Friday, May 24, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

​​​​​​​[ክቡር ሚኒስትሩ አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር የሆነ ወዳጃቸው ዘንድ ደውለው ስለምርጫው ውጤት እያወሩ ነው]

 • ላም ክቡር ሚኒስትር እንዴት አሉ?
 • ውጤቱ እንዴት ነው እንዳሰባችሁት አገኛችሁ?
 • እንዳሰብነው ጠቀለልነው ማለትዎ ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • ተቃዋሚዎች የተወሰኑ መቀመጫዎችን አግኝተዋል የሚል ዜና ተመልክቼ፣ ያው የአንተ ፓርቲ እንደሚሆን ገምቼ ነው የደወልኩት። 
 • ክቡር ሚኒስትር ተቃዋሚዎች አገኙ የተባለውንም ያሸነፈባቸው የእርስዎ ፓርቲ ነው። 
 • ተቃዋሚዎች የተወሰነ ወንበር አገኙ የሚለው መረጃ ሐሰተኛ ነው እያልከኝ ነው?
 • ሐሰተኛ አይደለም እውነታውን ማለቴ ነው፡፡
 • ምን እያልክ ነው? 
 • የእርስዎ ፓርቲን ወክለው በግል የተወዳደሩ ያሸነፉባቸው ናቸው ማለቴ ነው። 
 • በቀጣይ ፓርላማ እንገናኝ እንዳላልከኝ አንድም ወንበር ማግኘት አልቻላችሁም ማለት ነው? 
 • አንድም ወንበር ሳናስቀር ጠቀለልነው ቢሉ ይሻላል ክቡር ሚኒስትር። 
 • ለነገሩ ፓርላማ ባይሆንም ሌላ ቦታ መገናኘታችን አይቀርም።
 • ሌላ ቦታ የት?
 • ቶሞካ፡፡
 • ለምን?
 • ወንበር የለም እዚያ፡፡ 
 • በዚህ ይቀለዳል ክቡር ሚኒስትር
 • በል ደህና ዋል!

[ክቡር ሚኒስትሩ እየበረታ ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ጫና ለመቀልበስ የሚቻልበትን ሥልት ለመንደፍ ከአማካሪዎቻቸው ጋር የጀመሩትን ምክክር አጠናቀው ከቀድሞ ዲፕሎማቶች ጋር በጀመሩት ምክክር፣ አንድ አንጋፋ ዲፕሎማት ቢሯቸው ጋብዘው እየተወያዩ ነው]

 • እንደ እርስዎ ያሉ አገራቸውን በሙያቸው ያገለገሉ አንጋፋ ዲፕሎማቶች በተግባር የተፈተነ ተሞክሮ፣ አሁንም ለአገር ፋይዳ እንዳለው ስለምናምን ነው ዛሬ የተገናኘነው። 
 • ክቡር ሚኒስትር እርስዎ ወደ አመራርነት ከመጡ ወዲህ ከፓርቲና ከመንግሥት መዋቅር ውጪ የባለሙያዎችን ምክረ ሐሳብ ለመስማት የሚያደርጉት ጥረት በአገሬ ማየት የጀመርኩት አንድ በጎ ለውጥ ነው። 
 • ይህ ገና ጅማሮ ነውኢትዮጵያ የልጆቿን ሙሉ አቅም በስፋት እንድትጠቀም ያላደረገ መንግሥት ዋጋ እንደማይኖረው በፅኑ እናምናለን፣ በስፋት የምንተገብረው ይሆናል።
 • ክቡር ሚኒስትር ይህ ድንቅ ሐሳብ ነው፣ እኔም ዕውቀትና ተሞክሮዬን ዛሬም ለአገሬ መስጠት እንድችል ስለፈቀዱ ከልብ አመሠግንዎታለሁ። 
 • እንደሚያውቁት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገራችን ላይ ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጫና በርትቷል፣ ይህንን ጫና ለመቀልበስ በእኛ በኩል ብዙ ጥረት እያደረግን ቢሆንም ዘላቂ ውጤት አላመጣምና በኛ በኩል ያልተረዳነው ይኖር እንደሆነ፣ ከአንጋፋ ዲፕሎማቶቻችን ልምድና ዕውቀት በመቅሰም ለመመለስ እንሻለን። 
 • ክቡር ሚኒስትር አገራችን አሁን የገጠማት ዲፕሎማሲያዊ ጫና መነሻ ምን እንደሆነ መለየትና ለችግሩ ምላሽ ለመስጠት ቀዳሚው ተግባር ነው። 
 • ልክ ነው፣ እንደሚረዱት የጫናው መነሻም ሆነ ማጠንጠኛ አንድም ግድባችን ሲሆን ሌላው ደግሞ የሕግ ማስከበር ዘመቻው ነው። 
 • የጠቀሷቸው ምክንያቶች ዲፕሎማሲያዊ ጫናውን ለማሳረፍ እንደ መሣሪያ የተጠቀሙባቸው ስላለመሆናቸው ምን ያህል እርግጠኛ ነዎት? 
 • እንደ መሣሪያ ሲሉ ምን ማለትዎ ነው?
 • ማለቴ እነዚህ ጉዳዮች በኢትዮጵያ ላይ ጫናውን ለማሳረፍ ያመቹ ሊሆኑ ይችላሉ፣ ነገር ግን የሚፈለገው ውጤት ከተጠቀሱት ጉዳዮች ጋር የተገናኘ ላይሆን ይችላል ለማለት ፈልጌ ነው። 
 • ምክንያቶቹማ እነዚህ እንደሆኑ እነሱ ራሳቸው በግልጽ የሚናገሩት ነገር ነው፡፡ 
 • ክቡር ሚኒስትር የዲፕሎማሲ ጫናው ምክንያቶች እነዚህ ከሆኑ በማስረዳት ሊመለሱ የሚችሉ ናቸው የሚል እምነት አለኝ፣ ለምሳሌ ሚሲዮኖቻችን ግድቡ ምንም ጉዳት እንደማያደርስ በግልጽ በማስረዳት የተቀናቃኞቹ ጩኸት ምክንያታዊ አለመሆኑን ማጋለጥ ይቻላል፣ ሌላውንም እንደዚያው
 • ለማለት የፈለጉት ገብቶኛል አምባሳደር ነገር ግን አንድ ያልተረዱት ነገር አለ፡፡
 • ምንድነው?
 • ይኼውልዎት ያሉትን ከበቂ በላይ ሞክረናል፡፡ ነገር ግን ተቀናቃኞቻችን ጫና ከሚያደርሱብን ኃያል አገሮች ቁልፍ ሰዎች ጋር የተዛመዱ ናቸው፣ በዓለም አቀፍ ተቋማትም የራሳቸውን ሰዎች ሰግስገዋል።
 • እንዲህ ዓይነት ነገሮች ተፅዕኖ ለመፍጠር ምቹ ሁኔታን የፈጠረላቸው ይሆናል እንጂ፣ የአገሮችን ወይም የተቋማትን የፖለቲካ አቋም ያስቀይራሉ ለማለት ያስቸግራል ክቡር ሚኒስትር። 
 • [አይሰሙም እንዴ ሰውዬው] ክቡር ሚኒስትሩ አጉረመረሙ፡፡
 • ምን አሉኝ ክቡር ሚኒስትር?
 • ተቀናቃኞቻችን የቆየ ቤተሰባዊ ቅርበት ስለፈጠሩ ነው ጫናውን ለማክሸፍ የተቸገርነው እያልኩዎት ነው፣ ይህንን መረዳት ከፈለጉ በይፋ ሊመለከቱት ይችላሉ።
 • እንዴት?
 • በእኛ ላይ ጫና የፈጠሩት አገሮች ዲፕሎማቶች በግልጽ በየሚዲያው እየወጡ የእነሱን ሐሳብ እያራመዱና እየጻፉ ነው፣ በእኛ በኩል ያለውን እውነትና ምክንያታዊ ክርክር ግን ፈጽሞ አይጠቅሱም፣ ታዲያ ይኼ ቤተሰባዊ ትስስርን መሠረት ያደረገ መቆርቆር እንጂ ምን ሊሆን ይችላል?
 • ክቡር ሚኒስትር ከቤተሰባዊ ትስስሩ የበለጠ ኢትዮጵያ ፋይዳ ያላት አገር ነች፣ በቤተሰባዊ ትስስር የአገራቸውን ጥቅም ሊለውጡ ይችላሉ ለማለት ይከብዳል፣ እነሱ በኢትዮጵያ ላይ ጥቅም ባይኖራቸው እንኳ የእነሱ ወዳጅ የሆነ አገር ጥቅም በኢትዮጵያ ላይ ይኖራል። 
 • ልክ ነው፣ ታዲያ ምን እያሉኝ ነው? ምክረ ሐሳብዎ ምንድነው?
 • ለማለት የምፈልገው በኢትዮጵያ ላይ ብርቱ የሆነ ዲፕሎማሲያዊ ጫና እያደረጉ ያሉት አገሮች ታሪካዊና ፖለቲካዊ ፍላጎትን ማጥናትና ከኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁነቶች የትኛው የእነዚህን አገሮች ፍላጎት እንደጎዳ፣ ወይም የመጉዳት አቅም እንዳለው መተንተን ያስፈልጋል።
 •  ግድቡ ከእነሱ ታሪካዊና የፖለቲካ ፍላጎት ጋር ምን ያገናኘዋል? የዓባይ ውኃ ለእነሱ ምናቸው ነው? 
 • ክቡር ሚኒስትር ደፈሩኝ አይበሉኝና አንድ ጥያቄ ላንሳልዎት?
 • እባክዎ ይቀጥሉ?
 • ኤርትራ ላለፉት 30 ዓመታት ከዓለም የተገለለችና በምዕራባዊያኑ ማዕቀብ የተደቆሰች አገር እንዴት ልትሆን በቃች? ኤርትራ ኢትዮጵያን በመውጋቷ የተፈጠረ ይመስልዎታል?
 • አስተዋጽኦ ቢኖረውም አልሸባብን መደገፏ ነገሩን ሳያብሰው አይቀርም። 
 • አልሸባብን መደገፍ የሚለው በማዕቀብ ለማድቀቅ የተቀነባበረ ምክንያት አለመሆኑን እርግጠኛ መሆን ያሻል፣ አልሸባብ አሁንም እኮ አልጠፋም፡፡
 • እና ምን እያሉኝ ነው?
 • ክቡር ሚኒስትር ነገሮች ቀጥታ ግንኙነት ላይኖራቸው ይችላል፣ በመሆኑም የሚመሩት መንግሥት አውቆም ሆነ ሳያውቀው የነካው የእነሱ ቁልፍ ጥቅም እንደሚኖር ከልምድ መረዳት እችላለሁ፣ ነገር ግን በጥናታዊ ትንታኔ ቢታገዝ ደግሞ ለመፍትሔውም ጠቃሚ ነው
 • ይቀጥሉ… ይቀጥሉ…
 • እንጂማ ለጥቅም ተጋሪ ድጋፍ ሲባል ነው ጫና የበዛበኝ አይባልም ማለቴ ነው!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...

ያልነቃ ህሊና!

ከሽሮሜዳ ወደ አራት ኪሎ ልንጓዝ ነው። ነቀፋ አንሶላው፣ ትችት...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትር በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ እንዲሳተፉ ከተለዩ ባለሀብቶች መካከል እንዱ ጋ ስልክ ደውለው በንቅናቄው ላይ እንዲሳተፉ ግብዣቸውን እያቀረቡ ነው]

መቼም ኢትዮጵያ ታምርት በሚል የተጀመረውን አገር አቀፍ ንቅናቄ ሳትሰማ አትቀርም ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ልክ ነው፣ ሰምቻለሁ ክቡር ሚኒስትር። አሁን ደግሞ ንቅናቄውን ለማጠናከር ኢትዮጵያ ታምርት የሚል የታላቁ...

[ክቡር ሚኒስትሩ የቢሮ ሥራቸውን አጠናቀው ከውጭ አገር የመጣ ወንድማቸውን ለመጠየቅ ያረፈበት ገስት ሀውስ ሲደርሱ ወንድማቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ፕሮግራም በመገረም እየተከታተለ አገኙት]

ውይ መጣህ እንዴ? እስኪ አረፍ በል፡፡ ምንድነው እንዲህ ያስደነቀህ? ተደንቄ ሳይሆን ግራ ግብት ብሎኝ ነው። ምኑ ነው ግራ ያጋባህ? የድልድይ ማስመረቅና የድልድይ ማፍረስ ነገር ነዋ። አልገባኝም? አለቃችሁ ድልድይ ሲያስመርቁ የተናገሩትን...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከዘመዶቻቸውና ቤተሰቦቻቸው ጋር ሆነው በዓሉን በመኖሪያ ቤታቸው እያከበሩ ነው። ባለቤታቸውም ለበዓሉ የተዘጋጀውን ዳቦ ባርከው እንዲቆርሱ ለሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

በል ዳቦውን ባርክና ቁረስልንና በዓሉን እናክብር? ጥሩ ወዲህ አምጪው... አዎ! በል መርቅ... ከዓመት ዓመት ያድርሰን... ኧረ በሥርዓት መርቅ ተው? ከዓመት ዓመት ያድርሰን አልኩኝ እኮ ...አልሰማሽም? ከዓመት ዓመት መድረሱ ብቻ ምን...