Saturday, April 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ወላጆች ለተመድ አቤቱታ አቀረቡ

በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ወላጆች ለተመድ አቤቱታ አቀረቡ

ቀን:

መንግሥት የአገር መከላከያ ሠራዊት ከትግራይ ክልል እንዲወጣ ካደረገ በኋላ፣ በክልሉ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ልጆቻቸው ባለመውጣታቸው ምክንያት የተጨነቁ በሺዎች የሚቆጠሩ ወላጆች፣ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) አቤቱታ አቀረቡ፡፡

በሺዎች የሚቆጠሩ የተማሪ ወላጆች ዓርብ ሐምሌ 16 ቀን 2013 ዓ.ም. ወደ ተመድ ጽሕፈት ቤት በመሄድ፣ ልጆቻቸውን ዓለም አቀፉ ተቋም እንዲመልስላቸው ተማፅነዋል፡፡

የተማሪ ወላጆች ወደ ተመድ ጽሕፈት ቤት ያመሩት ትግራይ ክልል በሚገኙ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ያለ ማንም ጠያቂና ያለ በቂ ምግብ አቅርቦት ተዘግቶባቸው የሚገኙ ተማሪዎችን ለማስወጣት፣ የተመድ የስደተኞች ድርጅት ጥረት እያደረገ መሆኑን መረጃ በማግኘታቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ይሁን እንጂ ዓርብ ሙሉ ቀን በተመድ ጽሕፈት ቤት በለቅሶና በጩኸት ‹‹ልጆቻችንን መልሱልን፣ ያለ ልጆቻን ሌላ ጥያቄ የለንም፣ በሒደት የሚባል ንግግር አንፈልግም፤›› በማለት ድምፃቸውን አሰምተዋል፡፡

የመከላከያ ሠራዊት ከትግራይ ክልል ለቆ ከወጣ በኋላ ለፌዴራል መንግሥት ክልሉን የፌዴራል መንግሥት እንደማይቆጣጠረውና ውሳኔው በክልሉ ውስጥ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን ዕጣ ፈንታ ያላማከለ እንደነበር ወላጆች ተናግረዋል፡፡

ልጃቸው በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ያለ ማንም ጠያቂ በቀን ሁለት ዳቦ እየበላ በሥጋት እንደሚኖር ልጃቸው እንደነገራቸው የገለጹት አንድ ወላጅ፣ ላለፉት በርካታ ሳምንታት በተሰበረ ልብና ሐዘን መሰንበታቸውን ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ የሚማር ልጃቸውን ከአንድ ወር በላይ ማግኘት እንዳልቻሉ ለሪፖርተር የገለጹት ወ/ሮ አንጓች አብርሃ፣ የተማሪዎችን ድምፅ መጥፋት ተከትሎ ወላጆች ለፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፣ ለፓርላማ፣ ለተመድ፣ ለቀይ መስቀል፣ ለሰላም ሚኒስቴር፣ ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርና ለበርካታ የግልና የመንግሥት ተቋማት አቤቱታ ያቀረቡ ቢሆንም አጥጋቢ መልስ እንዳላገኙ ተናግረዋል፡፡

በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ ተማሪዎች በፌዴራል መንግሥትና በትግራይ ክልል በተከሰተ ግጭት ሳቢያ ያለ ምንም ማስጠንቀቂያ በጦርነት መሀል ያለ ጠያቂ አደጋ ውስጥ መሆናቸው እየታወቀ፣ የፌዴራል መንግሥትም ሆነ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ዕርዳታ አድራጊ ድርጅቶች ዝምታ እንዳሳዘናቸው የገለጹት ደግሞ መሠረት ተጫነ የተባሉ ወላጅ ናቸው፡፡

መንግሥት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በጠየቀው መሠረት ነዳጅ በማቅረብና በ9.3 ሚሊዮን ብር ወጭ 63 አውቶብሶች ቢከራይም፣ ተቋሙ ‹‹ልጆቹን እንመልሳለን›› ከማለት በቀር አጥጋቢ የሆነ መረጃ ሊሰጣቸው እንዳልቻለ የገለጹት ብርሃኑ ጥግነህ የተባሉ ልጃቸው በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የሚገኝ ወላጅ ናቸው፡፡

የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ሐምሌ 13 ቀን 2013 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ዩኒቨርሲቲው በባንክ የነበረው ገንዘብ እንዳይንቀሳቀስ መታገዱን፣ የ2014 ዓ.ም. በጀት እንዳልተለቀቀ በመግለጽ ለተማሪዎች አገልግሎት ማቅረብና ማስቀጠል እንደማይችል በመጥቀስ፣ ከሐምሌ 20 ቀን 2013 ዓ.ም. በኋላ ከምግብ ጋር በተያያዘ በተማሪዎቹ ላይ ለሚደርስ ችግር ኃላፊነት እንደማይወስድ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ሪፖርተር ጉዳዩን አስመልክቶ የተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽንና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ኃላፊዎችን በተደጋጋሚ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡     

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...