Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመግታት የሚጠበቀው የመንግሥትና የግል ጤና ተቋማት ቅንጅት

የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመግታት የሚጠበቀው የመንግሥትና የግል ጤና ተቋማት ቅንጅት

ቀን:

የዓለም ማኅበረሰብ ከፍተኛ የጤና ሥጋት የሆነና የሥርጭት አድማሱን እያሰፋ የመጣው የመጀመርያውና ሁለተኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ከአራት ሺሕ በላይ ሰዎችን ለሕልፈተ ሕይወትና ለጤንነት መታወክ ዳርጓቸዋል፡፡ አሁን ደግሞ ሦስተኛው ዙር እየመጣ ነው፡፡ ወረርሽኙ የተጠበቀውን ሥጋት እንዳያስከትል የመንግሥትና የግል ጤና ተቋማት በቅንጅት መንቀሳቀስ እንደሚጠበቅባቸው እየተገለጸ ነው፡፡

በጤና ሚኒስቴር የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተርና የኮቪድ-19 መከላከል ግብረ ኃይል አስተባባሪ ያዕቆብ ሰማን (ዶ/ር) እንደተናገሩት፣ ተቋማት በቅንጅት ሊሠሩ የሚችሉት ባለፉት ዙሮች የተገኙትን ልምዶችን በመቀመር፣ የየራሳቸውን የውስጥ አደረጃጀት በበለጠ አጠናክረው ሲንቀሳቀሱና የሪፈራል ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ መረጃዎችን በወቅቱ መለዋወጥ የቻሉ እንደሆነ ነው፡፡

በኮቪድ-19 ላይ የሕክምና አገልግሎት ለሚሰጡ የመንግሥትና የግል ጤና ተቋማት አገልግሎት የሚውሉ ‹‹አራት-ፒ›› የተባለ ስታንዳርድ እንደተዘጋጀ፣ ከስታንዳርዱም መካከል ተቋማቱ አገልግሎት መስጠት የሚያስችላቸው ዕቃዎችና መሳሪያዎች፣ እንዲሁም ባለሙያዎች አላቸው ወይ? የሆስፒታሉ ሕንፃ ለሕክምና ምቹ ነው ወይ? የሚሉ መሥፈርቶች እንደሚገኙባቸው ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ.ም. እንደተከሰተ፣ ቫይረሱ በደንብ ባለመታወቁ የተነሳ ብዙ ውጣ ውረዶችን እንዳስከተለ፣ ለዚህ ሕክምና መስጠት የሚችሉ የመንግሥት ጤና ተቋማትን የመለየት ችግር ሁሉ ተፈጥሮ እንደነበር፣ ይህ ከሆነ ከጥቂት ቀናትና ቫይረሱ በደንብ ከታወቀ በኋላ ሀብት የማሰባሰብና ከረጂ ድርጅቶች ማሽኖችን፣ የመታከሚያ ዕቃዎችንና መድኃኒቶችን ማግኘትና በአገር ደረጃ ወደ 20,000 የሚጠጉ አልጋዎችን ማደራጀት እንደተቻለ ነው የገለጹት፡፡

የሕክምና አገልግሎቱም መስጠት የተጀመረው በሦስት ዓይነት አካሄዶች ሲሆን  እነርሱም ‹‹ማይልድ፣ ሞደሬትና ሲቪየር›› እንደሚባሉ ከእነዚህም አካሄዶች መካከል ‹‹ማይልድ›› ማለት ብዙ ሕክምና ሳያስፈልጋቸው ተኝተው ቫይረሱ ሲለቃቸው የሚወጡ፣ ‹‹ሞደሬት›› ማለት ደግሞ የኦክስጅን ሕክምና ብቻ ተደርጎላቸው ወደ ሜካኒካል ቬንትሌተር ሳይሄዱ የሚወጡ፣ ሦስተኛውና የመጨረሻው አካሄድ ‹‹ሲቪየር›› የሚባለው ግን መካኒካል ቬንትሌተርና ክሪቲካል የሆነ ሕክምና የሚፈልጉ ናቸው፡፡

በተለይ ሞደሬትና ሲቪየር ሕክምና መስጠት የሚችሉ የጤና ተቋማትን ማቋቋም እጅግ በጣም ውድ ነው፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው የጽኑ ሕሙማን የሚገለገሉበት አልጋና መካኒካል ቬንትሌተር የሚያስፈልገው በመሆኑ ነው፡፡ መንግሥትም እነዚህን አገልግሎት የመስጠት አቅም ያላቸውን የጤና ተቋማት ማቋቋም ችግር ገጥሞት እንደነበር፣ ይህንንም ችግር ለመቋቋም በመጀመርያ ደረጃ የተወሰደው ዕርምጃ ቢኖር ይህ ዓይነቱን አገልግሎት መስጠት የሚችሉና ለዚህም ፍላጎት ያላቸውን የግል የጤና ተቋማትን መጠየቅና ማፈላለግ እንደነበር ነው የገለጹት፡፡

በዚህም የተነሳ የግል ጤና ተቋማት ባለቤቶች፣ የተቋማት አሶሴሽኖችና ፌዴሬሽኖች በተገኙበት ስብሰባ ከተደረገና በጉዳዩ ላይ ውይይት ከተካሄደ በኋላ ፍላጎታቸውን ያሳዩት ሁለት የግል ጤና ተቋማት እንደተገኙ ከእነዚህም መካከል አንደኛው ሃሌሉያ አጠቃላይ የግል ሆስፒታል እንደሆነ፣ ቀስ በቀስም ወደ አገልግሎቱ የገቡ የግል ጤና ተቋማት ቁጥር ወደ ሰባት ከፍ እንዳሉ ነው ያመለከቱት፡፡

የግል ጤና ተቋማት የሚያስከፍሉትን ዋጋ በተመለከተ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከመውጣቱ በፊት የመጀመርያው መመርያ እንደወጣ፣ በዚህም መመርያ መሠረት የዋጋ ጣሪያ እንደተቀመጠ አዋጁ ከወጣ በኋላ ግን ሁለተኛውና የተሻሻለው መመርያ እንደወጣ፣ በሁለተኛውም መመርያ መሠረት ታካሚዎች ለአገልግሎት የሚከፍሉት የገንዘብ አቅም ከጤና ተቋማቱ ጋር ተነጋግረው እንደወሰኑ ወይም ዋጋ በጤና ተቋማቱና ሕክምናን ፈልጎ ከሚመጣው ታካሚ መካከል በሚደረግ ስምምነት መሠረት የሚወሰን እንደሚሆን ነው የገለጹት፡፡

ይህ ሁሉ ሆኖ ግን የግል ጤና ተቋማት የሚያስከፍሉት ገንዘብ ከአቅም በላይ ነው የሚል እሮሮ በየጊዜው እንደሚሰማ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ አንድ ታካሚ ጽኑ ሕሙማን ክፍል ሲገባ በቀን 8,000 ዶላር፣ ለመደበኛ ሕክምና አንድ ቀን አድሮ ሲወጣ በቀን በአማካይ 1,000 ዶላር እንደሚጠይቅ ሳይገልጹ አላለፉም፡፡ ከዚህ አኳያ በኮቪድም ሆነ በሌላ በሽታ የግል ጤና ተቋም ለሚሰጠው አገልግሎት የሚያስከፍለው ገንዘብ የተጋነነ ነው፣ አይደለም ለማለት በመጀመርያ የዓለምንና የአካባቢ አገሮችን መነሻ (ቤንችማርክ) ማየት በጣም አስፈላጊ እንዲሆን ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ ውጭ በሆነ መልኩ በጣም የተጋነነ ዋጋ የሚያስከፍል ተቋም ካለ ፈቃድ ከሰጠው መንግሥታዊ አካል ከበቂ ማስረጃ ጋር መከሰስና ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ መቀጣት አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ተገቢ ባልሆነ መንገድ የሚደረግ አታካሮና ውንጀላ የግል ተቋማት ወደፊት እንዳይመጡ ከፍ ሲልም አገልግሎታቸውን ለማቆም እንዲገደዱ ይገፋፋቸዋል፡፡ ይህም በመንግሥት የጤና ተቋማት ጫና እንደሚፈጥር፣ ጫናውም ወረፋ ወደማስያዝ  ከፍ እንደሚልና ይህ ዓይነቱም ሁኔታን ሞትን እንደሚያፋጥን ከዳይሬክተሩ ማብራሪያ ለመረዳት ተችሏል፡፡

የኢትዮጵያ የግል ሆስፒታሎችና ጤና ማዕከላት ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮሐንስ በሻህ ኢትዮጵያ በማደግ ላይ የምትገኝና ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጨምሮ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች የተንሰራፋበት እንደመሆኑ መጠን፣ የግል ጤና ተቋማት ካልታከሉበት በስተቀር በመንግሥት ጤና ተቋማት ብቻ ለችግሮቹ መፍትሔ ለመሻት መሞከሩ የትም እንደማያደርስ ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...