Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊከ600 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የልህቀት ማዕከል ሊገነባ ነው

ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የልህቀት ማዕከል ሊገነባ ነው

ቀን:

በጄኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ውስጥ የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ የቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ልህቀት ማዕከል ሊገነባ ነው፡፡

ከዓለም ባንክ በተገኘው 643.8 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚገነባው ማዕከል በኢነርጂ ዘርፍ የኤሌክትሪካልና የዲጂታል ክፍለ አኅጉራዊ ማዕከል ሆኖ ያገለግላል፡፡

የፖሊ ቴክኒክ ኮሌጁ በዓለም ባንክ የምሥራቅ አፍሪካ የክህሎት ሽግግር ቀጣናዊ ትስስር ፕሮጀክት መሥፈርትን በማሟላቱ መመረጡን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ማዕከሉን ለመገንባት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር) እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የመሠረት ድንጋዩን ሰኔ 22 ቀን 2013 ዓ.ም. አስቀምጠዋል፡፡

ሚኒስትሩ እንደተናገሩት፣ የልህቀት ማዕከሉ በምሥራቅ አፍሪካ ደረጃ በጣም ጠንከር ያለ የአሠልጣኞች ሥልጠና የሚሰጥበት ይሆናል፡፡ ለዚህም የሚያገለግሉ ፋሲሊቲዎችን በማሟላት ረገድ መንግሥት የበኩሉን ዕገዛ ከማበርከት ወደኋላ አይልም፡፡

‹‹ከዚህም ተመርቀው የሚወጡ ወጣቶች በአብዛኛው ሥራ የሚፈጥሩ ወይም ኢንቨስተር የሚሆኑ እንጂ ሥራ ፈላጊዎች ሆነው ይቀራሉ ብለን አናምንምም፣ አንገምትም፤›› ብለዋል፡፡

ማዕከሉ ለኢትዮጵያ የኢነርጂና ኢንዱስትሪ ዘርፎች ትልቅ አቅም እንዳለው፣  ችግር ፈቺ የሆኑ ሥልጠናዎች እንደሚሰጡበትና በጉጉት የሚጠበቅ ከመሆኑ አንጻር ግንባታው ተፋጥኖ ወደ አገልግሎት እንዲገባ ሚኒስትሩ አሳስበዋል፡፡

ኮሌጁንም ወደ ዩኒቨርሲቲ ከፍ ለማድረግ የሚያስችሉ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው፣ ትምህርትና ሥልጠና ላይ የሚውለው ኢንቨስትመንት የሚያተርፍ እንጂ እንደ ሌላው ኢንቨስትመንት ለተደጋጋሚ ወጪ የሚዳርግ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡

በዚህም የተነሳ የከተማው አስተዳደር ለማዕከሉ አስፈላጊውን ግብዓት፣ በጀትና የሰው ኃይል በመመደብ የበኩሉን ዕገዛ ከማድረግ አይቆጠብም ብለዋል፡፡

የኮሌጁ ምክትል ዲን አቶ አድማሱ በቀለ፣ የማዕከሉ ግንባታ ሲጠናቀቅ የአስተዳደርና የመማሪያ ክፍሎች፣ ደረጃቸውን የጠበቁና ዘመናዊ ቤተመጻሕፍትና ክሊኒክ፣ የሕፃናት ማቆያ፣ የእንግዳ ማረፊያዎች፣ የተማሪዎች መመገቢያ ሬስቶራንቶች፣ ወርክሾፕ፣ የሜዳ ቴኒስ እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡

ማዕከሉ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከቀጣናው አገሮች ለተውጣጡ ሠልጣኝ ባለሙያዎች በኢነርጂ ዘርፍ፣ እንዲሁም በምርምርና ጥናት የልህቀት ማዕከል ሆኖ እንደሚያገለግል ነው ያመለከቱት፡፡

የጄኔራል ዊንጌት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ፋሺስት ጣሊያን ለስልክ ኦፕሬሽን ሲጠቀምባቸው በነበሩ ሁለት ክፍሎች ውስጥ ከ30 የማያንሱ ወጣቶችን በቀለም ትምህርት የማስተማር ሥራ የጀመረው በ1938 ዓ.ም. ሲሆን ኮንስትራክሽንን ማስተማር የገባው ደግሞ በ1973 ዓ.ም. ነው፡፡

ጄኔራል ዊንጌት ትምህርት ቤት ከየጠቅላይ ግዛቱ የተውጣጡ ምርጥ ተማሪዎች ተለይተው የሚማሩበት የነበረ ሲሆን፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ጨምሮ በርካታ ባለሙያዎችን ያፈራ መሆኑ ይታወቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...