Sunday, May 19, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

​​​​​​​[ክቡር ሚኒስትሩ በድል አድራጊነት ኩራት ወደ ቢሯቸው እየገቡ ሳለ ለውጡን አይቀበልም ተብሎ ከሚታማ አንድ ባልደረባቸው ጋር ኮሪደር ላይ ተገናኙ። እንኳን ደስ አሎት እንደሚላቸው ሲገምቱ ሰላምታ ብቻ አቅርቦላቸው መንገዱን መቀጠሉ አበሳጭቷቸው ቢሯቸው እንዲመጣ አስጠሩት] 

 • በድጋሚ ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር?
 • ለአንተ አብዝቶ ይስጥህ፡፡
 • ምን አሉኝ ክቡር ሚኒስትር?
 • ለአንተ አብዝቶ ቢሰጥህ ይሻላል ብዬ ነው። 
 • ምን?
 • ጤና ነዋ፡፡
 • ኧረ ደህና ነኝ፡፡ ጤነኛ ነኝ ክቡር ሚኒስትር አያስቡ።
 • ጤነኛ ብትሆንማ አገርና ሕዝብ ያስደሰተ ስኬት ያስደስትህ ነበር።
 • የምን ስኬት ነው? ሳልሰማ ያመለጠኝ ዜና አለ እንዴ ክቡር ሚኒስትር? 
 • መላ ሕዝቡን ያስፈነደቃና አገር ያኮራን ስኬት ለመስማት አለመቻል በራሱ የጤንነት ምልክት አይደለም። ታላቁ ህዳሴ ግድባችን የክብራችንና ልዕልናችን መገለጫ እንጂ ቁዘማችንን የምንገልጽበት አይደለም። 
 • አሁንአልገባኝም ክቡር ሚኒስትር?
 • ለውጡን እንደማትደግፍ እናውቃለን፡፡ ነገር ግን በዚህ የሕዝብ ፕሮጀክት ላይ ፊት ታዞራላችሁ ተብሎ አይታሰብም። የአገር ሰንደቅ በሆነው በዚህ ፕሮጀክት ስኬት አለመደሰት ክህደት ነው።
 • ክቡር ሚኒስትር በዚህ እንኳን እኔ አልታማም። ለውጡን አይቀበልም ተብዬ ዕውቅና ብከለከልም ከኔ በላይ ለግድቡ ግንባታ ከደመወዙ ያዋጣ ሠራተኛ የለም። 
 • ታዲያ ለምን ደስተኛ አልሆንክም?
 • በምን?
 • በሁለተኛው ዙር የውኃ ሙሌት።
 • እንደጠበኩት ባይሆንም ደስተኛ ነኝ፡፡
 • ደስተኛ ከሆንክ ሠራተኛው በሙሉ እንኳን ደስ አለህ እያለኝ ሲያልፍ እየተመለከትክ  ሰላም ብቻ ብለህ እንዴት ልታልፈኝ ቻልክ? 
 • ክቡር ሚኒስትር እኔም ተመሳሳይ ነገር እየጠበኩኝ ስለነበረ ይሆናል።
 • ምን ማለትህ ነው?
 • እንኳን ደስ አለህ ይሉኝ ይሆናል ብዬ እየጠበኩ ነበር፡፡ ለዚያ ነው የተላለፍነው።
 • አሃእኔ አንተን እነኳን ደስ አለህ እንድልህ ትፈልግ ነበር? 
 • ክቡር ሚኒስትር እኔን ብቻ ሳይሆን መላ ሠራተኛውን እንኳን ደስ አላችሁ ይላሉ ብዬ አስቤ ነበር። አሁንም አልረፈደም። ይህንን ማድረግ እንዳለብዎት አምናለሁ።
 • ወይ ጉድእንዴት ነው የተናናቅነው ባክህ?
 • ክቡር ሚኒስትር ፈጽሞ መናናቅ አይደለም። 
 • እና ምን እያልክ ነው?
 • ክቡር ሚኒስትር ይህ ስኬት ለአንድ ወገን የሚሰጥ አይደለም እያልኩ ነው። ለምሥጋናው ባለቤት ይሰጠው ከተባለም ምሥጋናውን መውሰድ ያለበት መንግሥት አይደለም።
 • ልክ ነህ። ለውጡን የማትደግፉት እናንተ ነበር ምሥጋናውን ማግኘት የነበረባችሁ። 
 • ምሥጋናው የሁሉም ሕዝብ ነው ክቡር ሚኒስትር። የበለጠ መውሰድ አለበት ከተባለ ግን ሕዝቡ በተለይም ደሃው ኢትዮጵያዊ ከመቀነቱ ፈትቶ ለቀጣይ ትውልድ ብርሃን ለሚሰንቀው ደሃ ነው መሰጠት ያለበት። 
 • የእናንተ ችግር ይህ ነው። ሁሉን ነገር ለፖለቲካ ቅስቀሳ ማዋል ላይ ነው ትኩረታችሁ።
 • ክቡር ሚኒስትር ያልተገባ ምሥጋና ስለጠበቁ እንጂ የፖለቲካ ቅስቀሳ አይደለም።
 • እናንተን ማሳመን አይቻልም በል ወደስራህ ተመለስ!

[ክቡር ሚኒስትሩ በህዳሴ ግድቡ ስኬት መላ ሠራተኛውን ለማመስገንና እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ሠራተኛው ወደ መሰብሰቢያ አዳራሽ እንዲገኝ አደረጉ ] 

 • በዛሬው ዕለት ላገኛችሁ የፈለኩት ለምን እንደሆነ እንደምትገምቱ እርግጠኛ ነኝ።
 • አዎ፡፡
 • ለዚህ ታላቅ የድል ቀን ለመድረስ የተቻለው እናንተ ጭምሮ መላው ሕዝብ ባደረገው ከፍተኛ ድጋፍ በመሆኑ ተገቢውን ምሥጋና ለማቅረብስለቀጣይ ድጋፍ ለመነጋገር ነው። በዚህ ላይ አስተያየት ያላችሁ ሐሳባችሁን ለማቅረብ ዕድል እሰጣለሁ፡፡
 • እሺ እዚያ ጋር እጅ ያወጣኸው ሐሳብህን ማቅረብ ትችላለህ።
 •  አመሠግናለው ክቡር ሚኒስትር የዛሬው ድል በአጭር ጊዜ ሊመጣ የቻለው ሠራዊቱ ደጀን ወዳለበት አካባቢ እንዲወጣ በመደረጉ ነው። 
 • [ተስብሳቢው አጉረመረመ…]
 • ሠራዊቱ ያስመዘገበው ድል
 • [ተሰብሳቢው ማጉረምረሙን ቀጠለ]
 • ሐሳቤን እንድገልጽ ይፈቀድልኝ ክቡር ሚኒስትር?
 • እባካችሁ አንዴ እንደማመጥማነህእየተወያየን ያለነው ስለ ህዳሴ ግድቡ ስኬት ስለሆነ በዚህ ላይ ብታተኩር?
 • ይቅርታ ክቡር ሚኒስትርወይይቱ በራያና አካባቢው ስለተመዘገበው ድል መስሎኝ ነው፡፡
 • በዚህ ጉዳይ ላይ በሌላ መድረክ እንወያያለንአሁን ማይኩን አጠገብህ ላለው አቀብልልኝ፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር ዕድሉን ስላገኘሁ አመሠግናለሁ። የህዳሴ ግድቡ ስኬት የሚያኮራ ቢሆንም በዕቅዱ መሠረት ይሞላል የተባለው የውኃ መጠን እንዳልተሞላ እየተወራ በመሆኑ ማብራሪያ ቢሰጡን?
 • መንግሥት ያስቀመጠው ግብ ኃይል ለማመንጨት የሚያስችል ውኃ መያዝ እንደሆነ ግልጽ መሆን አለበት። ይህንን በሰሞኑ የውኃ ሙሌት አሳክተናል። ሌላው አሉባልታ ጠላቶቻችን የሚነዙት ነው።እሺ ማይኩን ከኋላ ላለው አቀብሉልኝ
 • ክቡር ሚኒስትር እኔ ጥያቄ ሳይሆን ቀደም ባለው ጥያቄ ላይ አስተያየት ለመስጠት ነው የሚፈቀድልኝ ከሆነ?
 • ጥሩ ቀጥል፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር አርሶ እንዳሉት መንግሥት ያስቀመጠው ግብ ኃይል ማመንጨት እንጂ ውኃ ብቻ መያዝ አይደለም። በሌላ በኩል መንግሥት ይህንን ስኬት በምዕራብ በኩል ለማሳካት የቻለው ሌላ ግድብ በሰሜኑ በኩል እየገነባ እንደሆነ መዘንጋት የለበትም። ለዚህ ማስረጃ የሚሆነው በሰሜን በኩል ለተጀመረው ሥራ መንግሥት ባለፉት ወራት ብቻ ያወጣው ወጪ ግድቡ እስከ ዛሬ ከፈጀው ወጪ ጋር ተመጣጣኝ መሆኑ መዘንጋት የለበትም። 
 • ቀደም ያለው ባልደረባችን የተናረው ሁላችንንም የሚያስማማ ይመስለኛል። አይደለም እንዴ?
 • ጥያቄ አለኝልክ ነው… [ሠራተኛው አጉረመረመ] 
 • ጥሩ። እንደዚያ ከሆነ ሙሉ ሠራተኛው የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ ለመቀጠል ተስማምቷል ማለት ነው። በመሆኑም የአንድ ወር ደመወዙን በመስጠት ድጋፉን ለመቀጠል ተቋማችን ወስኗል!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...

በስድስተኛው ዙር ጠቅላላና ድጋሚ ምርጫ የሚሳተፉ ፓርቲዎች በገዥው ፓርቲ ላይ ተቃውሞ እያቀረቡ ነው

በ2013 ዓ.ም. ስድስተኛው ምርጫ ባልተካሄደባቸው ክልሎች በጠቅላላና በድጋሚ ምርጫ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ የቢሮ ሥራቸውን አጠናቀው ከውጭ አገር የመጣ ወንድማቸውን ለመጠየቅ ያረፈበት ገስት ሀውስ ሲደርሱ ወንድማቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ፕሮግራም በመገረም እየተከታተለ አገኙት]

ውይ መጣህ እንዴ? እስኪ አረፍ በል፡፡ ምንድነው እንዲህ ያስደነቀህ? ተደንቄ ሳይሆን ግራ ግብት ብሎኝ ነው። ምኑ ነው ግራ ያጋባህ? የድልድይ ማስመረቅና የድልድይ ማፍረስ ነገር ነዋ። አልገባኝም? አለቃችሁ ድልድይ ሲያስመርቁ የተናገሩትን...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከዘመዶቻቸውና ቤተሰቦቻቸው ጋር ሆነው በዓሉን በመኖሪያ ቤታቸው እያከበሩ ነው። ባለቤታቸውም ለበዓሉ የተዘጋጀውን ዳቦ ባርከው እንዲቆርሱ ለሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

በል ዳቦውን ባርክና ቁረስልንና በዓሉን እናክብር? ጥሩ ወዲህ አምጪው... አዎ! በል መርቅ... ከዓመት ዓመት ያድርሰን... ኧረ በሥርዓት መርቅ ተው? ከዓመት ዓመት ያድርሰን አልኩኝ እኮ ...አልሰማሽም? ከዓመት ዓመት መድረሱ ብቻ ምን...

[ክቡር ሚኒስትር መንግሥት ይፋ ያደረገውን ንቅናቄ አመራሮችና ቤተሰቦቻቸው በግንባር ቀደምትነት እንዲቀላቀሉ መታዘዙን ለባለቤታቸው እያጫወቱ በዚያውም ወደተከፈተው የባንክ ሒሳብ ገንዘብ እንዲያስተላልፉ እያግባቧቸው ነው]

በይ እስኪ ሞባይልሽን አውጪና ወደዚህ የባንክ ሒሳብ አንድ ሺሕ ብር አስተላልፊ? ለምን? መንግሥት ያስጀመረውን ንቅናቄ አመራሩ ከነቤተሰቡ ግንባር ቀደም ሆኖ እንዲደግፍ ታዟል። የምን ንቅናቄ ነው መንግሥት ያስጀመረው? ‹‹ፅዱ...