Sunday, May 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናሙስና በሦስት የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ በከፍተኛ ሁኔታ መኖሩ ተጠቆመ

ሙስና በሦስት የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ በከፍተኛ ሁኔታ መኖሩ ተጠቆመ

ቀን:

በኢትዮጵያ በሦስት የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ሙስና በከፍተኛ ሁኔታ መኖሩን፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከትግራይ ክልል ውጪ በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች የተደረገ ጥናት አመለከተ፡፡

የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ሦስተኛ አገር አቀፍ የሙስና ቅኝት ጥናትና የፀረ ሙስና ፖሊሲና ስትራቴጂ ላይ ያተኮረ ዓውደ ጥናት ማክሰኞ ሐምሌ 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ባካሄደበት ወቅት እንደተገለጸው ኮንስትራክሽን ዘርፍ፣ በመሬት አስተዳዳር፣ገቢዎችና ጉምሩክፍተኛ የሙስና ተጋላጭነት አለ፡፡

ኮሚሽኑ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ፣ በኢትዮጵያ የሙስና ሁኔታ በተመለከተ ከትግራይ ክልል ውጪ ባለፉት ሁለት ዓመታት በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች ከተለያዩ የሕይወት መስክ ላይ የሚገኙ 6,627 ሰዎችን በጥናቱ መካተቱን ጠቁሞ፣ ‹ፍሮንቴር› የተባለ የጥናት ተቋም 130 ባለሙያዎች መድቦ እንደተካሄደ አስታውቋል፡፡

- Advertisement -

ጥናቱ በአገሪቱ አሁን ላይ ያለውን የሙስና ደረጃ አመለካከት እንዳሳየና ሙስናን ማጥፋት ለዕድገትና ለመልካም አስተዳደር ወሳኝ በመሆኑ፣ የሙስና መከላከል ተግባር ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባጥናቱ ትኩረት ተሰጥቶ እንደተሠራ ተጠቁሟል፡፡

የጥናቱ ውጤትም በአሁኑ ወቅት አገሪቱን ከሚፈትኑ ትልልቅ ችግሮች መካከል ሙስና ሦስተኛ ደረጃ እንደሚገኝ ተነግሯል።

የከተማ ማዘጋጃ ቤቶች አካባቢም የሙስና ታጋላጭነት መኖሩንም በመጠቆም፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሙስናን ለመከላከል የሚያስችል ስትራቴጂ መቀየስ እንደሚገባቸው ጥናቱ አመልክቷል፡፡ ድርጊቱን ለመቀነስና ለማጥፋት ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ ያበራሩት የጥናቱ ቡድን መሪብታሙ ወንድሙ (ፕሮፌሰር) የተባሉ ምሁር ናቸው፡፡

‹‹ኮሚሽኑ ሙስናን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ወጥ ለማድረግ ፖሊሲና ስትራቴጂ እያዘጋጀ ነው፤›› ያሉት ደግሞ የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ምክትል ኮሚሽነር አቶ ወዶ አጦ ሲሆኑ፣ የተዘጋጀው ፖሊሲ በተለያዩ መድረኮች በዘርፉ ባለሙያዎችና በሚመለከታቸው አካላት በሚሰጡ ግብዓቶች ከበለፀገ በኋላ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ እንደሚላክ አስታውቀዋል፡፡

የጥናቱን ውጤት እንደ ወሳኝ ግብዓት በመጠቀም ሙስናን የመከላከል ሥራውን ለማጠናከር ርብርብ እንደሚደረግ ቃል ገብተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...