Monday, May 27, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ2014 በጀት ዓመት 70.6 ቢሊዮን ብር በጀት ወሰነ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ማክሰኞ ሐምሌ 6 ቀን 2013 ዓ.ም. ባካሄደው መደበኛ ጉባዔ፣ 2014 በጀት ዓመት 70,670,216,028 ብር በጀት ወስኖ ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መራ፡፡

ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ጉባዔ የተጠቀሰውን ያህል ከፈተኛ የሆነ በጀት ያፀደቀው 2014 በጀት ዓመት፣ ለካፒታልናመደበኛ ሥራዎች የከተማዋን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስቀጠልየነዋሪዎችን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ለማስቻል መሆኑን ጠቁሟል፡፡

2014 በጀት ድልድል 2013 በጀት ዓመት ከተያዘው በጀት ጋር ሲነፃፀር፣ 9,319,594,13.13 ብር ወይም 15.19 በመቶ ዕድገት እንዳለው አስታውቋል፡፡

ከተማ አስተዳዳሩ የቀጣይ አሥር ዓመታትና አምስት ዓመታት መሪ ዕቅድ የትኩረት አቅጣጫዎችንና ስትራቴጂክ ግቦችን መሠረት በማድረግ 2014 በጀት ዓመት ለኮንስትራክሽንለውኃና ፍሳሽለመንገድ ልማት፣ ለትምህርትና ሥልጠና፣  ለትራንስፖርት፣ ለአረንጓዴ ልማት፣ ለጤናና ለቤቶች ልማት ዘርፎች ከፍተኛ በጀት መመደቡን ገልጿል፡፡

በከተማ ደረጃ ለሚገኙ የማዕከል መሥሪያ ቤቶች በጠቅላላው 46,559,320,315.98 ብር የተመደበ ሲሆን፣ ከአጠቃላይ በጀት ውስጥ 65.88 በመቶ ድርሻ እንዳለውም አክሏል፡፡

ለማዕከል መሥሪያ ቤቶች ከተመደበው በጀት ውስጥ ለመደበኛ 16,248,362,343.73 ብር እና ለካፒታል 30,310,957,972.25 ብር ደልድሏል። ለክፍላተ ከተሞች የተመደበ በጀት ደግሞ 24,110,895,712.33 ብር ሲሆን፣ ከአጠቃላይ በጀት 34.12 በመቶ ድርሻ እንዳለው አስታውቋል፡፡ ከዚህ ውስጥ ለመደበኛ በጀት ብር 20,541,879,040.39 ብር እና ለካፒታል ደግሞ 3,569, 016,671.94 ብር በመሆን ደልድሏል።

በጀቱን ታክስ ከሆኑና ካልሆኑ ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ከሌሎች ምንጮች ማለትም ከብድርና ከዕርዳታ እንዲሁም ካለፈው በጀት ተሸጋሪ፣ በጀቱን ለሟሟላት በዕቅድ መያዙን የከተማው ፕሬስ ሴክሬታሪያት ማክሰኞ ሐምሌ 6 ቀን 2013 ዓ.ም. ይፋ ያደረገው መረጃ ያመለክታል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች