Saturday, May 18, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

​​​​​​​[ክቡር ሚኒስትሩ ይፋ የሚደረገውን መግለጫ በተመለከተ ከአማካሪያቸው ጋር እየመከሩ ነው]

[ክቡር ሚኒስትሩ ይፋ የሚደረገውን መግለጫ በተመለከተ ከአማካሪያቸው ጋር እየመከሩ ነው]

 • ክቡር ሚኒስትር ከጊዜያዊ አስተዳደሩ የቀረበልን ጥያቄ የተኩስ አቁም ስምምነት ነው የሚለው።
 • መቼ አጣሁት እሱን?
 • ስለዚህ የእኛ መግለጫም በቀረበው መሠረት የተኩስ አቁም ስምምነት ቢባል አይሻልም?
 • ስምምነት! ጤነኛ አይደለህም እንዴ? 
 • አጠፋሁ እንዴ ክቡር ሚኒስትር? የቀረበልን ጥያቄ እንደዚያ አይደለም እንዴ? 
 • ጥያቄ ጥያቄ አትበልብኝ። 
 • እሺ፡፡ 
 • ስምምነት ይለኛል እንዴ? በፓርላማው አሸባሪ ተብሎ ከተሰየመ አካል ጋር ስምምነት መፈጸም ወንጀል መሆኑን አታውቅም?
 • አሃዘንግቼዋለሁ ክቡር ሚኒስትር፡፡ 
 • በዚህ አያያዝህ ራስህንም ሳትዘነጋ አትቀርም።
 • ይቅርታ ክቡር ሚኒስትርምን እንበለው ታዲያ?
 • የተናጠል በለው!
 • የተናጠል ምን?
 • ምን? ምን ማለት ነው? 
 • የተናጠል ምን ልበለው ማለቴ ነው። ውሳኔ ልበለው?
 • አንተ ሰው ….

 

 • ምን ይሻላል ታዲያ?
 • የተናጠል ተኩስ አቁም ማወጁን ያሳውቃል በል 
 • እሺ ክቡር ሚኒስትርይኸው ተስተካክሏል፡፡ 
 • ምን ቀረ አሁን?
 • አንድ ነገር ብቻ ነው የቀረው፡፡
 • ምንድነው?
 • መግለጫው በማን እንደተሰጠ መግለጽ ነው የቀረው ግን ችግር የለውም በእርሶ የተሰጠ መሆኑን አሰፍራለሁ፡፡ 
 • አንተ ሰው ኧረ ተው ወደ ቀልብህ ተመለስ?
 • እና በካቢኔው ስም ቢወጣ ይሻላል?
 • ምኑ ተነክቶ ነው ይኼ ሰው ዛሬ! 
 • ምን አሉኝ ክቡር ሚኒስትር?
 • ሁለቱንም እንዳትጠቀም!
 • እና በምን ስም ቢወጣ ይሻላል?
 • በሪፐብሊኩ መንግሥት በል!
 • ጥሩ እንዳሉት አደርጋለሁ። አልቋል።
 • ውጣልኝ አሁን!
 • እሺእንዳሉት እወጣለሁ ክቡር ሚኒስትር። 

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ አንድ ተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ጋር እየደወሉ ነው] 

 • እንዴ! አሉ እንዴ ክቡር ሚኒስትር?
 • አለሁ …ቦታ ብቻ ነው የቀየርኩት።

 

 • ረዥም ጊዜ ሆነኝ ካየሁዎት ብዬ ነው ክቡር ሚኒስትር።
 • እውነት ነው… ውጤት እንዴት ሆነ? መቼም ከተማውን ሳታሸንፉ አልቀረም አይደል?
 • አይ ክቡር ሚኒስትር እሱን አያንሱት እስቲ፡፡ 
 • ለምን ….ምን ያህል አገኛችሁ?
 • ውጤቱን አያንሱት ክቡር ሚኒስትር …
 • ምነው?
 • የምርጫ ሕጉ አይፈቅድም፡፡ 
 • ምንድነው የማይፈቅደው፡፡ 
 • ቦርዱ ይፋ ሳያደርግ ውጤት መናገር ደንቡ አይፈቅድም፡፡ 
 • ለእኔ ብትነግረኝ ብዬ እንጂ ይፋ እንድታደርገው እንኳን አልነበረም፡፡ 
 • አይ ይቅር …ውጤቱስ ይቅር ..
 • ለነገሩ ሙሉውን ባታሸንፉ እንኳን ለጥምር መንግሥት የሚሆን አታጡም?
 • እርስዎ ቢኖሩ ነበራ?
 • እንዴት?
 • የጠፉ ኮንዶሚኒየም ቤቶችን እያጋለጥን ወደ ድምፅ እንቀይራቸው ነበር፡፡
 • ስለዚህ ባለፈው ያጋለጣችሁትን ያህል ድምፅ አግኝታችኋል ማለት ነዋ?
 • ውጤቱን አይጠይቁኝ አልኩዎት እኮ ክቡር ሚኒስትር? 
 • ለነገሩ ምንም ድምፅ ባታገኙም ጥምር መንግሥት መመሥረት ትችላላችሁ።
 • እንዴት አድርገን? ተሳስተዋል ሕጉ አይፈቅድም!
 • ውጤቱን ለማወቅ ብዬ ነው።
 • ከዚህ በኋላ አይደውሉልኝ ክቡር ሚኒስትር፡፡ 

 

[ክቡር ሚኒስትሩ በሰሞኑ መግለጫ ላይ ከአንድ ክልል ባለሥጣን ጋር በስልክ እየተወያዩ ነው]

 • ክቡር ሚኒስትር ፌዴራል መንግሥት መግለጫ ሲያወጣ እኛን መቼ አማከረ?
 • የፌዴራል መንግሥት በሥልጣን ክልሉ ተወስኖ ነው መግለጫ ያወጣው።
 • የእኛ መግለጫም በሥልጣን ክልላችን የተወሰነ እንጂ ስለሌላ አካባቢ አላነሳንም። 
 • ያወጣችሁት መግለጫ በክልሉ የተወሰነ ነው ለማለት አይቻልም። 
 • እንዴት? 
 • መግለጫውን አሁን ለማውጣት መጣደፍ መልዕክቱ ሌላ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡
 • ግልጽ የሆነው ምንድነው?
 • መልዕክቱ፡፡ 
 • ምንድነው መልዕክቱ?
 • ግልጽ ነው?
 • ክቡር ሚኒስትር ሊነግሩኝ የፈለጉትን በግልጽ ይንገሩኝ እባክዎትን?
 • በመካከላችን ክፍተት የሚፈጥር ነገር መፍጠር ጊዜው አይደለም ለማለት ነው።
 • ጊዜው ማለት?
 • ቢያንስ መንግሥት እስኪመሠረት እንዲህ ዓይነት ነገር ውስጥ መግባት ጥሩ አይደለም?
 • እሱ ነገር አያሳስብዎት ክቡር ሚኒስትር፡፡ 
 • ምኑ?
 • መንግሥት መመሥረት!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

ለፖለቲካዊም ይሁን ኢኮኖሚያዊ ትግል መቀዛቀዝ ምክንያቱ የጠራ ርዕዮተ ዓለም አለመኖር ወይስ የምሁራን መዳከም?

መሬት ላራሹ ብለው በተነሱ ተማሪዎችና ምሁራን ድምፅ የተቀጣጠለው የመጀመሪያው...

በአዲስ አበባ ለሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚሰጡ ድጋፎችንና መሥፈርቶችን ያካተተ አዲስ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማው ወስጥ ለሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች...

የዘንድሮ የወጭ ንግድ ገቢ ከዕቅዱም ሆነ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ መሆኑ ተገለጸ

የኢትዮጵያ የወጭ ንግድ ገቢ በተያዘው የበጀት ዓመትም የታቀደውን ያህል...

ሕይወትም እንዲህ ናት!

ከዊንጌት ወደ አየር ጤና ነው የዛሬው የጉዞ መስመራችን፡፡ አንዳንዴ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ የቢሮ ሥራቸውን አጠናቀው ከውጭ አገር የመጣ ወንድማቸውን ለመጠየቅ ያረፈበት ገስት ሀውስ ሲደርሱ ወንድማቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ፕሮግራም በመገረም እየተከታተለ አገኙት]

ውይ መጣህ እንዴ? እስኪ አረፍ በል፡፡ ምንድነው እንዲህ ያስደነቀህ? ተደንቄ ሳይሆን ግራ ግብት ብሎኝ ነው። ምኑ ነው ግራ ያጋባህ? የድልድይ ማስመረቅና የድልድይ ማፍረስ ነገር ነዋ። አልገባኝም? አለቃችሁ ድልድይ ሲያስመርቁ የተናገሩትን...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከዘመዶቻቸውና ቤተሰቦቻቸው ጋር ሆነው በዓሉን በመኖሪያ ቤታቸው እያከበሩ ነው። ባለቤታቸውም ለበዓሉ የተዘጋጀውን ዳቦ ባርከው እንዲቆርሱ ለሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

በል ዳቦውን ባርክና ቁረስልንና በዓሉን እናክብር? ጥሩ ወዲህ አምጪው... አዎ! በል መርቅ... ከዓመት ዓመት ያድርሰን... ኧረ በሥርዓት መርቅ ተው? ከዓመት ዓመት ያድርሰን አልኩኝ እኮ ...አልሰማሽም? ከዓመት ዓመት መድረሱ ብቻ ምን...

[ክቡር ሚኒስትር መንግሥት ይፋ ያደረገውን ንቅናቄ አመራሮችና ቤተሰቦቻቸው በግንባር ቀደምትነት እንዲቀላቀሉ መታዘዙን ለባለቤታቸው እያጫወቱ በዚያውም ወደተከፈተው የባንክ ሒሳብ ገንዘብ እንዲያስተላልፉ እያግባቧቸው ነው]

በይ እስኪ ሞባይልሽን አውጪና ወደዚህ የባንክ ሒሳብ አንድ ሺሕ ብር አስተላልፊ? ለምን? መንግሥት ያስጀመረውን ንቅናቄ አመራሩ ከነቤተሰቡ ግንባር ቀደም ሆኖ እንዲደግፍ ታዟል። የምን ንቅናቄ ነው መንግሥት ያስጀመረው? ‹‹ፅዱ...