Sunday, May 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናየፌዴራል የፀጥታ ኃይሎች ከመቀሌ ከተማ መውጣታቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ

የፌዴራል የፀጥታ ኃይሎች ከመቀሌ ከተማ መውጣታቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ

ቀን:

የፌዴራል መንግሥት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ያቀረበውን የተኩስ ይቁም ስምምነትን ጥያቄ ተቀብሎ ተኩስ ይቁም ካወጀ ከሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀትር በኋላ፣ የመከላከያና የፌዴራል የፀጥታ አባላት የመቀሌ ከተማን ሙሉ ለሙሉ ለቀው መውጣታቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

ነዋሪዎቹ የፌዴራል መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በወታደራዊናሲቪል ተሽከርካሪዎች በመሆን ከመቀሌ ለቀው ሲወጡ ያዩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ተሽከርካሪዎቹ የሚንቀሳቀሱት ተከታትለው እንደነበር የተናገሩት ነዋሪዎቹ፣ ከባድ መሣሪያዎችን በተጠንቀቅ የደቀኑ ወታደሮችንም ማየታቸውን አክለዋል። የፀጥታ አስከባሪ አባላቱ መቀሌን ለቅቀው መውጣታቸውን ተከትሎ፣ የትግራይ አማፅያን ወደ ከተማዋ መግባት መጀመራቸውን የሰሙ ቢሆንም በዓይን አለማረጋገጣቸውን ገልጸዋል።  

የፌዴራል መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች መቀሌን ሙሉ በሙሉ ለቀው ስለመውጣታቸውና ስለተኩስ አቁም እወጃው ማብራሪያ ለማግኘት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አብርሃም በላይ (ዶ/ር)ንም ሆነ የሚመለከታቸውን የመንግሥት ኃላፊዎች አግኝቶ ለማነጋገር የተደረገው ተደጋጋሚ ሙክራ ማተሚያ ቤት እስከገባንበት ማክሰኞ ምሽት ድረስ አልተሳካም፡፡

- Advertisement -

መንግሥት ተኩስ አቁም ያወጀው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከሳምንት በፊት ያቀረበውን ጥያቄ ካጤነ፣ የቀረቡትን ምክንያቶች ከመረመረና የራሱን ግምት ከወሰደ በኋላ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ ሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፣ ክረምት እየገባ በመሆኑ የትግራይ አርሶ አደር ተረጋግቶ የእርሻ ሥራውን እንዲያከናውን፣ የሰብዓዊ ድጋፍ ለተረጂዎች ያለ ምንም ችግር እንዲደርስና ወቅቱን የሚመጥን ፖለቲካዊ መፍትሔ ለመስጠት የፌዴራል መንግሥት የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያደርግ ተጠይቋል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ ባለፈው ሳምንት በይፋ ጥያቄውን ያቀረበው የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ ከክልሉዝብ ተወካዮች፣ ከቢሮና የዞኖች አመራር አባላት፣ በተለያየ ቦታ ከሚገኙ የትግራይ ተወላጆች፣ ከትግራይ ምሁራን፣ ከባለሀብቶችና ከሃይማኖት አባቶች ጋር ተከታታይ ምክክር ካደረገ በኋላ መሆኑንም አስታውቀዋል።

‹‹አሸባሪው የሕውሓት ቡድን በክልሉም ሆነ በአገሪቱ ላይ የፈጠረው ውስብስብ ችግር ወታደራዊ ብቻ ሳይሆን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ነው፤›› ያሉት አብርሃም በላይ (/) ለዚህም እስካሁን በፌዴራል መንግሥትና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የተለያዩ መፍትሔዎች ሲወሰዱ መቆየቱን አብራርተዋል።

በጊዜያዊ አስተዳደሩም ሆነ በፌዴራል መንግሥት እየተወሰዱ ያሉ ዕርምጃዎችን አስታውሰው፣ በቀጣይም ፖለቲካዊ አማራጮችን ታሳቢ ማድረግና የመፍትሔ ዕርምጃዎችን የመውሰድ አስፈላጊነት ላይ እምነት መኖሩን ጠቁመዋል። የክልሉ አርሶ አደር በዚህ ክረምት ወደ እርሻ ካልገባ የዘር ወቅት ስለሚያልፍ፣ በቀጣይ ገበሬው ለዓመታት ተረጂ ሆኖ የመኖርድል እንደሚገጥመው አውስተዋል፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚው ስለተኩስ ማቆም ጥያቄው ምክንያት በዝርዝር ካስረዱ በኋላ፣ ለፌዴራል መንግሥት ባለዘጠኝ ነጥብ ጥያቄ ማቅረባቸውንም ተናግረዋል፡፡

የተኩስ አቁም ስምምነቱ ገበሬው ተረጋግቶ እንዲያርስ፣ ለችግረኞች የሰብዓዊ ድጋፍና የዕርዳታ ቁሳቁስ ለማድረስ፣ የተፈናቃዮችን ቤት ጠግኖ ወደ ቦታቸው ለመመለስ እንደሚያስችልም አመልክተዋል።

የፌዴራል መንግሥትም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ላቀረበው የተኩስ አቁም ስምምነት ጥያቄ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ውሳኔውን በደብዳቤ አስታውቋል፡፡ የሕወሐት ቡድን ባለፉት ሰላሳ ዓመታት የሠራውንና በክልሉ ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ጉዳዩ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ሰፊ ጥረት ማድረጉንም በስፋት አብራርቷል፡፡

የፌዴራል መንግሥት ሕግማስከበር ጎን ለጎን የክልሉን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት በኢትዮጵያውያንና በኢትዮጵያ ወዳጆች ሲቀርቡ የነበሩ የመፍትሔሳቦችን የፌዴራል መንግሥት ሲያጤናቸው መቆየቱንና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በተካታታይ ያቀረበውን ጥያቄ ከተለያየ አቅጣጫ መመልከቱን አውስቷል፡፡ ጥያቄው በአንድ በኩል አካባቢውን ከሚመራ አካል የቀረበ በመሆኑና የትግራይም ሕዝብ ሰላምና ለውጥ ፈላጊ መሆኑን በተለያዩ መንገዶች ሲገልጽ የቆየ መሆኑ ስለሚታወቅ፣ የአገሪቱን ሉዓላዊነት ከውጭ ኃይሎች ከተሰነዘሩ ትንኮሳዎች ለመከላከልና ሁለተኛውን ዙር የህዳሴ ግድብ ለመሙላት ትኩረት መስጠት የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ በመሆኑ መቀበሉን አብራርቷል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በረሃ ከተበተነው ኃይል ውስጥ ሁኔታዎች ቢመቻቹለት ወደ ሰላም ሊመጣ የሚችል ኃይል ይኖራል ተብሎ ስለታመነ፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩን ጥያቄ መንግሥት በአዎንታዊነት መቀበሉንም ጠቁመዋል፡፡ ጥያቄው እንደተጠበቀ ሆኖ ዋነኞቹን የጥፋት መሪዎች ለሕግ የማቅረብ ሥራና የተጀመረው የምርመራ ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል እንደሚሆን ከግምት በማስገባትና አርሶ አደሩ ተረጋግቶ የእርሻ ሥራውን እንዲያከናውን፣ የዕርዳታ ሥራው ከወታደራዊ እንቅቃሴ ነፃ ሆኖ እንዲሠራጭ፣ ሰላምን የሚመርጡ የሕወሐት ርዝራዥ አካላት ወደ ሰላም መንገድ እንዲመጡ፣ ሳያውቁ ርዝራዡን የጥፋት ኃይል የተከተሉ እንደገና ለማሰብና ወደ ሰላማዊ መንገድ ለመምጣት ዕድል እንዲያገኙ ለማስቻል፣ ይህ የእርሻ ወቅት እስኪጠናቀቅ ድረስ የሚቆይ ያለቅድመ ሁኔታ በሰብዓዊነት ላይ የተመሠረተ በተናጠል የተኩስ አቁም ማድረጉን ይፋ አድርጓል፡፡

ሁሉም የፌዴራልና የክልል ሲቪልና ወታደራዊ ተቋማት፣ ከመንግሥት በሚሰጣቸው ዝርዝር አፈጻጸም መሠረት የተኩስ አቁም እወጃውን እንዲያከብሩና እንዲያስከብሩ ታዘዋል፡፡ ይኼን መልካም ዕድል ለክፉ የሚጠቀሙ ወገኖች ካጋጠሙ ግን አስፈላጊው ሕግን የማስከበር ተግባር እንደ አግባቡ የሚከናወን መሆኑንም አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በሥጋ ላይ አላግባብ እየተጨመረ ያለውን ዋጋ መንግሥት ሊቆጣጠረው ይገባል

በአገራችን የግብይት ሥርዓት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ ያልሆኑ ወይም ያልተገቡ የዋጋ...

ኢትዮጵያን የተባበረ ክንድ እንጂ የተናጠል ጥረት አይታደጋትም!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከምትገኝበት ውጥንቅጥ ውስጥ የምትወጣበት ዕድል ማግኘት...

የፖለቲካ ቅኝቱ የሕዝባችንን ታሪካዊ ትስስር ለምን አያከብርም?

በንጉሥ ወዳጅነው የዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መራሹ የ2010 ዓ.ም. የለውጥ መንግሥት...

ዛሬም ኧረ በሕግ!

በገነት ዓለሙ በዚህ በያዝነው ሚያዝያ/ግንቦት ወይም ሜይ ወር ውስጥ የተከበረው፣...