Sunday, May 19, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

​​​​​​​[ክቡር ሚኒስትሩ በክልሉ በጀት ጉዳይ ላይ አቅጣጫ ለመጠየቅ ወደ አለቃቸው ዘንድ ደወሉ]

[ክቡር ሚኒስትሩ በክልሉ በጀት ጉዳይ ላይ አቅጣጫ ለመጠየቅ ወደ አለቃቸው ዘንድ ደወሉ]

 • ጤና ይስጥልኝ አለቃ?
 • ሰላም፣ አሁን ተገናኝተን አልነበረም እንዴ? ምን ገጠመህ?
 • የተገናኘንበት ቦታ ለማውራት አመቺ ስላልነበር ነው አሁን የደወልኩት። 
 • እሺ ምን ነበር?
 • አለቃ የክልሉን በጀት እንዴት እንደምንለቅ እስካሁን የተቀመጠልን አቅጣጫ የለም። 
 • እነሱ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጠዋል ብለን አንለቅም። 
 • አለቃ
 • አይለቀቀም አልኩህ እኮ? በሌለን አቅም ከዚያም ከዚያም ብለን ከመቶ ቢሊዮን ብር በላይ ያወጣነው አይበቃም? 
 • አለቃ አልተረዱኝም። 
 • ምንድነው ያልተረዳሁት? አንዳንዴ አቋምህ ያጠራጥረኛል። 
 • አለቃ እኔ ለመጠየቅ የፈለግኩት ስለ 2013 ዓ.ም. በጀት አይደለም።
 • እና ስለመቼ ነው?
 • ስለ2014 ዓ.ም. በጀት ነው፣ በፀደቀው በጀት ለዚህ ክልልም ተይዟል። 
 • አሃእሱን ነው የምትለው?
 • አዎ፣ 2014 ዓ.ም. በጀት 12 ቢሊዮን ብር ተይዟል።
 • ዘንድሮ እንደ ወጣው ወጪ ቢሆን ኖሮ ለመጪዎቹ አሥር ዓመታት አይገባቸውም ነበር፣ ግን ምን ማድረግ ይቻላል?
 • ፓርላማው ያፀደቀውን በጀት ከመልቀቅ ውጪ ምን ማድረግ ይቻላል አለቃ? 
 • ይሁን ይለቀቅላቸው ሌላ ምን ማድረግ ይቻላል፡፡
 • የደወልኩት ለዚህ ነው አለቃ።
 • እኮ ይለቀቅ አልኩ አይደል እንዴ?
 • ለማን እንደምንለቅ እኮ ነው ግራ የገባን?
 • እንዴት? 
 • ያው ለእነሱ መልቀቅ አንችልማ?
 • ጭራሽ ለእነሱ? እንዴት አሰብከውባክህ?
 • ነገሩን ማለቴ እንጂ እንዲለቀቅ አስቤ አይደለም። 
 • ቢሆንም ጨርሶ እንደዚያ ማሰብ አልነበረብህም። 
 • ይቅርታ አለቃ ለማን እንደምንለቅ ተቸግረን ነው።
 • በጀቱ መለቀቅ ያለበትማ ለጊዜያዊ አስተዳደሩ ነው። 
 • ለእነሱ ለመልቀቅ አስበን አነጋግረናቸው ነበር። 
 • አንቀበልም አሉ?
 • አላሉም፣ ግን እነሱም አቅጣጫ እየጠበቁ ነው።
 • አቅጣጫ… አቅጣጫ… የምትሉት ነገር ምንድነው?
 • እነሱ የሚጠብቁት አቅጣጫ ክልሉን የማስተዳደር ኃላፊነታቸውን እንዴት እንደሚቀጥሉ ነው፣ እኛ ደግሞ
 • እንዳትጨርሰው
 • እኔን ነው አለቃ?
 • አንተ ራሱ አቅጣጫ ጠፍቶብሃል እንዳትጨርሰው። 
 • አለቃ ታዲያ በጀቱን ለማን ይሰጥ?
 • ዝም ብላችሁ ለጊዜያዊ አስተዳደሩ አስገቡ።
 • ጊዜያዊ አስተዳደሩ ከክልሉ ለቆ አዲስ አበባ ገብቷል
 • የትም ይግባበጀቱን ለእነሱ ልቀቅ። 
 • ጥሩ አለቃ ተጠያቂት እንዳያመጣብን ብዬ ነው እንዳሉት ለእነሱ እንለቃለን። 
 • ቆይቆይ
 • አቤት አለቃ?
 • ትንሽ አቆየው፡፡
 • አልገባኝም ምኑን ነው ማቆየው አለቃ?
 • በጀቱ ይዘግይ እንዳይለቀቅ ነው የምልህ። 
 • አይለቀቅ ይዘግይ?
 • አቅጣጫ እስከሚሰጣችሁ አቆዩት፡፡
 • ጥሩ፣ እንጠብቃለን አለቃ ደህና ይሁኑ!

[የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ ወደ አለቃው ቢሮ ሲገባ ሚኒስትሩ የፓርላማውን ስብሰባ በአካል ተገኝተው የመከታተል ዕቅዳቸውን ትተው፣ ቢሯቸው ያለውን የቴሌቪዥን ቻናል ለመቀየር ሲሞክሩ አገኛቸው]

 • ክቡር ሚኒስትር ምነው?
 • መጣህ እስኪ ቻናሉን ኢቲቪ ላይ አድርገው።
 • ምነው አስቸኳይ ጉዳይ ገጥሞዎት ነው?
 • አስቸኳይ ጉዳይ ቢገጥመኝ ለምን ኢቲቪ ላይ ቀይረው እልሃለሁ?
 • ማለቴየፓርላማውን ስብሰባ ተገኝተው እንደሚከታተሉ ነግረውኝ ነበር ብዬ ነው፡፡
 • ብዬ ነበር፣ ግን ሳስበው ወደ አዳራሹ ለመግባት የሚኖረው ፍተሻና ሠልፍ አደከመኝ።
 • እናንተም ትፈተሻላችሁ?
 • የሚቀር የለም።
 • አለቃ መቅረትዎን ቢያውቁ ግን ጥሩ ነው?
 • አስቸኳይ ጉዳይ ገጥሞኝ እንደሆነ ቀድሜ አሳውቂያለሁ። 
 • እንደዚያ ካደረጉ ጥሩ ነው። 
 • ጀምሯል እንዴእስኪ ድምፁን ከፍ አድርገው?
 • ዛሬ ደግሞ ፈጠን ብሎ ነው የተጀመረውብዙ ሳያመልጠን አይቀርም፡፡
 • ችግር የለውም ምሽት ላይ ሁሉም ቴሌቪዥኖች ይደግሙታል፡፡
 • እንዴ…? እንደዚያ ማለት አልነበረባቸውም ትክክል አይደሉም። 
 • አልሰማሁትም፣ ምንድነው ያሉት? 
 • ኢትዮጵያ 60 ኤምባሲዎች አያስፈልጓትም፣ ግማሹ መዘጋት አለበት እያሉ ነው። 
 • እንደዚያ አሉ እንዴ?
 • እንዴኬንያ ያለ አምባሳደር ኢትዮጵያ ቁጭ ብሎ የኬንያን ጋዜጣ ማንበብ ይችላል? ትክክል አይመስለኝም… ክቡር ሚኒስትር እንዴት ነው ነገሩ? 
 • በተለይ ለሕዝብ በቀጥታ እየተላለፈ እንደዚያ ባይባል ጥሩ ነበር፣ ችግሩ ግን ሰፊ ነው።
 •  የአንድን አምባሳደር ኃላፊነት ጋዜጣ አንብቦ መረጃ መላክ ብቻ እንደሆነ አድርጎ ማቅረብ ትክክል ነው?
 • ምን መሰለህ ሁሉም ባይሆኑ አንዳንዶቹ ዲፕሎማቶች ጋዜጣ ማንበብና በጋዜጣ ለወጣ ዘገባ መልስ መስጠት ብቻ አድርገው፣ እሱን እንደ ትልቅ ስኬት እንዲነገርላቸው ሲባዝኑ ጊዜያቸውን እንደሚያሳልፉ ባለፈው ገምግመን ነበር። አሁን ደግሞ በበይነ መረብ ስለህዳሴ ግድቡ ውይይት ማድረግ እንደ ፋሽን ይዘውታል። 
 • ታዲያ ይኼ ምን ችግር አለው ክቡር ሚኒስትር?
 • ችግር የለውም፣ ግን እንዱ ያደረገውን ሁሉም እንደ ፋሽን ይዘው በግድቡ የቴክኒክ ጉዳይ ውይይት ማድረጋቸው ጊዜ ማባከን ነው።
 • በቴክኒክ ጉዳይ ሊያግዙ ከሚችሉ ዳያስፖራ ምሁራን ጋር ከሆነ አይከፋም። 
 • ችግሩ እንደዚያ አለመሆኑ ነው፣ ሁሉም ኤምባሲዎች በጋራ ሆነው አንድ የበይነ መረብ የውይይት መድረክ ማዘጋጀት ወይም ደግሞ አንድ ቦታ የተደረገውን ውይይት ቅጅ ለዳያስፖራውም፣ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ተደራሽ ማድረግ ይችሉ ነበር። 
 • ልክ ነውእንደዚያ ማድረግ ይችሉ ነበር፣ ቢሆንም ያሉን ኤምባሲዎች በዝተዋል ይዘጉ ባይባል ጥሩ ነበር። 
 • በድፍኑ እንደዚያ ባይባል ጥሩ ነው። 
 • በድፍኑ ሲሉ ምን ለማለት ነው? 
 • አሁን ያለንበት ወቅት ከጀርባችን የሚወጉንየእኛን ወዳጅነት የማይፈልጉ በርካታ አገሮችን አሳይቶናል። በእነዚህ አገሮች ኤምባሲዎቻችንን ማቆየት ምንም ጥቅም የለውም። እሳቸውም ይህንን በግልጽ ለመናገር ስላልፈለጉ በሌላ መንገድ ኤምባሲዎች ሊዘጉ እንደሚችሉ እያሳወቁ ይመስለኛል።
 • እንዴእንዴአሁን የተናገሩት ደግሞ የባሰ ነው፣ ክቡር ሚኒስትር እንደዚህ ማለት የነበረባቸው አይመስለኝም፡፡
 •  ምንድነው እንደዚህ ያስደነገጠህ?
 • እስካሁን ክተት አላወጅንም እያሉ እኮ ነው፣ እንደዚያ ማለታቸው ጥሩ አልመሰለኝም፣ ባይሉ ይሻል ነበር።
 • ለምን? 
 • እንዴ ክቡር ሚኒስትር የውስጣችን ችግር እንጂ የውጭ ጠላት አይደል የገጠመን፡፡
 • ዝቡ ነገሩ ስላልገባው ነው ብዬ አስብ ነበር፣ አንተም እንደዚያ አልክ?
 • ክቡር ሚኒስትር ለውስጥ ችግር ክተት ማወጅ ልክ ነው እያሉ ነው?
 • አይደለም። ችግሩን የሚረዳ መጥፋቱ አስገርሞኝ ነው፣ ለነገሩ በእኛም በኩል የችግሩን መጠንና ሰንሰለት ለማስረዳት አልቻልንም። 
 • ችግሩ ሰፊና ወጣ ያለ ነው እያሉኝ ነው? 
 • እስከ ጎረቤት አገር የተዘረጋ ወጥመድ ነው፣ በቅርቡ በሱዳን በኩል የሚሞክሩትን ታያለህ። 
 • ምን አስበው ነው?
 • ሁሉም የየራሱን ፍላጎት ይዞ ነው የተሠለፈብን።
 • ታዲያ እነሱ ምን ያገኛሉ?
 • በጎረቤት አገር ድጋፍ ያሰናዱትን እሳት ከወዲያ ሆነው፣ እነሱ ደግሞ ከታች ያዘጋጁትን እሳት በአንድነት በመለኮስ ኃይላችንን ለማዛባት አሲረዋል።
 • እንደዚያማ ከሆነ ክተት መባል አለበት። 
 • አየህ ብዙ ወጥመድ ነው ያበጁልን፣ ክተት ቢባል እንኳን ያጠመዱትን ለመበጣጠስ እንጂ ለእነሱ አይሆንም!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...

በስድስተኛው ዙር ጠቅላላና ድጋሚ ምርጫ የሚሳተፉ ፓርቲዎች በገዥው ፓርቲ ላይ ተቃውሞ እያቀረቡ ነው

በ2013 ዓ.ም. ስድስተኛው ምርጫ ባልተካሄደባቸው ክልሎች በጠቅላላና በድጋሚ ምርጫ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ የቢሮ ሥራቸውን አጠናቀው ከውጭ አገር የመጣ ወንድማቸውን ለመጠየቅ ያረፈበት ገስት ሀውስ ሲደርሱ ወንድማቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ፕሮግራም በመገረም እየተከታተለ አገኙት]

ውይ መጣህ እንዴ? እስኪ አረፍ በል፡፡ ምንድነው እንዲህ ያስደነቀህ? ተደንቄ ሳይሆን ግራ ግብት ብሎኝ ነው። ምኑ ነው ግራ ያጋባህ? የድልድይ ማስመረቅና የድልድይ ማፍረስ ነገር ነዋ። አልገባኝም? አለቃችሁ ድልድይ ሲያስመርቁ የተናገሩትን...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከዘመዶቻቸውና ቤተሰቦቻቸው ጋር ሆነው በዓሉን በመኖሪያ ቤታቸው እያከበሩ ነው። ባለቤታቸውም ለበዓሉ የተዘጋጀውን ዳቦ ባርከው እንዲቆርሱ ለሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

በል ዳቦውን ባርክና ቁረስልንና በዓሉን እናክብር? ጥሩ ወዲህ አምጪው... አዎ! በል መርቅ... ከዓመት ዓመት ያድርሰን... ኧረ በሥርዓት መርቅ ተው? ከዓመት ዓመት ያድርሰን አልኩኝ እኮ ...አልሰማሽም? ከዓመት ዓመት መድረሱ ብቻ ምን...

[ክቡር ሚኒስትር መንግሥት ይፋ ያደረገውን ንቅናቄ አመራሮችና ቤተሰቦቻቸው በግንባር ቀደምትነት እንዲቀላቀሉ መታዘዙን ለባለቤታቸው እያጫወቱ በዚያውም ወደተከፈተው የባንክ ሒሳብ ገንዘብ እንዲያስተላልፉ እያግባቧቸው ነው]

በይ እስኪ ሞባይልሽን አውጪና ወደዚህ የባንክ ሒሳብ አንድ ሺሕ ብር አስተላልፊ? ለምን? መንግሥት ያስጀመረውን ንቅናቄ አመራሩ ከነቤተሰቡ ግንባር ቀደም ሆኖ እንዲደግፍ ታዟል። የምን ንቅናቄ ነው መንግሥት ያስጀመረው? ‹‹ፅዱ...