Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊ​​​​​​​ለአምስት ዓመታት የሚዘልቀው ሁለተኛው የአዕምሮ ጤና ስትራቴጂ ይፋ ሆነ

​​​​​​​ለአምስት ዓመታት የሚዘልቀው ሁለተኛው የአዕምሮ ጤና ስትራቴጂ ይፋ ሆነ

ቀን:

ከ2013 ዓ.ም. እስከ 2017 ዓ.ም. ድረስ የሚቆየው ሁለተኛው የአምስት ዓመት ብሔራዊ የአዕምሮ ጤና ስትራቴጂ ይፋ ሆነ፡፡ በያዝነው ሳምንት ይፋ የሆነው ስትራቴጂ ግሎባል ኮምፕሬሄንሲቭ ሜንታል ሔልዝ አክሽን ከዘላቂ የልማት ግቦች ጋር ተጣጥመው በመተግበር ላይ የሚገኙ ሥራዎችን ለማጠናከርና ክፍተቶችን ለመሸፈን በሚያስችል መልክ የተቀየሰ ነው፡፡

የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፣ የመጀመርያው ብሔራዊ የአዕምሮ ጤና ስትራቴጂክ ዕቅድ የጤና ባለሙያዎችን ቁጥርና ስብጥር በማሻሻል፣ የአዕምሮ ጤና አገልግሎቶችን ተደራሽ በማድረግ ብዙ ውጤቶችን አበርክቷል፡፡

የአዕምሮ፣ የነርቭና የአደንዛዥ ዕፅ ችግሮች ዋና ዋና የኅብረተሰብ ጤና ችግሮች መሆናቸውን ሚኒስትሯ አመልክተው፣ ይህም ለአካል ጉዳተኝነት፣ የዕለት ተዕለት ኑሮን በማስተጓጎልና ምርታማነትን በመቀነስ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳለው አስረድተዋል፡፡

በመድኃኒትና በሕክምና መሣሪያዎች ዘርፍ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታትና የተሻሉ አሠራሮችን ለመዘርጋት የሚያስችሉ የውሳኔ ምክረ ሐሳቦች የማመንጨት ሥራ እየተከናወነ እንደሆነ ሚኒስትሯ ጠቅሰው፣ የሚመነጨው የውሳኔ ሐሳብ ችግሮቹን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይፈታል የሚል እምነት እንዳላቸው አስረድተዋል፡፡

 

ከታዩት ልዩ ልዩ ችግሮች መካከልም መድኃኒቶቹንና መሣሪያዎችን አጠቃቀም፣ አመራረት፣ ግዥና ሽያጭ ላይ ያጠነጠኑ ሲሆን ተግዳሮቶችን ለመፍታት በሚካሄደው እንቅስቃሴ ላይ ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሚኒስቴሩ የሜዲካል ሰርቪስ ዳይሬክተር አቶ ያዕቆብ ሰማን መድኃኒትና የሕክምና መሣሪያዎችን የማምረቱ ጉዳይ በቀጣይም በመንግሥት ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶት ከሚሠራባቸው ተግባራት ቀዳሚ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...