብኝት ነው። ይህ የዩኤስኤአይዲ አስተዳዳሪ ሆኜ ያደረግኩት ሁለተኛው ጉብኝቴ መሆኑን ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ የመጀመሪያውን ጉዞዬን ወደ ኢትዮነጵያ ማድረጌ ለእኔ ትልቅ ነገር ነው። ከአገሪቱና ከሕዝቦቿ ጋር ያለን ግንኙነት ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ ማሳያም መሆኑም ላይ አጽንኦት መስጠት እፈልጋለሁ። ነገር ግን ይህ ጉብኝት አጭር ነው። በእርግጥ ወደ ትግራይ መሄድ አልቻልንም በዚህ ጉብኝት። ነገር ግን ቢያንስ የዕርዳታ ቁሳቁሶችን ያከማቸንበትና ዕርዳታ የተጫኑና ወደ ትግራይ ክልል ዕርዳታ ለማደረስ ዝግጁ ሆነው ያሉ ተሽከርካሪዎች ከሚገኙበት ሥፍራ ተገኝተን፣ እነዚህን የዕርዳታ ቁሳቁሶች የሚጭኑና የተሽከርካሪ ሾፌሮችን ማነጋገር ችለናል። ከኃላፊነቴ አንፃር በእነዚህ ድርጅቶች በኩል ያለውን ችግር መስማት መቻላችን ወሳኝ ነው ብዬ አምናለሁ። ብዙዎቹ ከትግራይ ክልል ውጪ የስልክ ወይም ሌላ ዓይነት ግንኙነት ማድረግ አልቻሉም፡፡ ብዙዎችም ሠራተኞቻቸውን መክፈል ወይም ጥሬ ገንዘብ ወደ አካባቢው ማድረስ አልቻሉም። በከፍተኛ ሁኔታ አጣብቂኝ ውስጥ ነው ያሉት። እንደምታውቁት ከጁላይ 8 ቀን ጀምሮ ተመድ ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ የሰብዓዊ ዕርዳታ በረራዎችን እንዲጀምር መንግሥት ፈቃድ መስጠቱን አስተላልፎ ነበር። ዕርዳታዎችን በተሽከርካሪ ማድረስን የሚያግዝ ስለሆነ ትልቅ ስምምነት ነበር። ነገር ግን ተመድ በሠራው ግምገማ ሰብዓዊ ድጋፉን ለማሳለጥ ይቻል ዘንድ፣ የሰው ኃይልና ሌሎች ነገሮችን ለማድረስ ዕለታዊ በረራዎች የግድ አስፈላጊ መሆናቸውን ተገነዘበ። የተመድ የሰብዓዊ ዕርዳታ ድርጅት እንዳለው መንግሥት ፈቃዱን ከሰጠ ጀምሮ እስካሁን ለሰው ኃይል በረራ ሁለት ይለፎችን ብቻ ነው ያገኘው። እናም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ሁለት በረራዎችና ሁለት ተሽከርካሪዎች ማለት ነው፣ ይህ ደግሞ በቂ አይደለም። እናም በጥቅሉ ጥያቄውን ስመልስ ትልቁ ትኩረቴ እነዚህ አስቸኳይ የሰብዓዊ ዕርዳታ ጉዳዮች ላይ ነበር።

ከኢትዮጵያ መንግሥት ያገኘሁት ማስተማመኛ መንግሥት ለንፁኃንትግራይ ተወላጆች ደኅንነትና አገልግሎት በፅኑ እንደሚሠራ ነው። እንደማስበው ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አስተላልፍ የነበረውም ነጥብ ይኸው ነው። ሰብዓዊ ዕርዳታ ላይ የሚሠሩ ሁሉ በትግራይ ለወራት የምግብ እጥረት መፈጠሩ እንዳሳሰባቻው የሰላም ሚኒስትሯ ለጠቅላይ ሚኒስተሩ መልዕክት እንደሚያስተላልፉም አረጋግጠውልኛል። በአንፃራዊ ሁኔታ ለሥራው አዲስ የሆንኩት እኔ እንኳ የችግሩን አሳሳቢነት ለወራት ሳስጠነቅቅ ነበር። እኛ ድጋፍ የምናደርግላቸው ድርጅቶች የራሳቸውን ነዳጅ እስከማደል ድረስ ከባድ ችግር ውስጥ ነበሩ። የትኛውን መርሐ ግብር አቋርጠን የትኞቹን ማስቀጠል አለብን የሚለውንም ማሰብ ነበረባቸው። ለምሳሌ ዛሬ እንደሰማነው ምናልባትም የትምህርት ፕሮግራሞችን ማስቀጠል ይችላሉ። ምክንያቱም የሰው ኃይል እዚያው ስላለና ወደ ትምህርት ቤቶቹ በእግር መጓዝ ስለሚችሉ። የሰው ኃይል ስል ትልቅ ልፋትና ግብዓት የሚጠይቀውን ነፍስ በማዳን ረገድ ትልቅ ሚና ያላቸውን ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች ማለቴ ነው። ይህ የነፍስ አድን ሥራ በከፍተኛ ሁኔታ  ረዥም ርቀት መጓዝንም ይጠይቃል። እስኪ ለራሳችሁ አስቡት ውስን በሆነ የነዳጅ መጠን ሁለት ማኅበረሰቦችን ማግኘት አለብኝ። ነገር ግን መንገድ ከተጨመረብኝ ለዚያ ዕለት የተመደበው ነዳጅ ተበላብኝ ማለት ነው። የዕርዳታ ሠራተኞች እንዲህ የግብዓት እጥረት ባለበት በዚህ መንገድ ሊሠሩ አይችሉም። ምንም የላቸውም ማለት ይቻላል። በዚህ ሳቢያ የሚጎዱት ደግሞ ንፁኃን፣ ወላጆችና አዛውንቶች፣ እንዲሁም መንቀሳቀስና መውጣት ያልቻሉ ሰዎች ናቸው። እናም ሚኒስትሯ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲያስተላልፉልኝ ያልኳቸው መልዕክቴ ይህ ነበር። እንደምታውቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ከተማ ውስጥ የሉም። እኛ ግን  በትግራይ ክልል እየተፈጸሙ ያሉ ግድያዎችና የዕርዳታ ሰዎች እየተገደሉ መሆናቸው አሳስቦናል። የእነዚህ ግድያዎች በገለልተኛ አካል መጣራት እጅግ አስፈላጊ ሲሆን፣ ሚኒስትሯ ይህንንም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚያደርሱ ቃል ገብተውልኛል።

ሁሉም የመንግሥት ባለሥልጣናት የዕርዳታ ሠራተኞች ኢትዮጵያውያንን እያገለገሉ እንደሆነ፣ ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ድምፃቸውን ማሰማት አለባቸው። በዚህ በአደገኛ ትርክቶች፣ ግጭትና ጥቃት ነገሮች ፅንፍ ለፅንፍ በሆኑበት ወቅት የባለሥልጣናት ባላቸው መንገድ ሁሉ ነገሮች እንዲረግቡ ድምፃቸውን ማሰማት በጣም ጠቃሚ ነው። ስለዚህምኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ድጋፋቸውን ዕርዳታ ለሚሹ በመስጠት መስዋዕትነትን እየከፈሉ ላሉ እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርቤያለሁ። እነዚህ ተረጂዎች ዘርተውአምርተው ለራሳቸው መሆን ይችሉ የነበሩ፣ ነገር ግን ይህን ማድረግ ያልቻሉ ናቸው። እናም ብዙዎቹ በሕይወታቸው ለመጀመርያ ጊዜ ራሳቸውን ከውጭ የሚመጣ ዕርዳታ ጥገኛ ሆኖ ያገኙ ናቸው። እናም እንደገና ለሁሉም ወገኖች በግልጽና በይፋ መናገር የምፈልገው፣ የዚህ አገር ሕዝብ ሁሌም የዕርዳታ ሠራተኞችን ገለልተኝነትና ነፃነት እንዲያከብር ነው። ይህ እጅግ እጅግ ጠቃሚ ነው። ስለትዕግሥታችሁ አመሠግናለሁ።

ተዛማጅ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች ለማግኘት

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች


ተዛማጅ ፅሁፎች

‹‹ግጭቶች በሰብዓዊ ዕርዳታ ሥራዎቻችን ላይ የሚያሳድሩትን አሉታዊ ተፅዕኖና እየተከሰተ ያለውን ሥቃይ እያየን ነው›› ሆላንደር ሆላንደር፣ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት የኢትዮጵያና የጂቡቲ ዋና...

ከበርካታ የአፍሪካ አገሮች መካከል ኢትዮጵያ ለአሜሪካ የቅርብ ወዳጅ እንደሆነች ይነገርላታል፡፡ ክፍለ ዘመንን የተሻገረው የሁለቱ አገሮች ግንኙነት ሰሞኑን ዲፕሎማቲክ ግንኙነት የጀመሩበትን 120ኛ ዓመት ክብረ በዓላቸውን...

‹‹በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚኖሩንን እንቅስቃሴዎች ሊያግዙ የሚችሉ ተቋማት ያስፈልጉናል›› ገመቹ ዋቅቶላ (ዶ/ር)፣ የአይ ካፒታል አፍሪካ ኢንስቲትዩት ዋና ሥራ አስፈጻሚ

የኢትዮጵያንና የምሥራቅ አፍሪካን የፋይናንስ ተቋማት መሠረት በማድረግ በየዓመቱ የሚካሄደው የምሥራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ጉባዔ፣ በበርካታ አጀንዳዎች አማካይነት በተለይ ለፖሊሲ አውጪዎች ግብዓቶችን ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ ከዚህ ጎን...

‹‹ኢትዮጵያ ብዙ ፈተና እየገጠማት ቢሆንም ከፈተናው ውስጥ ቀስ እያልን እንወጣለን ብዬ አስባለሁ›› ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር)፣ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር

ከጥቂት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ የመንግሥት ለውጥ መካሄዱን ተከትሎ  በቀደሙት ጊዜያት ከተቋማዊ ስሙ ባለፈ በሚያከናውናቸው ተግባራት፣ ተቋሙን ይመሩት በነበሩ ኮሚሽነሮች፣ እንዲሁም በአጠቃላይ ተቋማዊ ባህሪው ከአስፈጻሚው...