Friday, May 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየቀድሞ የአዲስ አበባ ከንቲባ ዘውዴ ተክሉ (1926 – 2013)

የቀድሞ የአዲስ አበባ ከንቲባ ዘውዴ ተክሉ (1926 – 2013)

ቀን:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ1973 – 1981 ዓ.ም. ድረስ በከንቲባነት ያገለገሉት ኢንጂነር ዘውዴ ተክሉ በ87 ዓመታቸው ማረፋቸው ተገልጿል፡፡

ኢንጂነር ዘውዴ በስምንት ዓመት የከንቲባነት ጉዟቸው ካከናወኗቸው ተግባራት በጉልህ የሚነሱ፣ የአዲስ አበባ ከተማ መቶኛ ዓመት ኢዮቤልዩን በከፍተኛ ደረጃ በማስከበር፣ የአዲስ አበባ ሙዚየምን በማደራጀትና በማሟላት፣ የእንጦጦ ቅዱስ ራጉኤል መደብር ኤልያስ መንገድን በማሠራት፣ የሐምሌ 19 መናፈሻ፣ የየካና ሌሎች ዘጠኝ የመናፈሻ ቦታዎችን ለሕዝብ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረጋቸው ነው፡፡

የምሕንድስና፣ የአርክቴክቸርና የከተማ ፕላን ትምህርታቸውን የተከታተሉት ከንቲባ ዘውዴ ከ1961 ዓ.ም. ጀምሮ ለ22 ዓመታት በተለያየ መንግሥታዊ ተቋማት በሙያቸው በከፍተኛ ኃላፊነት ማገልገላቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት የተኘገነው መረጃ ያመለክታል፡፡

- Advertisement -

ገጸ ታሪካቸው እንደሚሳየው፣ በ1981 .ም. በማዕከላዊ ፕላንና ዘመቻ መመርያ ውስጥ በምክትል ኮሚሽነርነት የፊዚካል ፕላኒንግ መምርያ ኃላፊ በመሆን ለሁለት ዓመታት ያገለገሉት ከንቲባ ዘውዴ፣ በግንቦት 1983 .ም. የተደረገውን የመንግሥት ለውጥ ተከትሎ ለሁለት ዓመታት እስር ቆይተው ፍርድ ቤት በመቅረብ በነፃ ተለቀዋል፡፡

ከንቲባ ዘውዴ ተክሉ በጡረታ ላይ በነበሩበት ወቅትም ቢሆን አገርንና ወገንን ከማገልገል ባለመቆጠብ 1997 .ም. የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ፎርም ሲመሠረት የፎረሙ ሰብሳቢ በመሆን እስከ ዕለተ ሞታቸው አገልግለዋል፡፡

ከዚህም ሌላ የሙስና ወንጀል ለመከታተል የተቋቋመው ዓለም አቀፍ የግልጽነት (Transparency International) መሥራችና አባል በመሆን ሠርተዋል፡፡ እንደዚሁም የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መታሰቢያ ድርጅት በምሥረታው በመሳተፍና በአባልነት አገልግለዋል፡፡

ማኅበረሰቡን ለረጅም ጊዜ በማገልገል የሚታወቁት ከንቲባ ዘውዴ ተክሉ፣ ለረጅም ጊዜ በሠሯቸው ማኅበረሰብ ተኮር ተግባራት 2007 ዓ.ም.  የበጎ ሰው ሽልማት ተሰጥቷቸዋል፡፡

ከአባታቸው ከባሻ ተክሉ አመኑና ከእናታቸው ከወ/ አስካለ ደገፉ በሐረርጌ ጠቅላይ ግዛት  በሐረር ዙሪያ አውራጃ በኤጀርሳ ጎሮ ወረዳ ገንደጋራ በሚባል አካባቢ መጋቢት 7 ቀን 1926 .ም.ተወለዱት ከንቲባ ዘውዴ ተክሉ፣ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በ87 ዓመታት ያረፉት ሐምሌ 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ነው፡፡ ሥርዓተ ቀብራቸው ሐምሌ 13 ቀን በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል፡፡

ነፍስ ኄር ዘውዴ ተክሉ ባለትዳርና ሦስት ሴት ልጆችንና ስድስት የልጅ ልጅ  ለማየት የታደሉ ነበሩ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...