Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊከስምንት ቢሊዮን ብር በላይ የሚፈጀው የጤና መሪ ዕቅድ

ከስምንት ቢሊዮን ብር በላይ የሚፈጀው የጤና መሪ ዕቅድ

ቀን:

የጤና ሚኒስቴር በመተግበር ላይ በሚገኘው በሁለተኛው የአምስት ዓመት ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በዋናነት ትኩረት ካደረገባቸው አጀንዳዎች ውስጥ አንደኛውና ዋነኛው የጤናው ምላሽ ሥርዓትን ማሻሻል፣ ከድንገተኛ ጤና አደጋዎች ኅብረተሰቡን በመከላከልና የድንገተኛ አደጋ ፅኑ ሕሙማን አገልግሎትን በማስፋት ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ለዜጎች ማዳረስ ነው፡፡

የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ መምራት እንዲያስችል፣ ሚኒስቴሩ አገር አቀፍ የድንገተኛ አደጋና የፅኑ ሕሙማን ሕክምና የአምስት ዓመት መሪ ዕቅድን ከተለያዩ የባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር አዘጋጅቶ ሰኔ 1 ቀን 2013 ዓ.ም. ይፋ አድርጓል፡፡

መሪ ዕቅዱ በሒልተን አዲስ የስብሰባ አዳራሽ ይፋ ሲደረግ የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) ባደረጉት ንግግር፣ መሪ ዕቅዱ ከአምስት ዓመቱ የጤና ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ጋር ተሰናስሎ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ማኅበረሰቡን ከተለያዩ አደጋዎች ለመጠበቅ፣ ጥራቱን የጠበቀና ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ለመስጠትም ታሳቢ መደረጉን፣ በተለያዩ ምክንያቶች ተፈጥሮዓዊና ሰው ሠራሽ አደጋዎች የተበራከቱበት ወቅት እንደመሆኑም ዕቅዱ ይህንን የድንገተኛና የፅኑ ሕሙማን ሕክምና በተቀናጀ መልኩ ለመመለስ እንደሚያስችል አውስተዋል፡፡

ማንኛውም የጤና አገልግሎት መሠረቱ ባለሙያ እንደሆነ፣ በዚህም የተነሳ በሕክምና፣ በነርስና በሌሎችም ሙያዎች የተካኑ በማፍራት ረገድ (ስፔሻሊቲ) ካለፉት ቅርብ ዓመታት ወዲህ እየተስፋፋ እንደመጣ፣ ይህ ዓይነቱንም አካሄድ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል፡፡

በሚኒስትሯ መግለጫ እንደተገለጸው፣ አደጋዎች ሲከሰቱ ከቅድመ ሆስፒታል ጀምሮ እስከ ፅኑ ሕሙማን ሕክምና ድረስ ያሉ ምዕራፎች በመሪ ዕቅዱ ላይ ተካቷል፡፡ በዘርፉ ከመንግሥት፣ ከክልሎችና ከኅብረተሰቡ በተገኘ መዋጮ 3000 አምቡላንሶች በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች አገልግሎት የሚሰጡ ይሆናል፡፡

ኅብረተሰቡ አገልግሎቱን በቀላሉ ማግኘት የሚችልበት ሥርዓት መዘርጋትና የጥሪ ማዕከላትን ማስፋፋትም በዕቅዱ ውስጥ ተይዟል ያሉት ሚኒስትሯ፣ በቀጣይ አምስት ዓመታት በድንገተኛ አደጋና የፅኑ ሕሙማን ሕክምናን በማጣት የሚደርሰውን የሞትና የአካል መጉደል ለመከላከልም ዓይነተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

ለድንገተኛና ፅኑ ሕሙማን ሕክምና የሚሆኑ መሣሪያዎችም ሆኑ መድኃኒቶች ዋጋቸው ውድ መሆናቸውን በማውሳትዕቅዱ ተፈጻሚነት ግን የሁሉም ርብርብ ያስፈልጋል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

መሪ ዕቅዱ ተገልጋዩን ያማከለና ጥራት ያለው የድንገተኛና የፅኑ ሕሙማን ሕክምና የሚያሰጥ መሆኑን ያመለከቱት በጤና ሚኒስቴር የድንገተኛና ፅኑ ሕሙማን ሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር አለኝታ ገብረየሱስ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

የድንገተኛ ሕክምናን ለማዳረስ የተቀናጀና አቅም ያለው ባለሙያ ያስፈልጋል ባሉት ዳይሬክተሯ አነጋገር ዕቅዱ ቅንጅታዊ አሠራርን፣ ትብብርንና መደጋገፍን ያማከለና በዓለምና በአገር ደረጃ ካሉት አጋር ድርጅቶች ጋር በቅርብና በጋራ አብሮ መሥራትን እንደ ዋነኛ መገልገያ አድርጎ ይዟል፡፡

አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ስድስት ከተሞች ለሚገኙ የመንግሥት ጤና ተቋማት የድንገተኛ አደጋና ፅኑ ሕክምና ክፍሎች መቋቋማቸውን ዳይሬክተሯ ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

አምቡላንሶቹ የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት እንዲሰጡ በባለሙያና በሚያስፈልጋቸው ግብዓቶች የተሟላ እንዲሆኑ ለማድረግ ከጠብታ አምቡላንስ ጋር በመተባበር የተጀመሩ ሥራዎች መኖራቸውን ጠቁመው፣ ጅማሮውም በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑንና ለሁሉም ሰፋ ያለ ሙዓለ ንዋይ የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ የተነሳ በየተራ እንዲከናወኑ መደረጉን ነው ያመለከቱት፡፡

አምቡላንሶች ታካሚውን ለሚመላለስ እንደ ትራንስፖርት መጠቀሚያ ብቻ ሳይሆን የሕክምና አገልግሎት የሚሰጥባቸው መሆን እንዳለባቸው ለዚህም ልዩ ትኩረት እንደተሰጠው፣ ከዚህም ሌላ የአምቡላንስ አገልግሎት ፈጣንና በቴክኖሎጂ የታገዘ እንደሆነና ለዚህም የስምሪት ማዕከላት እንዲቋቋሙ ለማድረግ የሚያስችል ሥራ በዕቅዱ እንደተካተተ አስረድተዋል፡፡

የአምስት ዓመቱን መሪ ዕቅድ ለመተግበር 8.37 ቢሊዮን ብር (200 ሚሊዮን ዶላር) እንደሚያስፈልግ፣ የገንዘቡም ምንጭ በዋነኝነት መንግሥት ሲሆን ከባለድርሻ አካላትም የሚደረግ ዕገዛ እንደሚኖር ተጠቁሟል፡፡

ከሚኒስትሯ ማብራሪያ ለመረዳት እንደተቻለው፣ በአሁኑ ጊዜ በመላው የአገሪቱ ክፍሎች 53 የፅኑ ሕሙማን ሕክምና ክፍሎች አሉ፡፡ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ፈተና ቢሆንም የተለያዩ የጤና ሥርዓቶችን ለማጠናከር እንደ መልካም አጋጣሚ ሆኗል፡፡ ከዚህ አኳያ 35 አዳዲስና ተጨማሪ የፅኑ ሕክምና ክፍል እየተቋቋሙ ነው፡፡

ይህንን መዋቅራዊ በሆነ መልኩ የማስቀጠልና የማስፋት ሥራ እንደሚቀጥል፣ ኦክስጅን ማምረት መቻልና ተደራሽነትንም ትልቅ ትኩረት እንደሚሰጠውም ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...