Monday, May 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናአንዳንድ ተቋማት ሕጋዊ መሠረት በሌላቸው መመርያዎች የተገልጋዮችን መብቶች እየጣሱ መሆኑ ተጠቆመ

አንዳንድ ተቋማት ሕጋዊ መሠረት በሌላቸው መመርያዎች የተገልጋዮችን መብቶች እየጣሱ መሆኑ ተጠቆመ

ቀን:

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምንም ዓይነት መመርያ ባለማስመዝገቡ ሕጋዊ መሠረትና ተፈጻሚነት የለውም ተብሏል

አንዳንድ ተቋማት የተሰጣቸውን የውክልና ሥልጣን ባልተገባ መንገድ በመጠቀም፣ ሕጋዊ መሠረት የሌላቸውንና የተገልጋዩን ማኅበረሰብ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የሚጥሱ መመርያዎችን አውጥተው እንደሚጠቀሙ ተጠቆመ፡፡

የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ የቆየውና በተለይም ከመመርያዎች ጋር የተያያዘ ጉዳይ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን፣ ሕግ የማውጣት ሥልጣን ያለው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቢሆንም፣ የፌዴራል ተቋማትና ተጠሪ መሥሪያ ቤቶች የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ የቆየውና በተለይም ከመመርያዎች ጋር የተያያዘመሆኑ፣ ተቋማቱ የየራሳቸውን የአሠራር መመርያ የማውጣት ውክልና የተሰጣቸው ቢሆንም፣ የውክልና ሥልጣኑን ያላግባብ እየተጠቀሙ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

- Advertisement -

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ፣ የሕግ ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ  አቶ ተስፋዬ ዳባ ሰኔ 23 ቀን 2013 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት፣ አንዳንድ አስፈጻሚ ተቋማት ሕጋዊ መሠረት የሌላቸውንና አሳታፊ ያልሆኑ መመርያዎችን በሚፈልጉበት መንገድ በማውጣት፣ ተገልጋዩን ማኅበረሰብ ለከፋ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ሲዳርጉ ቆይተዋል፡፡

በሕገ መንግሥቱ ውስጥ የመንግሥት ሥራ ግልጽና ተጠያቂነት ባለው መንገድ መመራት አለበት ተብሎ ግልጽ ሆኖ የተቀመጥ ቢሆንም፣ አንዳንድ አስፈጻሚ ተቋማት ግን ሕጋዊ መሠረት የሌላቸውንና አሳታፊ ያልሆኑ መመርያዎችን በሚፈልጉት መንገድ በማውጣት፣ ተገልጋዩን ማኅበረሰብ ለከፋ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ሲዳርጉ መቆየታቸውን አስረድተዋል፡፡ ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት ከመጋቢት 29 ቀን 2012 .ም. ጀምሮ የፌዴራል የአስተዳደር ሥነ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 እንዲፀድቅ መደረጉን፣ ይኼም የሆነው ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ተከብረው ዜጎች ከተቋማቱ የሚፈልጉትን አገልግሎቶች ማግኘት እንዲችሉ፣ የሚወጡ መመርያዎች በጠቅላላ ግልጽነት ያላቸው፣ ተገልጋዩን ማኅበረሰብ አሳታፊ ያደረጉና ከግምት ውስጥ ያስገቡ እንዲሆኑም ጭምር ታሳቢ ተደርጎ መሆኑን አቶ ተስፋዬ አብራርተዋል፡፡

በፌዴራል የአስተዳደር ሥነ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 መሠረት የተመዘገቡ፣ በጠቅላይ ዓቃቤ ሕግና መመርያውን ባወጣው ተቋም ድረ ገጽ ላይ ተጭኖ ለኅብረተሰቡ ይፋ የተደረገ መሆን እንዳለበትም መደንገጉንም አክለዋል፡፡

ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት መሠረት እስካሁን ስላከናወናቸው ተግባራትና አጠቃላይ ሒደቶች ያብራሩት ምክትል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ፣ ከለውጡ በኋላ ከሰብዓዊ መብትናዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ጋር በተያያዘ በርካታ አዋጆችን የማሻሻልና አዳዲስ አዋጆችን የማውጣት ተግባራት መከናወናቸውን ጠቁመው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ የፀረ ሽብርና ሌሎች በርካታ አዋጆችን የማሻሻል፣ እንዲሁም የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት የዕርቀ ሰላም ኮሚሽን፣ የማንነትና የአስተዳደር ወሰን ጉዳዮች ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጆችን የማውጣትና ተግባራዊ እንዲደረጉ የማድረግ ሥራ መከናወኑን በአብነት ጠቅሰዋል፡፡

በተጨማሪም 60 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠሩ ሕጎችን የማሻሻል ሥራ መከናወኑንና በቀጣይነትም እየተሠራ እንደሆነ የጠቆሙት አቶ ተስፋዬ፣ የንግድ ሕግን የማሻሻል ሥራ ተጠናቆ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቆ ተግባራዊ የተደረገ መሆኑንና የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ የማሻሻያ ሥራ ተጠናቆ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡን ተናግረዋል፡፡ በቅርቡ በምክር ቤቱ የሕግ፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቅራቢነት እንደሚፀድቅም አክለዋል፡፡

የአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ሥሪያ ቤቶችን ጨምሮ በፌዴራል አስፈጻሚ ተቋማት እስካሁን ድረስ በአዋጁ መሠረት የተመዘገቡ መመርያዎች ብዛት 857 ብቻ መሆናቸውን የገለጹት ምክትል ዓቃቤ ሕጉ፣ ከእነዚህም ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 66 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 159ገንዘብ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ 89 የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር 73፣ እንዲሁም ሌሎች ተቋማትም በተዋረድ ያወጧቸውን መመርያዎች እያስመዘገቡ ቢሆንም፣ በተቃራኒው የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ግን ምንም ዓይነት መመርያ አለማስመዝገቡንና ሕጋዊ መሠረትና ተፈጻሚነት እንደሌለውም ገልጸዋል፡፡

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ ሌሎች ያወጧቸውን መመርያዎች ያላስመዘገቡ ተቋማት፣ በሥራ ላይ ያዋሏቸውን መመርያዎች ሕጋዊ መሠረትና ተፈጻሚነት እንደሌላቸው ተረድተው፣ በአዋጁ መሠረት እንዲያስመዘግቡና ሕገ መንግሥታዊ ግዴታቸውን እንዲያከብሩ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡ ያልተመዘገቡና ተፈጻሚነት የሌላቸውን መመርያዎች ተጠቅመው መንግሥታዊ ሥራዎችን እያከናወኑ ያሉና በተገልጋዩ ማኅበረሰብ ላይ የመልካም አስተዳደር ችግር የሚፈጥሩ ተቋማት ሲያጋጥሙ፣ በፍርድ ቤት በኩል ክስ በመመሥረት የተወሰነባቸውን ውሳኔ ውድቅ የማስደረግና ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን የማስጠበቅ መብት እንዳላቸው አስታወቀዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ለውጭ ባንኮች መከፈት አገር በቀል ባንኮችን ለምን አስፈራቸው?

የማይረጥቡ ዓሳዎች የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች ሙግት ሲሞገት! - በአመሐ...

የምርጫ 97 ትውስታ!

በበቀለ ሹሜ      መሰናዶ ኢሕአዴግ ተሰነጣጥቆ ከመወገድ ከተረፈ በኋላ፣ አገዛዙን ከማሻሻልና...

ሸማቾች የሚሰቃዩት በዋጋ ንረት ብቻ አይደለም!

የሸማች ችግር ብዙ ነው፡፡ ሸማቾች የሚፈተኑት ባልተገባ የዋጋ ጭማሪ...

መንግሥት ከለጋሽ አካላት ሀብት ለማግኘት የጀመረውን ድርድር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፓርላማው አሳሰበ

የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገልጿል አዲስ አበባ...